1For this cause, I Paul, the prisoner of Christ Jesus for you the nations,
1ስለዚህም አሕዛብ ስለ ሆናችሁ ስለ እናንተ የክርስቶስ ኢየሱስ እስር የሆንሁ እኔ ጳውሎስ ለእግዚአብሔር እንበረከካለሁ።
2if, indeed, ye did hear of the dispensation of the grace of God that was given to me in regard to you,
2ለእናንተ ስለ ተሰጠኝ ስለ እግዚአብሔር ጸጋ መጋቢነት በእርግጥ ሰምታችኋል፤
3that by revelation He made known to me the secret, according as I wrote before in few [words] —
3አስቀድሜ በአጭሩ እንደ ጻፍሁ፥ ይህን ምሥጢር በመግለጥ አስታወቀኝ፤
4in regard to which ye are able, reading [it], to understand my knowledge in the secret of the Christ,
4ይህንም ስታነቡ የክርስቶስን ምሥጢር እንዴት እንደማስተውል ልትመለከቱ ትችላላችሁ፤
5which in other generations was not made known to the sons of men, as it was now revealed to His holy apostles and prophets in the Spirit —
5ይህም፥ አሕዛብ አብረው እንዲወርሱ፥ በአንድ አካልም አብረው እንዲሆኑ፥ በወንጌልም መስበክ በክርስቶስ ኢየሱስ በሆነ የተስፋ ቃል አብረው እንዲካፈሉ፥ ለቅዱሳን ሐዋርያትና ለነቢያት በመንፈስ አሁን እንደ ተገለጠ በሌሎቹ ትውልዶች ዘንድ ለሰው ልጆች አልታወቀም።
6that the nations be fellow-heirs, and of the same body, and partakers of His promise in the Christ, through the good news,
7እንደ ኃይሉ ሥራ እንደ ተሰጠኝም እንደ እግዚአብሔር ጸጋ ስጦታ መጠንየወንጌል አገልጋይ ሆንሁለት።
7of which I became a ministrant, according to the gift of the grace of God that was given to me, according to the working of His power;
8ፍለጋ የሌለውን የክርስቶስን ባለ ጠግነት ለአሕዛብ እሰብክ ዘንድ፥ ሁሉንም በፈጠረው በእግዚአብሔር ከዘላለም የተሰወረው የምሥጢር ሥርዓት ምን እንደሆነ ለሁሉ እገልጥ ዘንድ ይህ ጸጋ ከቅዱሳን ሁሉ ይልቅ ለማንስ ለኔ ተሰጠ፤
8to me — the less than the least of all the saints — was given this grace, among the nations to proclaim good news — the untraceable riches of the Christ,
10ብዙ ልዩ ልዩ የእግዚአብሔር ጥበብ አሁን በቤተ ክርስቲያን በኩል በሰማያዊ ስፍራ ውስጥ ላሉት አለቆችና ሥልጣናት ትታወቅ ዘንድ፤
9and to cause all to see what [is] the fellowship of the secret that hath been hid from the ages in God, who the all things did create by Jesus Christ,
11ይህም በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የፈጸመው የዘላለም አሳብ ነበረ፥
10that there might be made known now to the principalities and the authorities in the heavenly [places], through the assembly, the manifold wisdom of God,
12በእርሱም ዘንድ ባለ እምነታችን በኩል በመታመን ድፍረትና መግባት በእርሱ አለን።
11according to a purpose of the ages, which He made in Christ Jesus our Lord,
13ስለዚህ ስለ እናንተ ስላለ መከራዬ እንዳትታክቱ እለምናችኋለሁ፥ ክብራችሁ ነውና።
12in whom we have the freedom and the access in confidence through the faith of him,
14ስለዚህ ምክንያት በሰማይና በምድር ያለ አባትነት ሁሉ ከሚሰየምበት ከአብ ፊት እንበረከካለሁ፤
13wherefore, I ask [you] not to faint in my tribulations for you, which is your glory.
16በመንፈሱ በውስጥ ሰውነታችሁ በኃይል እንድትጠነክሩ ክርስቶስም በልባችሁ በእምነት እንዲኖር እንደ ክብሩ ባለ ጠግነት መጠን ይስጣችሁ፤ የእናንተ ሥርና መሠረት በፍቅር ይጸና ዘንድ፥
14For this cause I bow my knees unto the Father of our Lord Jesus Christ,
18ከቅዱሳን ሁሉ ጋር ስፋቱና ርዝመቱ ከፍታውም ጥልቅነቱም ምን ያህል መሆኑን ለማስተዋል፥ ከመታወቅም የሚያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር ለማወቅ ትበረቱ ዘንድ፥ እስከ እግዚአብሔርም ፍጹም ሙላት ደርሳችሁ ትሞሉ ዘንድ።
15of whom the whole family in the heavens and on earth is named,
20እንግዲህ በእኛ እንደሚሠራው ኃይል መጠን ከምንለምነው ወይም ከምናስበው ሁሉ ይልቅ እጅግ አብልጦ ሊያደርግ ለሚቻለው፥
16that He may give to you, according to the riches of His glory, with might to be strengthened through His Spirit, in regard to the inner man,
21ለእርሱ በቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ኢየሱስ እስከ ትውልዶች ሁሉ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።
17that the Christ may dwell through the faith in your hearts, in love having been rooted and founded,
18that ye may be in strength to comprehend, with all the saints, what [is] the breadth, and length, and depth, and height,
19to know also the love of the Christ that is exceeding the knowledge, that ye may be filled — to all the fulness of God;
20and to Him who is able above all things to do exceeding abundantly what we ask or think, according to the power that is working in us,
21to Him [is] the glory in the assembly in Christ Jesus, to all the generations of the age of the ages. Amen.