1And I saw a new heaven and a new earth, for the first heaven and the first earth did pass away, and the sea is not any more;
1አዲስ ሰማይንና አዲስ ምድርንም አየሁ፥ ፊተኛው ሰማይና ፊተኛይቱ ምድር አልፈዋልና፥ ባሕርም ወደ ፊት የለም።
2and I, John, saw the holy city — new Jerusalem — coming down from God out of the heaven, made ready as a bride adorned for her husband;
2ቅድስቲቱም ከተማ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም፥ ለባልዋ እንደ ተሸለመች ሙሽራ ተዘጋጅታ፥ ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አየሁ።
3and I heard a great voice out of the heaven, saying, `Lo, the tabernacle of God [is] with men, and He will tabernacle with them, and they shall be His peoples, and God Himself shall be with them — their God,
3ታላቅም ድምፅ ከሰማይ። እነሆ፥ የእግዚአብሔር ድንኳን በሰዎች መካከል ነው ከእነርሱም ጋር ያድራል፥ እነርሱም ሕዝቡ ይሆናሉ እግዚአብሔርም እርሱ ራሱ ከእነርሱ ጋር ሆኖ አምላካቸው ይሆናል፤
4and God shall wipe away every tear from their eyes, and the death shall not be any more, nor sorrow, nor crying, nor shall there be any more pain, because the first things did go away.`
4እንባዎችንም ሁሉ ከዓይኖቻቸው ያብሳል፥ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ ኀዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ የቀደመው ሥርዓት አልፎአልና ብሎ ሲናገር ሰማሁ።
5And He who is sitting upon the throne said, `Lo, new I make all things; and He saith to me, `Write, because these words are true and stedfast;`
5በዙፋንም የተቀመጠው። እነሆ፥ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ አለ። ለእኔም። እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛዎች ናቸውና ጻፍ አለኝ።
6and He said to me, `It hath been done! I am the Alpha and the Omega, the Beginning and the End; I, to him who is thirsting, will give of the fountain of the water of the life freely;
6አለኝም። ተፈጽሞአል። አልፋና ዖሜጋ፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ። ለተጠማ ከሕይወት ውኃ ምንጭ እንዲያው እኔ እሰጣለሁ።
7he who is overcoming shall inherit all things, and I will be to him — a God, and he shall be to me — the son,
7ድል የሚነሣ ይህን ይወርሳል አምላክም እሆነዋለሁ እርሱም ልጅ ይሆነኛል።
8and to fearful, and unstedfast, and abominable, and murderers, and whoremongers, and sorcerers, and idolaters, and all the liars, their part [is] in the lake that is burning with fire and brimstone, which is a second death.`
8ዳሩ ግን የሚፈሩና የማያምኑ የርኵሳንም የነፍሰ ገዳዮችም የሴሰኛዎችም የአስማተኛዎችም ጣዖትንም የሚያመልኩ የሐሰተኛዎችም ሁሉ ዕድላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ነው፤ ይኸውም ሁለተኛው ሞት ነው።
9And there came unto me one of the seven messengers, who have the seven vials that are full of the seven last plagues, and he spake with me, saying, `Come, I will shew thee the bride of the Lamb — the wife,`
9ሰባቱም ኋለኛዎች መቅሠፍቶች የሞሉባቸውን ሰባቱን ጽዋዎች ከያዙት ከሰባቱ መላእክት አንዱ መጥቶ። ወደዚህ ና፥ የበጉንም ሚስት ሙሽራይቱን አሳይሃለሁ ብሎ ተናገረኝ።
10and he carried me away in the Spirit to a mountain great and high, and did shew to me the great city, the holy Jerusalem, coming down out of the heaven from God,
10በመንፈስም ወደ ታላቅና ወደ ረጅም ተራራ ወሰደኝ፥ የእግዚአብሔርም ክብር ያለባትን ቅድስቲቱን ከተማ ኢየሩሳሌምን ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አሳየኝ፤ ብርሃንዋም እጅግ እንደ ከበረ ድንጋይ እንደ ኢያሰጲድ ድንጋይ ሆኖ እንደ ብርሌ የጠራ ነበረ፤
11having the glory of God, and her light [is] like a stone most precious, as a jasper stone clear as crystal,
12ታላቅና ረጅም ቅጥር ነበራት፥ አሥራ ሁለትም ደጆች ነበሩአት በደጆቹም አሥራ ሁለት መላእክት ቆሙ፥ የአሥራ ሁለቱም የእስራኤል ልጆች ነገዶች ስሞች ተጽፈውባቸው ነበር።
12having also a wall great and high, having twelve gates, and at the gates twelve messengers, and names written thereon, which are [those] of the twelve tribes of the sons of Israel,
13በምሥራቅ ሦስት ደጆች፥ በሰሜንም ሦስት ደጆች፥ በደቡብም ሦስት ደጆች፥ በምዕራብም ሦስት ደጆች ነበሩ።
13at the east three gates, at the north three gates, at the south three gates, at the west three gates;
14ለከተማይቱም ቅጥር አሥራ ሁለት መሠረቶች ነበሩአት፥ በእነርሱም ውስጥ የአሥራ ሁለቱ የበጉ ሐዋርያት ስሞች ተጽፈው ነበር።
14and the wall of the city had twelve foundations, and in them names of the twelve apostles of the Lamb.
15የተናገረኝም ከተማይቱንና ደጆችዋን ቅጥርዋንም ይለካ ዘንድ የወርቅ ዘንግ ነበረው።
15And he who is speaking with me had a golden reed, that he may measure the city, and its gates, and its wall;
16ከተማይቱም አራት ማዕዘን ነበራት፥ ርዝመትዋም እንደ ስፋትዋ ልክ ነበረ። ከተማይቱንም በዘንግ ለካት አሥራ ሁለትም ሺህ ምዕራፍ ሆነች፤ ርዝመትዋና ስፋትዋ ከፍታዋም ትክክል ነው።
16and the city lieth square, and the length of it is as great as the breadth; and he did measure the city with the reed — furlongs twelve thousand; the length, and the breadth, and the height, of it are equal;
17ቅጥርዋንም ለካ፥ መቶ አርባ አራት ክንድ በሰው ልክ፥ እርሱም በመልአክ ልክ።
17and he measured its wall, an hundred forty-four cubits, the measure of a man, that is, of the messenger;
18ቅጥርዋም ከኢያሰጲድ የተሠራ ነበረ፥ ከተማይቱም ጥሩ ብርጭቆ የሚመስል ጥሩ ወርቅ ነበረች።
18and the building of its wall was jasper, and the city [is] pure gold — like to pure glass;
19የከተማይቱም ቅጥር መሠረት በከበረ ድንጋይ ሁሉ ተጌጦ ነበር፤ ፊተኛው መሠረት ኢያሰጲድ፥ ሁለተኛው ሰንፔር፥ ሦስተኛው ኬልቄዶን፥ አራተኛው መረግድ፥
19and the foundations of the wall of the city with every precious stone have been adorned; the first foundation jasper; the second, sapphire; the third, chalcedony; the fourth, emerald;
20አምስተኛው ሰርዶንክስ፥ ስድስተኛው ሰርድዮን፥ ሰባተኛው ክርስቲሎቤ፥ ስምንተኛው ቢረሌ፥ ዘጠነኛው ወራውሬ፥ አሥረኛው ክርስጵራስስ፥ አሥራ አንደኛው ያክንት፥ አሥራ ሁለተኛው አሜቴስጢኖስ ነበረ።
20the fifth, sardonyx; the sixth, sardius; the seventh, chrysolite; the eighth, beryl; the ninth, topaz; the tenth, chrysoprasus; the eleventh, jacinth; the twelfth, amethyst.
21አሥራ ሁለቱም ደጆች አሥራ ሁለት ዕንቆች ነበሩ፤ እየአንዳንዱ ደጅ ከአንድ ዕንቍ የተሠራ ነበረ። የከተማይቱም አደባባይ ጥሩ ብርጭቆ የሚመስል ጥሩ ወርቅ ነበረ።
21And the twelve gates [are] twelve pearls, each several one of the gates was of one pearl; and the broad-place of the city [is] pure gold — as transparent glass.
22ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክና በጉ መቅደስዋ ናቸውና መቅደስ በእርስዋ ዘንድ አላየሁም።
22And a sanctuary I did not see in it, for the Lord God, the Almighty, is its sanctuary, and the Lamb,
23ለከተማይቱም የእግዚአብሔር ክብር ስለሚያበራላት መብራትዋም በጉ ስለ ሆነ፥ ፀሐይ ወይም ጨረቃ እንዲያበሩላት አያስፈልጓትም ነበር።
23and the city hath no need of the sun, nor of the moon, that they may shine in it; for the glory of God did lighten it, and the lamp of it [is] the Lamb;
24አሕዛብም በብርሃንዋ ይመላለሳሉ፥ የምድርም ነገሥታት ክብራቸውን ወደ እርስዋ ያመጣሉ፤
24and the nations of the saved in its light shall walk, and the kings of the earth do bring their glory and honour into it,
25በዚያም ሌሊት ስለሌለ ደጆችዋ በቀን ከቶ አይዘጉም፥
25and its gates shall not at all be shut by day, for night shall not be there;
26የአሕዛብንም ግርማና ክብር ወደ እርስዋ ያመጣሉ።
26and they shall bring the glory and the honour of the nations into it;
27ለበጉም በሆነው በሕይወት መጽሐፍ ከተጻፉት በቀር፥ ጸያፍ ነገር ሁሉ ርኵሰትና ውሸትም የሚያደርግ ወደ እርስዋ ከቶ አይገባም።
27and there may not at all enter into it any thing defiling and doing abomination, and a lie, but — those written in the scroll of the life of the Lamb.