1እኔም፥ ወንድሞች ሆይ፥ ወደ እናንተ በመጣሁ ጊዜ በቃልና በጥበብ ብልጫ ለእግዚአብሔር ምስክርነቴን ለእናንተ እየነገርሁ አልመጣሁም።
1只傳耶穌基督釘十字架弟兄們,我從前到你們那裡去,並沒有用高言大智向你們傳講 神的奧祕。
2በመካከላችሁ ሳለሁ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር እርሱም እንደተሰቀለ ሌላ ነገር እንዳላውቅ ቆርጬ ነበርና።
2因為我曾立定主意,在你們中間甚麼都不想知道,只知道耶穌基督和他釘十字架的事。
3እኔም በድካምና በፍርሃት በብዙ መንቀጥቀጥም በእናንተ ዘንድ ነበርሁ፤
3我在你們那裡的時候,又軟弱又懼怕,而且戰戰兢兢;
4እምነታችሁም በእግዚአብሔር ኃይል እንጂ በሰው ጥበብ እንዳይሆን፥ ቃሌም ስብከቴም መንፈስንና ኃይልን በመግለጥ ነበረ እንጂ፥ በሚያባብል በጥበብ ቃል አልነበረም።
4我說的話、講的道,都不是用智慧的話去說服人,而是用聖靈和能力來證明,
6በበሰሉት መካከል ግን ጥበብን እንናገራለን፥ ነገር ግን የዚችን ዓለም ጥበብ አይደለም የሚሻሩትንም የዚችን ዓለም ገዦች ጥበብ አይደለም፤
5使你們的信不是憑著人的智慧,而是憑著 神的能力。
7ነገር ግን እግዚአብሔር አስቀድሞ ከዘመናት በፊት ለክብራችን የወሰነውን፥ ተሰውሮም የነበረውን የእግዚአብሔርን ጥበብ በምሥጢር እንናገራለን።
6屬靈的人看透萬事然而在信心成熟的人中間,我們也講智慧,但不是這世代的智慧,也不是這世代將要滅亡的執政者的智慧。
8ከዚችም ዓለም ገዦች አንዱ እንኳ ይህን ጥበብ አላወቀም፤ አውቀውስ ቢሆኑ የክብርን ጌታ ባልሰቀሉትም ነበር፤
7我們所講的,是從前隱藏的、 神奧祕的智慧,就是 神在萬世以前,為我們的榮耀所預定的;
9ነገር ግን። ዓይን ያላየችው ጆሮም ያልሰማው በሰውም ልብ ያልታሰበው እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀው ተብሎ እንድተጻፈ፥ እንዲህ እንናገራለን።
8這智慧,這世代執政的人沒有一個知道,如果他們知道,就不會把榮耀的主釘在十字架上了。
10መንፈስም የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ስንኳ ሳይቀር ሁሉን ይመረምራልና ለእኛ እግዚአብሔር በመንፈሱ በኩል ገለጠው።
9正如經上所記:“ 神為愛他的人所預備的,是眼睛未曾見過,耳朵未曾聽過,人心也未曾想到的。”
11በእርሱ ውስጥ ካለው ከሰው መንፈስ በቀር ለሰው ያለውን የሚያውቅ ሰው ማን ነው? እንዲሁም ደግሞ ከእግዚአብሔር መንፈስ በቀር ለእግዚአብሔር ያለውን ማንም አያውቅም።
10但 神卻藉著聖靈把這些向我們顯明了,因為聖靈測透萬事,連 神深奧的事也測透了。
12እኛ ግን ከእግዚአብሔር እንዲያው የተሰጠንን እናውቅ ዘንድ ከእግዚአብሔር የሆነውን መንፈስ እንጂ የዓለምን መንፈስ አልተቀበልንም።
11除了在人裡面的靈,誰能知道人的事呢?同樣,除了 神的靈,也沒有人知道 神的事。
13መንፈሳዊውን ነገር ከመንፈሳዊው ነገር ጋር አስተያይተን መንፈስ በሚያስተምረን ቃል ይህን ደግሞ እንናገራለን እንጂ የሰው ጥበብ በሚያስተምረን ቃል አይደለም።
12我們所領受的,不是這世界的靈,而是從 神來的靈,使我們能知道 神開恩賜給我們的事。
14ለፍጥረታዊ ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና አይቀበለውም፤ በመንፈስም የሚመረመር ስለ ሆነ ሊያውቀው አይችልም።
13我們也講這些事,不是用人的智慧所教的言語,而是用聖靈所教的言語,向屬靈的人解釋屬靈的事(“向屬靈的人解釋屬靈的事”或譯:“用屬靈的話解釋屬靈的事”)。
15መንፈሳዊ ሰው ግን ሁሉን ይመረምራል ራሱ ግን በማንም አይመረመርም።
14然而屬血氣的人不接受 神的靈的事,因為他以為是愚笨的;而且他也不能夠明白,因為這些事,要有屬靈的眼光才能領悟。
16እንዲያስተምረው የጌታን ልብ ማን አውቆት ነው? እኛ ግን የክርስቶስ ልብ አለን።
15屬靈的人能看透萬事,卻沒有人能看透他,
16如經上所記:“誰曾知道主的心意,能夠指教他呢?”但我們已經得著基督的心意了。