Amharic: New Testament

聖經新譯本

1 Peter

5

1እንግዲህ እኔ፥ ከእነርሱ ጋር ሽማግሌ የክርስቶስም መከራ ምስክር ደግሞም ሊገለጥ ካለው ክብር ተካፋይ የሆንሁ፥ በመካከላቸው ያሉትን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ፤
1務要牧養 神的羊群我這同作長老,也是為基督受苦作見證,又是同享將來所要顯現的榮耀的,勸你們當中作長老的:
2በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ ሳይሆን፥ በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘት ሳይሆን ጐብኙት፤
2務要牧養你們中間的羊群,按著 神的旨意照顧他們。不是出於勉強,而是出於甘心;不是因為貪財,而是出於熱誠;
3ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማኅበሮቻችሁን በኃይል አትግዙ፤
3也不是要轄制託付你們的羊群,而是作他們的榜樣。
4የእረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማያልፈውን የክብርን አክሊል ትቀበላላችሁ።
4到了牧長顯現的時候,你們必定得著那永不衰殘的榮耀冠冕。
5እንዲሁም፥ ጐበዞች ሆይ፥ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ፥ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።
5照樣,你們青年人要順服年長的。就是你們各人也要彼此以謙卑為裝束,因為“ 神敵擋驕傲的人,賜恩給謙卑的人。”
6እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ፤
6所以你們要謙卑,服在 神大能的手下,到了時候,他必叫你們升高。
7እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።
7你們要把一切憂慮卸給 神,因為他顧念你們。
8በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤
8你們要謹守、警醒。你們的仇敵魔鬼,好像吼叫的獅子走來走去,尋找可以吞吃的人;
9በዓለም ያሉት ወንድሞቻችሁ ያን መከራ በሙሉ እንዲቀበሉ እያወቃችሁ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት።
9你們要用堅強的信心抵擋他,因為知道你們在世上的弟兄,也經歷過同樣的苦難。
10በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ ለጥቂት ጊዜ መከራን ከተቀበላችሁ በኋላ ራሱ ፍጹማን ያደርጋችኋል ያጸናችሁምል ያበረታችሁማል።
10但滿有恩典的 神,就是在基督裡召你們進入他永遠榮耀的那一位,在你們受了短暫的苦難之後,必定親自成全你們,堅固你們,賜力量給你們,建立你們。
11ለእርሱ ክብርና ኃይል እስከዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን።
11願權能歸給他,直到永遠。阿們。
12እየመከርኋችሁና የምትቆሙባት ጸጋ እውነትኛ የእግዚአብሔር ጸጋ እንድትሆን እየመሰከርሁላችሁ፥ የታመነ ወንድም እንደ ሆነ በቈጠርሁት በስልዋኖስ እጅ በአጭሩ ጽፌላችኋለሁ።
12勸勉和祝福我藉著我認為忠心的弟兄西拉,簡略地寫了這封信勸勉你們,又向你們證實這是 神真正的恩典;你們要在這恩典上站立得住。
13ከእናንተ ጋር ተመርጣ በባቢሎን ያለች ቤተ ክርስቲያን ልጄም ማርቆስ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።
13在巴比倫與你們同蒙揀選的,和我兒子馬可都問候你們。
14በፍቅር አሳሳም እርስ በርሳችሁ ሰላምታ ተሰጣጡ። በክርስቶስ ላላችሁ ለሁላችሁ ሰላም ይሁን። አሜን።
14你們要用愛心彼此親嘴問安。願平安歸與你們所有在基督裡的人。