1በአንፊጶልና በአጶሎንያም ካለፉ በኋላ ወደ ተሰሎንቄ መጡ፥ በዚያም የአይሁድ ምኵራብ ነበረ።
1帖撒羅尼迦的騷動保羅和西拉經過暗非波里、亞波羅尼亞,來到帖撒羅尼迦,在那裡有猶太人的會堂。
2ጳውሎስም እንደ ልማዱ ወደ እነርሱ ገባ፥ ሦስት ሰንበትም ያህል ከእነርሱ ጋር ከመጻሕፍት እየጠቀሰ ይነጋገር ነበር፤
2保羅照他的習慣進去,一連三個安息日,根據聖經與他們辯論,
3ሲተረጉምም ክርስቶስ መከራ እንዲቀበልና ከሙታን እንዲነሣ ይገባው ዘንድ እያስረዳ። ይህ እኔ የምሰብክላችሁ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ነው ይል ነበር።
3講解證明基督必須受害,從死人中復活,說:“我所傳給你們的這位耶穌,就是基督。”
4ከእነርሱም አንዳንዶቹ ተረድተው ከሚያመልኩም ከግሪክ ሰዎች ብዙ ከከበሩትም ሴቶች ጥቂቶች ያይደሉ፥ ከጳውሎስና ከሲላስ ጋር ተባበሩ።
4他們中間有人給說服了,就附從了保羅和西拉;還有一大群虔誠的希臘人,和不少顯要的婦女。
5አይሁድ ግን ቀንተው ከሥራ ፈቶች ክፉ ሰዎችን አመጡ ሕዝብንም ሰብስበው ከተማውን አወኩ፥ ወደ ሕዝብም ያወጡአቸው ዘንድ ፈልገው ወደ ኢያሶን ቤት ቀረቡ፤
5但猶太人嫉妒起來,招聚了一些市井流氓,糾合成群,騷動全城,衝進了耶孫的家,搜索保羅和西拉,要把他們交給民眾。
6ባላገኙአቸውም ጊዜ ኢያሶንንና ከወንድሞች አንዳንዶችን ወደ ከተማው አለቆች ጎትተው። ዓለምን ያወኩ እነዚህ ወደዚህ ደግሞ መጥተዋል፥ ኢያሶንም ተቀብሎአቸዋል፤
6搜索不到他們,就把耶孫和幾個弟兄,拉到地方長官那裡,喊叫著說:“這些擾亂天下的人,也到這裡來了,
7እነዚህም ሁሉ። ኢየሱስ የሚሉት ሌላ ንጉሥ አለ እያሉ የቄሣርን ትእዛዝ ይቃወማሉ ብለው ጮኹ።
7耶孫卻收留他們。這些人都違背凱撒的法令,說另外還有一個王耶穌。”
8ሕዝቡና የከተማውም አለቆች ይህን ነገር በሰሙ ጊዜ ታወኩ፥
8群眾和地方長官聽見這話,就驚慌起來,
9ከኢያሶንና ከሌሎቹም ዋስ ተቀብለው ለቀቁአቸው።
9取得耶孫和其餘的人簽保後,才放了他們。
10ወዲያውም ወንድሞች ጳውሎስንና ሲላስን በሌሊት ወደ ቤርያ ሰደዱአቸው፥ በደረሱም ጊዜ ወደ አይሁድ ምኵራብ ገቡ፤
10來到比里亞弟兄們當夜立刻送保羅和西拉往比里亞去。二人到了,就進入猶太人的會堂。
11እነዚህም በተሰሎንቄ ከሚኖሩት ይልቅ ልበ ሰፊዎች ነበሩና። ነገሩ እንደዚሁ ይሆንን? ብለው ዕለት ዕለት መጻሕፍትን እየመረመሩ ቃሉን በሙሉ ፈቃድ ተቀበሉ።
11這裡的人,比帖撒羅尼迦人開明,熱切接受主的道,天天考查聖經,要知道所聽的是否與聖經相符。
12ስለዚህም ከእነርሱ ብዙ፥ ከግሪኮችም የከበሩት ሴቶችና ወንዶች ጥቂት ያይደሉ፥ አመኑ።
12結果他們中間有很多人信了,也有高貴的希臘婦女,男的也不少。
13በተሰሎንቄ ያሉት አይሁድ ግን ጳውሎስ በቤርያ ደግሞ የእግዚአብሔርን ቃል እንደ ሰበከ ባወቁ ጊዜ፥ ወደዚያው ደግሞ መጡና ሕዝቡን አወኩ።
13但帖撒羅尼迦的猶太人,知道保羅又在比里亞宣講 神的道,就到那裡去,煽動挑撥群眾。
14በዚያን ጊዜም ወንድሞቹ ወዲያው ጳውሎስን እስከ ባሕር ድረስ ይሄድ ዘንድ ሰደዱት፤ ሲላስና ጢሞቴዎስም በዚያው ቀሩ።
14弟兄們立刻把保羅送到海邊去;西拉和提摩太仍然留在比里亞。
15ጳውሎስን የሸኙት ግን እስከ አቴና አደረሱት፥ እንደሚቻላቸውም በፍጥነት ወደ እርሱ ይመጡ ዘንድ ወደ ሲላስና ወደ ጢሞቴዎስ ትእዛዝ ተቀብለው ሄዱ።
15護送保羅的人帶他到了雅典;保羅吩咐他們叫西拉和提摩太趕快去見他,於是他們就回去了。
16ጳውሎስም በአቴና ሲጠብቃቸው ሳለ፥ በከተማው ጣዖት መሙላቱን እየተመለከተ መንፈሱ ተበሳጨበት።
16在雅典保羅在雅典等候他們的時候,看見滿城都是偶像,心靈十分忿激。
17ስለዚህም በምኵራብ ከአይሁድና እግዚአብሔርን ከሚያመልኩ ሰዎች ጋር በየቀኑም በገበያ ከሚያገኛቸው ጋር ይነጋገር ነበር።
17於是在會堂裡,同猶太人和虔誠的人辯論;並且天天在市中心和所遇見的人辯論。
18ከኤፊቆሮስ ወገንና ኢስጦኢኮችም ከተባሉት ፈላስፎች አንዳንዶቹ ከእርሱ ጋር ተገናኙ። አንዳንዶቹም። ይህ ለፍላፊ ምን ሊናገር ይወዳል? አሉ፤ ሌሎችም የኢየሱስንና የትንሣኤውን ወንጌል ስለ ሰበከላቸው። አዲሶችን አማልክት የሚያወራ ይመስላል አሉ።
18還有伊壁鳩魯派和斯多亞派的哲學家也同他爭論,有的說:“這個拾人牙慧的人要說甚麼呢?”有的說:“他似乎是一個宣傳外地鬼神的人。”這是因為保羅傳揚耶穌和復活的道理。
19ይዘውም። ይህ የምትናገረው አዲስ ትምህርት ምን እንደሆነ እናውቅ ዘንድ ይቻለናልን? በጆሮአችን እንግዳ ነገር ታሰማናለህና፤ እንግዲህ ይህ ነገር ምን እንደሆነ እናውቅ ዘንድ እንፈቅዳለን ብለው አርዮስፋጎስ ወደ ተባለው ስፍራ ወሰዱት።
19他們拉著保羅,把他帶到亞略.巴古那裡,說:“你所講的這個新道理,我們可以知道嗎?
21የአቴና ሰዎች ሁሉና በዚያ የኖሩ እንግዶች አዲስ ነገርን ከመናገርና ከመስማት በቀር በሌላ ጉዳይ አይውሉም ነበርና።
20因為你把一切新奇的事,傳到我們耳中,我們願意知道這些事是甚麼意思。”
22ጳውሎስም በአርዮስፋጎስ መካከል ቆሞ እንዲህ አለ። የአቴና ሰዎች ሆይ፥ እናንተ በሁሉ ነገር አማልክትን እጅግ እንደምትፈሩ እመለከታለሁ።
21原來所有雅典人和外僑,專好談論和打聽新奇的事,來打發時間。
23የምታመልኩትን እየተመለከትሁ ሳልፍ። ለማይታወቅ አምላክ የሚል ጽሕፈት ያለበትን መሠዊያ ደግሞ አግኝቼአለሁና። እንግዲህ ይህን ሳታውቁ የምታመልኩትን እኔ እነግራችኋለሁ።
22保羅站在亞略.巴古當中,說:“各位雅典人,我看你們在各方面都非常敬畏鬼神。
24ዓለሙንና በእርሱ ያለውን ሁሉ የፈጠረ አምላክ እርሱ የሰማይና የምድር ጌታ ነውና እጅ በሠራው መቅደስ አይኖርም፤
23我走路的時候,仔細看你們所敬拜的,發現有一座壇,上面寫著‘獻給不認識的神’。我現在把你們不認識而敬拜的這位神,傳給你們。
25እርሱም ሕይወትንና እስትንፋስን ሁሉንም ለሁሉ ይሰጣልና አንዳች እንደሚጎድለው በሰው እጅ አይገለገልም።
24創造宇宙和其中萬有的 神,既然是天地的主,就不住在人手所造的殿宇,
26ምናልባትም እየመረመሩ ያገኙት እንደ ሆነ፥ እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩ የሰውን ወገኖች ሁሉ ከአንድ ፈጠረ፥ የተወሰኑትንም ዘመኖችና ለሚኖሩበት ስፍራ ዳርቻ መደበላቸው። ቢሆንም ከእያንዳንዳችን የራቀ አይደለም።
25也不受人手的服事,好像他缺少甚麼;他自己反而把生命、氣息和一切,賜給萬人。
28ከእናንተ ከባለ ቅኔዎች አንዳንዶች ደግሞ። እኛ ደግሞ ዘመዶቹ ነንና ብለው እንደ ተናገሩ፥ በእርሱ ሕያዋን ነንና እንንቀሳቀሳለን እንኖርማለን።
26他從一個本源造出了萬族來,使他們住在整個大地上,並且定了他們的期限和居住的疆界,
29እንግዲህ የእግዚአብሔር ዘመዶች ከሆንን፥ አምላክ በሰው ብልሃትና አሳብ የተቀረጸውን ወርቅ ወይም ብር ወይም ድንጋይ እንዲመስል እናስብ ዘንድ አይገባንም።
27要他們尋求 神,或者可以摸索而找到他。其實他離我們各人不遠,
30እንግዲህ እግዚአብሔር ያለማወቅን ወራት አሳልፎ አሁን በየቦታቸው ንስሐ ይገቡ ዘንድ ሰውን ሁሉ ያዛል፤
28因著他我們可以生存、活動、存在,就如你們有些詩人說:‘原來我們也是他的子孫。’
31ቀን ቀጥሮአልና፥ በዚያም ቀን ባዘጋጀው ሰው እጅ በዓለሙ ላይ በጽድቅ ሊፈርድ አለው፤ ስለዚህም እርሱን ከሙታን በማስነሣቱ ሁሉን አረጋግጦአል።
29我們既然是 神的子孫,就不應該以為他的神性是好像人用手藝、心思所雕刻的金銀石頭一樣。
32የሙታንንም ትንሣኤ በሰሙ ጊዜ እኵሌቶቹ አፌዙበት፥ እኵሌቶቹ ግን። ስለዚህ ነገር ሁለተኛ እንሰማሃለን አሉት።
30過去那無知的時代, 神不加以追究;現在,他卻吩咐各處的人都要悔改,
33እንዲሁም ጳውሎስ ከመካከላቸው ወጣ።
31因為他已經定好了日子,要藉著他所立的人,按公義審判天下,並且使他從死人中復活,給萬人作一個可信的憑據。”
34አንዳንዶች ወንዶች ግን ተባብረው አመኑ፤ ከእነርሱ ደግሞ በአርዮስፋጎስ ያለው የፍርድ ቤት ፈራጅ ዲዮናስዮስ ደማሪስ የሚሉአትም አንዲት ሴት ሌሎችም ከእነርሱ ጋር ነበሩ።
32眾人一聽到死人復活的事,就譏笑他,但有的說:“我們要再聽聽你講這件事!”
34但有幾個人接近他,並且信了主,其中有亞略.巴古的議員丟尼修,一個名叫戴馬里的女子,還有其他的人。