1ሁከቱም ከቀረ በኋላ ጳውሎስ ደቀ መዛሙርቱን አስመጥቶ መከራቸው፥ ተሰናብቶአቸውም ወደ መቄዶንያ ይሄድ ዘንድ ወጣ።
1往馬其頓及希臘騷亂平息以後,保羅派人把門徒請了來,勸勉一番,就辭別起行,往馬其頓去。
2ያንም አገር እያለፈ በብዙ ቃል ከመከራቸው በኋላ ወደ ግሪክ አገር መጣ።
2他走遍那一帶地方,用許多話勸勉眾人,然後來到希臘。
3በዚያም ሦስት ወር ተቀምጦ ወደ ሶርያ በመርከብ ሊሄድ ባሰበ ጊዜ፥ አይሁድ ሴራ ስላደረጉበት በመቄዶንያ አልፎ ይመለስ ዘንድ ቆረጠ።
3他在那裡住了三個月,正要坐船往敘利亞去的時候,有些猶太人設計要害他,他就決意路經馬其頓回去。
4የሸኙትም የቤርያው ሱሲጳጥሮስ ከተሰሎንቄ ሰዎችም አርስጥሮኮስና ሲኮንዱስ የደርቤኑም ጋይዮስና ጢሞቴዎስ የእስያ ሰዎችም ቲኪቆስ ጥሮፊሞስም ነበሩ፤
4與他同行的有比里亞人畢羅斯的兒子所巴特,帖撒羅尼迦人亞里達古和西公都,特庇人該猶和提摩太,亞西亞人推基古和特羅非摩。
5እነዚህም ወደ ፊታችን አልፈው በጢሮአዳ ቆዩን።
5這些人先走,在特羅亞等候我們。
6እኛ ግን ከቂጣ በዓል ቀን በኋላ ከፊልጵስዩስ በመርከብ ተነሥተን በአምስት ቀን ወደ ጢሮአዳ ወደ እነርሱ ደረስንና በዚያ ሰባት ቀን ተቀመጥን።
6至於我們,過了除酵節才從腓立比開船,五天後到特羅亞他們那裡,逗留了七天。
7ከሳምንቱም በመጀመሪያ ቀን እንጀራ ለመቁረስ ተሰብስበን ሳለን፥ ጳውሎስ በነገው ሊሄድ ስላሰበ ከእነርሱ ጋር ይነጋገር ነበር፥ እስከ መንፈቀ ሌሊትም ነገሩን አስረዘመ።
7在特羅亞使猶推古復活禮拜日,我們聚會擘餅的時候,保羅對大家講道,他因第二天就要起行,就一直講到半夜。
8ተሰብስበንም በነበርንበት ሰገነት እጅግ መብራት ነበረ።
8我們聚會的那座樓上,有許多燈火。
9አውጤኪስ የሚሉትም አንድ ጎበዝ በመስኮት ተቀምጦ ታላቅ እንቅልፍ አንቀላፍቶ ነበር፤ ጳውሎስም ነገርን ባስረዘመ ጊዜ እንቅልፍ ከብዶት ከሦስተኛው ደርብ ወደ ታች ወደቀ፥ ሞቶም አነሡት።
9有一個少年人,名叫猶推古,坐在窗臺上,因為保羅講得很長,他很困倦,沉沉地睡著了,就從三樓跌下來;把他扶起來的時候,已經死了。
10ጳውሎስም ወርዶ በላዩ ወደቀ፥ አቅፎም። ነፍሱ አለችበትና አትንጫጩ አላቸው።
10保羅走下去,伏在他身上;把他抱住,說:“你們不要驚慌,他還活著。”
11ወጥቶም እንጀራ ቆርሶም በላ፤ ብዙ ጊዜም እስኪነጋ ድረስ ተነጋገረ እንዲህም ሄደ።
11隨即回到樓上,擘餅吃了,又講了很久,直到天亮才走。
12ብላቴናውንም ደኅና ሆኖ ወሰዱት እጅግም ተጽናኑ።
12他們把活著的孩子帶走,得到很大的安慰。
13እኛ ግን ጳውሎስን ከዚያ እንቀበለው ዘንድ ስላለን ወደ መርከብ ቀድመን ሄድንና ወደ አሶን ተነሣን፤ እርሱ በመሬት ይሄድ ዘንድ ስላሰበ እንደዚህ አዞ ነበርና።
13從特羅亞往米利都我們先上船,開往亞朔,照著保羅的安排,要在那邊接他,因為他自己要走陸路去。
14በአሶንም ባገኘን ጊዜ ተቀብለነው ወደ ሚጢሊኒ መጣን፤
14他在亞朔與我們會合,我們接他上船,去到米推利尼。
15በማግሥቱም ከዚያ በባሕር ተነሥተን በኪዩ ፊት ለፊት ደረስን፥ በነገውም ወደ ሳሞን ተሻገርን በትሮጊሊዮም አድረን በማግሥቱ ወደ ሚሊጢን መጣን።
15從那裡開船,第二天到了基阿對面,過了一天就在撒摩靠岸,再過一天到了米利都。
16ጳውሎስ በእስያ እጅግ እንዳይቀመጥ ኤፌሶንን ይተው ዘንድ ቆርጦ ነበርና ቢቻለውም በዓለ ኀምሳን በኢየሩሳሌም ይውል ዘንድ ይቸኩል ነበርና።
16原來保羅決定越過以弗所,免得在亞西亞耽擱時間,因為他希望能在五旬節趕到耶路撒冷。
17ከሚሊጢንም ወደ ኤፌሶን ልኮ የቤተክርስቲያንን ሽማግሌዎች አስጠራቸው፤
17保羅勸勉以弗所的長老他從米利都派人去以弗所,請教會的長老來。
18ወደ እርሱም በመጡ ጊዜ እንዲህ አላቸው። ወደ እስያ ከገባሁበት ከመጀመሪያ ቀን ጀምሮ፥ በትሕትና ሁሉና በእንባ ከአይሁድም ሴራ በደረሰብኝ ፈተና ለጌታ እየተገዛሁ ዘመኑን ሁሉ ከእናንተ ጋር እንዴት እንደ ኖርሁ እናንተው ታውቃላችሁ፤
18他們到了,保羅說:“你們知道,自從我到了亞西亞的第一天,我一直怎樣跟你們相處,怎樣服事主,
20ወደ እግዚአብሔር ዘንድ ንስሐንና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ማመንን ለአይሁድና ለግሪክ ሰዎች እየመሰከርሁ በጉባኤም በየቤታችሁም አወራሁላችሁና አስተማርኋችሁ እንጂ፥ ከሚጠቅማችሁ ነገር አንዳች ስንኳ አላስቀረሁባችሁም።
19凡事謙卑,常常流淚,忍受猶太人謀害的試煉。
22አሁንም፥ እነሆ፥ እኔ በመንፈስ ታስሬ ወደ ኢየሩሳሌም እሄዳለሁ፥ በዚያም የሚያገኘኝ ምን እንደ ሆነ አላውቅም፤
20你們也知道,我從來沒有留下一件有益的事,不在眾人面前或在家裡告訴你們,教導你們。
23ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ። እስራትና መከራ ይቆይሃል ብሎ በየከተማው ሁሉ ይመሰክርልኛል።
21我對猶太人和希臘人都作過見證,要他們悔改歸向 神,信靠我們的主耶穌。
24ነገር ግን ሩጫዬንና ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን አገልግሎት እርሱም የእግዚአብሔርን ጸጋ ወንጌልን መመስከር እፈጽም ዘንድ ነፍሴን በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር እቆጥራለሁ።
22現在,我的心靈受到催逼,要去耶路撒冷,我不知道在那裡會遭遇甚麼事,
25አሁንም፥ እነሆ፥ እኔ የእግዚአብሔርን መንግሥት እየሰበክሁ በመካከላችሁ የዞርሁ ሁላችሁ ከእንግዲህ ወዲህ ፊቴን እንዳትዩ አውቃለሁ።
23只知道在各城裡聖靈都向我指明,說有捆鎖和患難在等著我。
26ስለዚህ እኔ ከሰው ሁሉ ደም ንጹሕ እንደ ሆንሁ ዛሬ በዚች ቀን እመሰክርላችኋለሁ።
24但我並不珍惜自己的性命,只求跑完我的路程,完成我從主耶穌所領受的職分,為 神恩惠的福音作見證。
27የእግዚአብሔርን ምክር ሁሉ ነግሬአችኋለሁና፥ ምንም አላስቀረሁባችሁም።
25“我曾在你們那裡走遍各地,宣揚 神的國。現在,我知道你們眾人不會再見我的面了。
28በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።
26所以我今天向你們作證,我是清白的,與眾人的罪(“罪”原文作“血”)無關。
29ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ፥ ደቀ መዛሙርትንም ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሡ እኔ አውቃለሁ።
27因為 神的全部計劃,我已經毫無保留地傳給你們了。
31ስለዚህ ሦስት ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሠጽ እንዳላቋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ።
28聖靈既然立你們為全群的監督,牧養 神用自己的血所贖來的教會,你們就應當為自己謹慎,也為全群謹慎。
32አሁንም ለእግዚአብሔርና ያንጻችሁ ዘንድ በቅዱሳንም ሁሉ መካከል ርስትን ይሰጣችሁ ዘንድ ለሚችል ለጸጋው ቃል አደራ ሰጥቻችኋለሁ።
29我知道在我離開之後,必有兇暴的豺狼進入你們中間,不顧惜羊群。
33ከማንም ብር ወይም ወርቅ ወይም ልብስ አልተመኘሁም፤
30你們自己中間也必有人起來,講些歪曲悖謬的話,引誘門徒跟從他們。
34እነዚህ እጆቼ በሚያስፈልገኝ ነገር ለእኔና ከእኔ ጋር ላሉት እንዳገለገሉ እናንተ ታውቃላችሁ።
31所以你們應當警醒,記念我三年之久,晝夜不停地帶著眼淚勸戒你們各人。
35እንዲሁ እየደከማችሁ ድውዮችን ልትረዱና እርሱ ራሱ። ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው እንዳለ የጌታን የኢየሱስን ቃል ልታስቡ ይገባችሁ ዘንድ በሁሉ አሳየኋችሁ።
32現在我把你們交託給 神和他恩惠的道;這道能建立你們,也能在所有成聖的人中賜基業給你們。
36ይህንም ብሎ ተንበርክኮ ከሁላቸው ጋር ጸለየ።
33我從來沒有貪圖任何人的金銀或衣服。
37ሁሉም እጅግ አለቀሱ፥ ጳውሎስንም አንገቱን አቅፈው ይስሙት ነበር፤
34我這兩隻手,供應了我和同伴的需要,這是你們自己知道的。
38ይልቁንም። ከእንግዲህ ወዲህ ፊቴን አታዩም ስላላቸው ነገር እጅግ አዘኑ። እስከ መርከብም ድረስ ሸኙት።
35我凡事以身作則,你們必須照樣辛勞,扶助軟弱的人,並且記念主耶穌的話:‘施比受更為有福。’”
38他們最傷心的,是保羅說他們不會再見他的面那句話。最後他們送他上了船。