Amharic: New Testament

聖經新譯本

Acts

7

1ሊቀ ካህናቱም። ይህ ነገር እንዲህ ነውን? አለው፤
1司提反的申辯大祭司說:“真有這些事嗎?”
2እርሱም እንዲህ አለ። ወንድሞችና አባቶች ሆይ፥ ስሙ። የክብር አምላክ ለአባታችን ለአብርሃም በካራን ሳይቀመጥ ገና በሁለት ወንዝ መካከል ሳለ ታየና።
2司提反說:“各位父老兄弟請聽!我們的祖宗亞伯拉罕,在美索不達米亞,還沒有住在哈蘭的時候,榮耀的 神向他顯現,
3ከአገርህና ከዘመዶችህም ወጥተህ ወደማሳይህ ወደ ማንኛውም ምድር ና አለው።
3對他說:‘你要離開本地本族,到我指示你的地方去。’
4በዚያን ጊዜ ከከለዳውያን አገር ወጥቶ በካራን ተቀመጠ። ከዚያም አባቱ ከሞተ በኋላ እናንተ ዛሬ ወደምትኖሩባት ወደዚች አገር አወጣው።
4他就離開迦勒底人的地方,住在哈蘭。他父親死後, 神又叫他從那裡遷到你們現在所住的地方。
5በዚችም የእግር ጫማ ስንኳ የሚያህል ርስት አልሰጠውም፤ ነገር ግን ልጅ ሳይኖረው ለእርሱ ከእርሱም በኋላ ለዘሩ ርስት አድርጎ ይሰጠው ዘንድ ተስፋ ሰጠው።
5在這裡 神並沒有賜他產業,連立足之地也沒有。但 神應許把這地賜給他和他的後裔為業,雖然那時他還沒有兒子。
6እግዚአብሔርም ዘሩ በሌላ አገር መጻተኞች እንዲሆኑ አራት መቶ ዓመትም ባሪያዎች እንዲያደርጉአቸው እንዲያስጨንቁአቸውም እንዲህ ተናገረ፤
6 神就這樣說:‘你的後裔必在外地寄居,人要奴役、虐待他們四百年。’
7ደግሞም እግዚአብሔር። እንደ ባሪያዎች በሚገዙአቸው ሕዝብ ላይ እኔ እፈርድባቸዋለሁ፥ ከዚህም በኋላ ይወጣሉ በዚህም ስፍራ ያመልኩኛል አለ።
7 神又說:‘奴役他們的那個國家,我要親自懲罰。以後,他們要出來,在這地方事奉我。’
8የመገረዝንም ኪዳን ሰጠው፤ እንዲሁም ይስሐቅን ወለደ በስምንተኛውም ቀን ገረዘው ይስሐቅም ያዕቆብን ያዕቆብም አሥራ ሁለቱን የአባቶችን አለቆች።
8 神也賜他割禮為約。這樣,亞伯拉罕生了以撒,第八天就給他行了割禮。後來,以撒生雅各,雅各生了十二位祖先。
9የአባቶችም አለቆች በዮሴፍ ቀንተው ወደ ግብፅ ሸጡት፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበረ፥
9“祖先妒忌約瑟,把他賣到埃及去,然而 神與他同在,
10ከመከራውም ሁሉ አወጣው፥ በግብፅ ንጉሥ በፈርዖንም ፊት ሞገስንና ጥበብን ሰጠው፥ በግብፅና በቤቱ ሁሉ ላይም ቢትወደድ አድርጎ ሾመው።
10救他脫離一切苦難,使他在埃及王法老面前,有智慧、得恩寵。法老立他為首相,管理埃及和法老的全家。
11በግብፅና በከነዓንም አገር ሁሉ ራብና ብዙ ጭንቅ መጣ፥ አባቶቻችንም ምግብን አላገኙም።
11後來埃及和迦南全地遭遇饑荒、大災難,我們的祖先找不到糧食。
12ያዕቆብም በግብፅ እህል መኖሩን በሰማ ጊዜ በመጀመሪያ አባቶቻችንን ሰደዳቸው፤
12雅各聽見埃及有穀糧,就派我們的祖先去,這是第一次。
13በሁለተኛውም ዮሴፍ ለወንድሞቹ ታወቀ፥ የዮሴፍም ትውልድ በፈርዖን ዘንድ ተገለጠ።
13第二次的時候,約瑟就向哥哥們表露自己的身世,法老才知道約瑟的家世。
14ዮሴፍም አባቱን ያዕቆብንና ሰባ አምስት ነፍስ የነበረውን ቤተ ዘመድ ሁሉ ልኮ አስጠራ።
14約瑟就派人去把他父親雅各和全家七十五人都接來。
15ያዕቆብም ወደ ግብፅ ወረደ እርሱም ሞተ አባቶቻችንም፤
15於是雅各下了埃及。後來他和我們祖先都死了,
16ወደ ሴኬምም አፍልሰው አብርሃም ከሴኬም አባት ከኤሞር ልጆች በብር በገዛው መቃብር ቀበሩአቸው።
16運到示劍,埋葬在亞伯拉罕用銀子向哈抹子孫買來的墳地裡。
17እግዚአብሔርም ለአብርሃም የማለለት የተስፋው ዘመን ሲቀርብ፥ ዮሴፍን የማያውቀው ሌላ ንጉሥ በግብፅ ላይ እስኪነሣ ድረስ፥ ሕዝቡ እየተጨመሩ በግብፅ በዙ።
17“ 神給亞伯拉罕的應許快要實現的時候,以色列人在埃及人口繁盛增多;
19እርሱም ወገናችንን ተተንኵሎ ሕፃናትን በሕይወት እንዳይጠብቁ ወደ ውጭ ይጥሉ ዘንድ አድርጎ አባቶቻችንን አስጨነቀ።
18但是,到了另一位不認識約瑟的君王興起統治埃及的時候,
20በዚያን ጊዜ ሙሴ ተወለደ በእግዚአብሔርም ፊት ያማረ ነበር፤ በአባቱ ቤትም ሦስት ወር አደገ፤
19他就謀害我們的同胞,虐待我們的祖先,逼他們拋棄自己的嬰孩,不容嬰孩存活。
21በተጣለም ጊዜ የፈርዖን ልጅ አነሣችው ልጅም ይሆናት ዘንድ አሳደገችው።
20就在那時候,摩西出生了,他非常俊美,在父親的家中撫養了三個月。
22ሙሴም የግብፆችን ጥበብ ሁሉ ተማረ፥ በቃሉና በሥራውም የበረታ ሆነ።
21他被拋棄的時候,法老的女兒把他拾起來,當作兒子撫養。
23ነገር ግን አርባ ዓመት ሲሞላው ወንድሞቹን የእስራኤልን ልጆች ይጐበኝ ዘንድ በልቡ አሰበ።
22摩西學盡了埃及人的一切學問,說話行事都有能力。
24አንዱም ሲበደል አይቶ ረዳው፥ የግብፅን ሰውም መትቶ ለተገፋው ተበቀለ።
23“到了四十歲,他心中起了一個念頭,要去看望自己的同胞以色列人。
25ወንድሞቹም እግዚአብሔር በእጁ መዳንን እንዲሰጣቸው የሚያስተውሉ ይመስለው ነበር፥ እነርሱ ግን አላስተዋሉም።
24當他看見有一個人受欺負,就去護衛,為那受屈的抱不平,打死了那個埃及人。
26በማግሥቱም እርስ በርሳቸው ሲጣሉ አገኛቸው፥ ሊያስታርቃቸውም ወዶ። ሰዎች ሆይ፥ እናንተስ ወንድማማች ናችሁ፤ ስለ ምን እርስ በርሳችሁ ትበዳደላላችሁ? አላቸው።
25他以為同胞們都必知道 神要藉著他的手拯救他們,事實上他們卻不知道。
27ያም ባልንጀራውን የሚበድል ግን። አንተን በእኛ ላይ ሹምና ፈራጅ እንድትሆን የሾመህ ማን ነው?
26第二天,有人在打架,摩西就出面調解,說:‘你們是弟兄,為甚麼彼此欺負呢?’
28ወይስ ትናንትና የግብፁን ሰው እንደ ገደልኸው ልትገድለኝ ትወዳለህን? ብሎ ገፋው።
27那欺負人的把他推開,說:‘誰立了你作我們的領袖和審判官呢?
29ሙሴም ከዚህ ነገር የተነሣ ሸሽቶ በምድያም አገር መጻተኛ ሆኖ ኖረ፤ በዚያም ሁለት ልጆች ወለደ።
28難道你想殺我,像昨天殺那個埃及人一樣嗎?’
30አርባ ዓመትም ሲሞላ የጌታ መልአክ በሲና ተራራ ምድረ በዳ በቍጥቋጦ መካከል በእሳት ነበልባል ታየው።
29摩西因為這句話,就逃到米甸地寄居,在那裡生了兩個兒子。
31ሙሴም አይቶ ባየው ተደነቀ፤ ሊመለከትም ሲቀርብ የጌታ ቃል። እኔ የአባቶችህ አምላክ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ ነኝ ብሎ ወደ እርሱ መጣ። ሙሴም ተንቀጥቅጦ ሊመለከት አልደፈረም።
30“過了四十年,在西奈山的曠野,有一位使者,在荊棘中的火燄裡,向摩西顯現。
33ጌታም። የቆምህባት ስፍራ የተቀደሰች ምድር ናትና የእግርህን ጫማ አውልቅ።
31他見了這個異象,十分驚奇;他正上前察看的時候,就有主的聲音說:
34በግብፅ ያሉትን የሕዝቤን መከራ ፈጽሜ አይቼ መቃተታቸውንም ሰምቼ ላድናቸው ወረድሁ፤ አሁንም ና፥ ወደ ግብፅ እልክሃለሁ አለው።
32‘我是你祖宗的 神,就是亞伯拉罕、以撒、雅各的 神。’摩西戰戰兢兢,不敢觀看。
35ሹምና ፈራጅ እንድትሆን የሾመህ ማን ነው? ብለው የካዱትን፥ ይህን ሙሴን በቍጥቋጦው በታየው በመልአኩ እጅ እግዚአብሔር ሹምና ቤዛ አድርጎ ላከው።
33主對他說:‘把你腳上的鞋脫掉,因為你所站的地方是聖地。
36ይህ ሰው በግብፅ ምድርና በኤርትራ ባሕር በምድረ በዳም አርባ ዓመት ድንቅና ምልክት እያደረገ አወጣቸው።
34我的子民在埃及所受的痛苦,我實在看見了;他們的歎息我也聽見了,我下來是要救他們。你來,我要派你到埃及去。’
37ይህ ሰው ለእስራኤል ልጆች። እግዚአብሔር ከወንድሞቻችሁ እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣላችኋል፤ እርሱን ስሙት ያላቸው ሙሴ ነው።
35他們拒絕了這位摩西,說:‘誰立了你作領袖和審判官呢?’但 神藉著在荊棘中向他顯現的使者的手,派他作領袖和救贖者。
38ይህ ሰው በሲና ተራራ ከተናገረው መልአክና ከአባቶቻችን ጋር በምድረ በዳ በማኅበሩ ውስጥ የነበረው ነው፤ ይሰጠንም ዘንድ ሕይወት ያላቸውን ቃላት ተቀበለ፤
36這人領他們出來,並且在埃及地、紅海和曠野,行奇事神蹟四十年。
39ለእርሱም አባቶቻችን ሊታዘዙት አልወደዱም፤ ነገር ግን ገፉት በልባቸውም ወደ ግብፅ ተመለሱ፤
37以前那位對以色列人說‘ 神要從你們弟兄中間,給你們興起一位先知像我’的,就是這摩西。
40አሮንንም። በፊታችን የሚሄዱ አማልክት ሥራልን፤ ይህ ከግብፅ ምድር ያወጣን ሙሴ ምን እንደ ሆነ አናውቅምና አሉት።
38那曾經在曠野的大會中,和那在西奈山上對他說話的使者同在,也與我們的祖先同在的,就是他。他領受了活的聖言,傳給我們。
41በዚያም ወራት ጥጃ አደረጉ ለጣዖቱም መሥዋዕት አቀረቡ፥ በእጃቸውም ሥራ ደስ አላቸው።
39我們的祖先不肯聽從他,反而把他推開,他們的心已經轉向了埃及,
42እግዚአብሔር ግን ዘወር አለ የሰማይንም ጭፍራ ያመልኩ ዘንድ አሳልፎ ሰጣቸው፥ በነቢያትም መጽሐፍ። እናንተ የእስራኤል ቤት፥ አርባ ዓመት በምድረ በዳ የታረደውን ከብትና መሥዋዕትን አቀረባችሁልኝን?
40就對亞倫說:‘給我們做一些神像,可以走在我們前頭。因為把我們從埃及地領出來的那個摩西,我們不知道他遭遇了甚麼事。’
43ትሰግዱላቸውም ዘንድ የሠራችኋቸውን ምስሎች እነርሱንም የሞሎክን ድንኳንና ሬምፉም የሚሉትን የአምላካችሁን ኮከብ አነሣችሁ፤ እኔም ከባቢሎን ወዲያ እሰዳችኋለሁ ተብሎ እንዲህ ተጽፎአል።
41在那些日子裡,他們做了一個牛犢,把祭物獻給那偶像,並且因自己手所做的而歡樂。
44እንዳየው ምስል አድርጎ ይሠራት ዘንድ ሙሴን ተናግሮ እንዳዘዘው፥ የምስክር ድንኳን ከአባቶቻችን ዘንድ በምድረ በዳ ነበረች፤
42於是 神轉身離開,任憑他們事奉天象,正如先知書所說:‘以色列家啊,你們在曠野四十年,豈是將祭牲和祭物獻給我呢?
45አባቶቻችንም ደግሞ በተራ ተቀብለው እግዚአብሔር በፊታቸው ያወጣቸውን የአሕዛብን አገር በያዙት ጊዜ ከኢያሱ ጋር አገቡአት፥ እስከ ዳዊት ዘመንም ድረስ ኖረች።
43你們抬著摩洛的帳幕,和理番神的星,就是你們做來敬拜的像。所以我要把你們放逐到巴比倫那一邊去。’
46እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ አግኝቶ ለያዕቆብ አምላክ ማደሪያን ያገኝ ዘንድ ለመነ።
44“我們的祖先在曠野有作證的帳幕,就是跟摩西談話的那位指示他,依照他看見的樣式做的。
47ነገር ግን ሰሎሞን ቤት ሠራለት።
45我們的祖先相繼承受了這帳幕, 神把外族人從他們面前趕走以後,他們就同約書亞把帳幕帶進所得為業的地方,直到大衛的日子。
48ነገር ግን ነቢዩ። ሰማይ ዙፋኔ ነው ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ ለእኔ ምን ዓይነት ቤት ትሠራላችሁ? ይላል ጌታ፥ ወይስ የማርፍበት ስፍራ ምንድር ነው? ይህንስ ሁሉ እጄ የሠራችው አይደለምን? እንዳለ፥ ልዑል የሰው እጅ በሠራችው አይኖርም።
46大衛在 神面前蒙了恩,就求為雅各的 神找個居所,
51እናንተ አንገተ ደንዳኖች ልባችሁና ጆሮአችሁም ያልተገረዘ፥ እናንተ ሁልጊዜ መንፈስ ቅዱስን ትቃወማላችሁ፤ አባቶቻችሁ እንደ ተቃወሙት እናንተ ደግሞ።
47而由所羅門為他建造殿宇。
52ከነቢያትስ አባቶቻችሁ ያላሳደዱት ማን ነው? የጻድቁንም መምጣት አስቀድሞ የተናገሩትን ገደሉአቸው፤ በመላእክት ሥርዓት ሕግን ተቀብላችሁ ያልጠበቃችሁት እናንተም አሁን እርሱን አሳልፋችሁ ሰጣችሁት ገደላችሁትም።
48其實至高者並不住人手所造的,正如先知說:
54ይህንም በሰሙ ጊዜ በልባቸው በጣም ተቈጡ ጥርሳቸውንም አፋጩበት።
49‘主說:天是我的寶座,地是我的腳凳,你們要為我建造怎樣的殿呢?哪裡是我安息的地方呢?
55መንፈስ ቅዱስንም ተሞልቶ ወደ ሰማይ ትኵር ብሎ ሲመለከት የእግዚአብሔርን ክብር ኢየሱስንም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አየና።
50這一切不都是我手所造的嗎?’
56እነሆ፥ ሰማያት ተከፍተው የሰው ልጅም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አያለሁ አለ።
51“你們頸項剛硬、心和耳都未受割禮的人哪!你們時常抗拒聖靈,你們的祖先怎樣,你們也怎樣。
57በታላቅ ድምፅም እየጮኹ ጆሮአቸውን ደፈኑ፥ በአንድ ልብ ሆነውም ወደ እርሱ ሮጡ፥
52有哪一個先知,你們的祖先不迫害呢?你們殺了那些預先宣告那義者要來的人,現在又把那義者出賣了,殺害了。
58ከከተማም ወደ ውጭ አውጥተው ወገሩት። ምስክሮችም ልብሳቸውን ሳውል በሚሉት በአንድ ጎበዝ እግር አጠገብ አኖሩ።
53你們領受了由天使傳達的律法,卻不遵守。”
59እስጢፋኖስም። ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ነፍሴን ተቀበል ብሎ ሲጠራ ይወግሩት ነበር።
54司提反被石頭打死眾人聽了這些話,心中非常惱怒,就向著司提反咬牙切齒。
60ተንበርክኮም። ጌታ ሆይ፥ ይህን ኃጢአት አትቍጠርባቸው ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህንም ብሎ አንቀላፋ። ሳውልም በእርሱ መገደል ተስማምቶ ነበር።
55但司提反被聖靈充滿,定睛望著天,看見 神的榮耀,並且看見耶穌站在 神的右邊,
56就說:“看哪!我看見天開了,人子站在 神的右邊。”
57眾人大聲喊叫,掩著耳朵,一齊向他衝過去,
58把他推出城外,用石頭打他。那些證人把自己的衣服,放在一個名叫掃羅的青年人腳前。
59他們用石頭打司提反的時候,他呼求說:“主耶穌啊,求你接收我的靈魂!”
60然後跪下來大聲喊著說:“主啊,不要把這罪歸給他們!”說了這話,就睡了。