Amharic: New Testament

聖經新譯本

John

10

1እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ወደ በጎች በረት በበሩ የማይገባ በሌላ መንገድ ግን የሚወጣ እርሱ ሌባ ወንበዴም ነው፤
1耶穌是好牧人“我實實在在告訴你們,那不從門進羊圈,倒從別處爬進去的,那人就是賊,就是強盜;
2በበሩ የሚገባ ግን የበጎች እረኛ ነው።
2那從門進去的,才是羊的牧人。
3ለእርሱ በረኛው ይከፍትለታል፤ በጎቹም ድምፁን ይሰሙታል፥ የራሱንም በጎች በየስማቸው ጠርቶ ይወስዳቸዋል።
3看門的給他開門,羊也聽他的聲音;他按著名字呼叫自己的羊,領牠們出來。
4የራሱንም ሁሉ ካወጣቸው በኋላ በፊታቸው ይሄዳል፥ በጎቹም ድምፁን ያውቃሉና ይከተሉታል፤
4他把自己的羊領出來以後,就走在前頭,羊也跟隨他,因為認得他的聲音。
5ከሌላው ግን ይሸሻሉ እንጂ አይከተሉትም፥ የሌሎችን ድምፅ አያውቁምና።
5牠們決不會跟隨陌生人,反而逃避他,因為不認得陌生人的聲音。”
6ኢየሱስ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፤ እነርሱ ግን የነገራቸው ምን እንደ ሆነ አላስተዋሉም።
6耶穌對他們說了這個譬喻,他們卻不明白他所說的是甚麼。
7ኢየሱስም ደግሞ አላቸው። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ እኔ የበጎች በር ነኝ።
7於是耶穌又說:“我實實在在告訴你們,我就是羊的門。
8ከእኔ በፊት የመጡ ሁሉ ሌቦችና ወንበዴዎች ናቸው፤ ዳሩ ግን በጎቹ አልሰሙአቸውም።
8所有在我以先來的,都是賊和強盜;羊卻不聽從他們。
9በሩ እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል፥ ይገባልም ይወጣልም መሰማሪያም ያገኛል።
9我就是門,如果有人藉著我進來,就必定得救,並且可以出、可以入,也可以找到草場。
10ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ።
10賊來了,不過是要偷竊、殺害、毀壞;我來了,是要使羊得生命,並且得的更豐盛。
11መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል።
11我是好牧人,好牧人為羊捨命。
12እረኛ ያልሆነው በጎቹም የእርሱ ያልሆኑ ሞያተኛ ግን ተኵላ ሲመጣ ባየ ጊዜ በጎቹን ትቶ ይሸሻል፤ ተኵላም ይነጥቃቸዋል በጎቹንም ይበትናቸዋል።
12那作雇工不是牧人的,羊也不是自己的,他一見狼來,就把羊撇下逃跑,狼就抓住羊群,把他們驅散了;
13ሞያተኛ ስለ ሆነ ለበጎቹም ስለማይገደው ሞያተኛው ይሸሻል።
13因為他是個雇工,對羊群漠不關心。
14መልካም እረኛ እኔ ነኝ፥ አብም እንደሚያውቀኝ እኔም አብን እንደማውቀው የራሴን በጎች አውቃለሁ የራሴም በጎች ያውቁኛል፤ ነፍሴንም ስለ በጎች አኖራለሁ።
14我是好牧人,我認識我的羊,我的羊也認識我,
16ከዚህም በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱን ደግሞ ላመጣ ይገባኛል ድምፄንም ይሰማሉ፥ አንድም መንጋ ይሆናሉ እረኛውም አንድ።
15好像父認識我,我也認識父一樣;並且我為羊捨命。
17ነፍሴን ደግሞ አነሣት ዘንድ አኖራለሁና ስለዚህ አብ ይወደኛል።
16我還有別的羊,不在這羊圈裡;我必須把牠們領來,牠們也要聽我的聲音,並且要合成一群,歸於一個牧人。
18እኔ በፈቃዴ አኖራታለሁ እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም። ላኖራት ሥልጣን አለኝ ደግሞም ላነሣት ሥልጣን አለኝ ይህችን ትእዛዝ ከአባቴ ተቀበልሁ።
17父愛我,因為我把生命捨去,好再把它取回來。
19እንግዲህ ከዚህ ቃል የተነሣ በአይሁድ መካከል እንደ ገና መለያየት ሆነ።
18沒有人能奪去我的生命,是我自己捨去的。我有權把生命捨去,也有權把它取回來;這是我從我的父所領受的命令。”
20ከእነርሱም ብዙዎች። ጋኔን አለበት አብዶአልም፤ ስለ ምንስ ትሰሙታላችሁ? አሉ።
19猶太人因著這些話又起了紛爭。
21ሌሎችም። ይህ ጋኔን ያለበት ሰው ቃል አይደለም፤ ጋኔን የዕውሮችን ዓይኖች ሊከፍት ይችላልን? አሉ።
20他們當中有許多人說:“他是鬼附的,他發瘋了;為甚麼要聽他呢?”
22በኢየሩሳሌምም የመቅደስ መታደስ በዓል ሆነ፤
21另外有人說:“這話不是鬼附的人所說的。鬼怎能使瞎子的眼睛開了呢?”
23ክረምትም ነበረ። ኢየሱስም በመቅደስ በሰሎሞን ደጅ መመላለሻ ይመላለስ ነበር።
22猶太人棄絕耶穌在耶路撒冷,獻殿節到了,那時是冬天。
24አይሁድም እርሱን ከበው። እስከ መቼ ድረስ በጥርጣሪ ታቆየናለህ? አንተ ክርስቶስ እንደ ሆንህ ገልጠህ ንገረን አሉት።
23耶穌在殿的所羅門廊上走過,
25ኢየሱስም መለሰላቸው፥ እንዲህ ሲል። ነገርኋችሁ አታምኑምም እኔ በአባቴ ስም የማደርገው ሥራ ይህ ስለ እኔ ይመሰክራል፤
24猶太人圍著他,對他說:“你使我們心裡懸疑不定,要到幾時呢?如果你是基督,就公開地告訴我們吧!”
26እናንተ ግን እንደ ነገርኋችሁ ከበጎቼ ስላልሆናችሁ አታምኑም።
25耶穌對他們說:“我已經告訴你們,你們卻不相信;我奉我父的名所作的事,可以為我作證。
27በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ እኔም አውቃቸዋለሁ ይከተሉኝማል፤
26只是你們不信,因為你們不是我的羊。
28እኔም የዘላለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ፥ ለዘላለምም አይጠፉም፥ ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም።
27我的羊聽我的聲音,我也認識他們,他們也跟隨我。
29የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ ይበልጣል፥ ከአባቴም እጅ ሊነጥቃቸው ማንም አይችልም።
28我賜給他們永生,他們永不滅亡,誰也不能把他們從我手裡奪去。
30እኔና አብ አንድ ነን።
29那位把羊群賜給我的父比一切都大,也沒有人能把他們從我父的手裡奪去。
31አይሁድ ሊወግሩት ደግመው ድንጋይ አነሡ።
30我與父原為一。”
32ኢየሱስ። ከአባቴ ብዙ መልካም ሥራ አሳየኋችሁ፤ ከእነርሱ ስለ ማናቸው ሥራ ትወግሩኛላችሁ? ብሎ መለሰላቸው።
31猶太人又拿起石頭要打他。
33አይሁድም። ስለ መልካም ሥራ አንወግርህም፤ ስለ ስድብ፤ አንተም ሰው ስትሆን ራስህን አምላክ ስለ ማድረግህ ነው እንጂ ብለው መለሱለት።
32耶穌對他們說:“我把許多從父那裡來的善事顯給你們看,你們因哪一件要用石頭打我呢?”
34ኢየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው። እኔ። አማልክት ናችሁ አልሁ ተብሎ በሕጋችሁ የተጻፈ አይደለምን?
33猶太人對他說:“我們不是因為善事用石頭打你,而是因為你說了僭妄的話;又因為你是個人,竟然把自己當作 神。”
35መጽሐፉ ሊሻር አይቻልምና እነዚያን የእግዚአብሔር ቃል የመጣላቸውን አማልክት ካላቸው፥
34耶穌說:“你們的律法上不是寫著‘我說你們是神’嗎?
36የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ስላልሁ እናንተ አብ የቀደሰውን ወደ ዓለምም የላከውን። ትሳደባለህ ትሉታላችሁን?
35聖經是不能廢除的,如果那些承受 神的道的人, 神尚且稱他們是神,
37እኔ የአባቴን ሥራ ባላደርግ አትመኑኝ፤
36那麼父所分別為聖又差到世上來的,他自稱是 神的兒子,你們就說他說了僭妄 神的話嗎?
38ባደርገው ግን፥ እኔን ስንኳ ባታምኑ አብ በእኔ እንደ ሆነ እኔም በአብ እንደ ሆንሁ ታውቁና ታስተውሉ ዘንድ ሥራውን እመኑ።
37我若不作我父的事,你們就不必信我;
39እንግዲህ ደግመው ሊይዙት ፈለጉ፤ ከእጃቸውም ወጣ።
38我若作了,你們縱然不信我,也應當信這些事,好使你們確實知道,我父是在我裡面,我也在父裡面。”
40ዮሐንስም በመጀመሪያ ያጠምቅበት ወደ ነበረው ስፍራ ወደ ዮርዳኖስ ማዶ እንደ ገና ሄደ በዚያም ኖረ።
39他們又要逮捕耶穌,他卻從他們的手中逃脫了。
41ብዙ ሰዎችም ወደ እርሱ መጥተው። ዮሐንስ አንድ ምልክት ስንኳ አላደረገም፥ ነገር ግን ዮሐንስ ስለዚህ ሰው የተናገረው ሁሉ እውነት ነበረ አሉ።
40耶穌又往約旦河東去,到約翰從前施洗的地方,住在那裡。
42በዚያም ብዙዎች በእርሱ አመኑ።
41許多人到他那裡去,說:“約翰沒有行過一件神蹟,但約翰指著這人所說的一切話,都是真實的。”
42在那裡就有許多人信了耶穌。