1የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ የያዕቆብም ወንድም የሆነ ይሁዳ፥ በእግዚአብሔር አብ ተወደው ለኢየሱስ ክርስቶስም ተጠብቀው ለተጠሩ፤
1問安耶穌基督的僕人,雅各的兄弟猶大,寫信給那些被召的人,就是在父 神裡蒙愛,並且為了耶穌基督而蒙保守的人。
2ምሕረትና ሰላም ፍቅርም ይብዛላችሁ።
2願憐憫、平安、慈愛多多加給你們。
3ወዳጆች ሆይ፥ ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ፥ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።
3要竭力維護信仰親愛的,我曾經迫切地想寫信給你們,論到我們共享的救恩;現在我更覺得必須寫信勸勉你們,要竭力維護從前一次就全交給了聖徒的信仰,
4ከብዙ ጊዜ በፊት ለዚህ ፍርድ የተጻፉ አንዳንዶች ሰዎች ሾልከው ገብተዋልና፤ ኃጢአተኞች ሆነው የአምላካችንን ጸጋ በሴሰኝነት ይለውጣሉ ንጉሣችንንና ጌታችንንም ብቻውን ያለውን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ።
4因為有人已經混進你們中間,他們就是早被判定受刑的不敬虔的人。這些人把我們 神的恩典當作放縱情慾的藉口,並且否認獨一的主宰我們的主耶穌基督。
5ዳሩ ግን ሁሉን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ምንም የተማራችሁ ብትሆኑ ጌታ ከግብፅ አገር ሕዝቡን አድኖ የማያምኑትን በኋላ እንዳጠፋቸው ላሳስባችሁ እወዳለሁ።
5列舉史實作鑒戒雖然這一切事情你們都早已知道,我仍然要提醒你們:從前主從埃及地把人民救出來,跟著就把那些不信的人除滅了。
6መኖሪያቸውንም የተዉትን እንጂ የራሳቸውን አለቅነት ያልጠበቁትን መላእክት በዘላለም እስራት ከጨለማ በታች እስከ ታላቁ ቀን ፍርድ ድረስ ጠብቆአቸዋል።
6還有,那不守本位擅離自己居所的天使,主用永遠的鎖鍊把他們拘留在黑暗裡,直到那大日子的審判。
7እንዲሁም እንደ እነርሱ ዝሙትን ያደረጉና ሌላን ሥጋ የተከተሉ ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸውም የነበሩ ከተማዎች በዘላለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ሆነዋል።
7又像所多瑪、蛾摩拉和周圍城市的人,與他們一樣的淫亂,隨從反常的情慾,以致遭受永火的刑罰,成了後世的鑒戒。
8እንዲሁም እነዚህ ሰዎች ደግሞ እያለሙ ሥጋቸውን ያረክሳሉ ጌትነትንም ይጥላሉ ሥልጣን ያላቸውንም ይሳደባሉ።
8雖然是這樣,這些醉生夢死的人還是照樣玷污身體,藐視主權,毀謗尊榮。
9የመላእክት አለቃ ሚካኤል ግን ከዲያብሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ ስለ ሙሴ ሥጋ ሲነጋገር። ጌታ ይገሥጽህ አለው እንጂ የስድብን ፍርድ ሊናገረው አልደፈረም።
9天使長米迦勒為了摩西的屍體與魔鬼爭論的時候,還不敢用毀謗的話定他的罪,只說:“主責備你!”
10እነዚህ ግን የማያውቁትን ሁሉ ይሳደባሉ፥ አእምሮም እንደሌላቸው እንስሶች በፍጥረታቸው በሚያውቁት ሁሉ በእርሱ ይጠፋሉ።
10但這些人毀謗他們所不知道的,他們只知道按本性所能領悟的事,好像沒有理性的禽獸,就因這些事敗壞了自己。
11ወዮላቸው፥ በቃየል መንገድ ሄደዋልና ስለ ደመወዝም ለበለዓም ስሕተት ራሳቸውን አሳልፈው ሰጥተዋል በቆሬም መቃወም ጠፍተዋል።
11他們有禍了,因為他們走上了該隱的道路,又為了財利闖進巴蘭的歧途,並且在可拉的背叛中滅亡了。
12እነዚህ ከእናንተ ጋር ሲጋበዙ በፍቅር ግብዣችሁ እንደ እድፍ ናቸው፤ እንደ እረኞች ያለ ፍርሃት ራሳቸውን ይጠብቃሉ፤ በነፋስ የተወሰዱ ውኃ የሌለባቸው ደመናዎች፥ ፍሬ የማያፈሩ ሁለት ጊዜ የሞቱ ከነሥራቸው የተነቀሉ በበጋ የደረቁ ዛፎች፥
12這些人膽敢與你們同席,他們只顧餵飽自己,是你們愛筵中的暗礁;是無雨的浮雲,隨風飄蕩;是秋天不結果子的樹,連根拔起,死而又死;
13የገዛ ነውራቸውን አረፋ እየደፈቁ ጨካኝ የባሕር ማዕበል፥ ድቅድቅ ጨለማ ለዘላለም የተጠበቀላቸው የሚንከራተቱ ከዋክብት ናቸው።
13是海中的狂浪,濺起了自己可恥的泡沫;是流蕩的星,有漆黑的幽暗永遠為他們存留。
14ከአዳም ጀምሮ ሰባተኛ የሆነ ሄኖክ። እነሆ፥ ጌታ በሁሉ ላይ እንዲፈርድ፥ በኃጢአተኝነትም ስላደረጉት ስለ ኃጢአተኛ ሥራቸው ሁሉ ዓመፀኞችም ኃጢአተኞች በእርሱ ላይ ስለ ተናገሩ ስለ ጭከና ነገር ሁሉ ኃጢአተኞችን ሁሉ እንዲወቅስ ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋር መጥቶአል ብሎ ለእነዚህ ደግሞ ትንቢት ተናገረ።
14亞當的第七世孫以諾,也曾經預言這些人說:“看,主必同他的千萬聖者降臨,
16እነዚህ እንደ ምኞታቸው እየሄዱ የሚያንጎራጉሩና ስለ ዕድላቸው የሚያጕረመርሙ ናቸው፥ እንዲረባቸውም ለሰው ፊት እያደሉ አፋቸው ከመጠን ይልቅ ታላቅ ቃል ይናገራል።
15要審判眾人,又要定所有不敬虔的人的罪,因為他們妄行各樣不敬虔的事,並且說了種種剛愎的話頂撞 神。”
17እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት ቀድሞ የተነገረውን ቃል አስቡ፤
16這些人常發牢騷,怨天尤人,順著自己的私慾行事,口說誇張的話,為了利益就不惜阿諛奉承。
18እነርሱ። በመጨረሻው ዘመን በኃጢአተኝነት እንደ ገዛ ምኞታቸው እየሄዱ ዘባቾች ይሆናሉ ብለዋችኋልና።
17要在至聖的信仰上建立自己但你們呢,親愛的,你們要記住我們主耶穌基督的使徒從前所說的話。
19እነዚህ የሚያለያዩ ሥጋውያንም የሆኑ መንፈስም የሌላቸው ሰዎች ናቸው።
18他們曾經對你們說:“末世必有好譏笑人的人,隨著自己不敬虔的私慾行事。”
20እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ ከሁሉ ይልቅ በተቀደሰ ሃይማኖታችሁ ራሳችሁን ለማነጽ እየተጋችሁ በመንፈስ ቅዱስም እየጸለያችሁ፥
19這些人分黨結派,是屬血氣的,沒有聖靈。
21ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሕረት ስትጠባበቁ በእግዚአብሔር ፍቅር ራሳችሁን ጠብቁ።
20但你們呢,親愛的,你們要在至聖的信仰上建立自己,在聖靈裡禱告,
22አንዳንዶች ተከራካሪዎችንም ውቀሱ፥ አንዳንዶችንም ከእሳት ነጥቃችሁ አድኑ፥
21要保守自己在 神的愛中,仰望我們主耶穌基督的憐憫,直到永生。
23አንዳንዶችንም በሥጋ የረከሰውን ልብስ እንኳ እየጠላችሁ በፍርሃት ማሩ።
22有些人心裡疑惑,你們要憐憫他們;
24ሳትሰናከሉም እንዲጠብቃችሁ፥ በክብሩም ፊት በደስታ ነውር የሌላችሁ አድርጎ እንዲያቆማችሁ ለሚችለው
23有些人你們要拯救,把他們從火中搶救出來;又有些人你們要戰戰兢兢地憐憫他們,連染上情慾污漬的衣服也應當憎惡。
25ብቻውን ለሆነ አምላክና መድኃኒታችን ከዘመን ሁሉ በፊት አሁንም እስከ ዘላለምም ድረስ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ግርማ ኃይልም ሥልጣንም ይሁን፤ አሜን።
24頌讚的禱告願榮耀、威嚴、能力、權柄,藉著我們的主耶穌基督,從萬世以前,及現在,直到永永遠遠,歸給獨一的 神我們的救主。他能保守你們不至跌倒,使你們毫無瑕疵,欣然站在他榮光之前。阿們。