1ኢየሱስም መንፈስ ቅዱስ መልቶበት ከዮርዳኖስ ተመለሰ፥ በመንፈስም ወደ ምድረ በዳ ተመርቶ፥
1耶穌受試探(太4:1~11;可1:12~13)耶穌被聖靈充滿,從約旦河回來,聖靈引他到曠野,四十天受魔鬼的試探。
2አርባ ቀን ከዲያብሎስ ተፈተነ። በነዚያም ቀኖች ምንም አልበላም፥ ከተጨረሱም በኋላ ተራበ።
2那些日子他甚麼也沒有吃,日子滿了他就餓了。
3ዲያብሎስም። የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፥ ይህን ድንጋይ። እንጀራ ሁን ብለህ እዘዝ አለው።
3魔鬼對他說:“你若是 神的兒子,就吩咐這塊石頭變成食物吧!”
4ኢየሱስም። ሰው በእግዚአብሔር ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል ብሎ መለሰለት።
4耶穌回答:“經上記著:‘人活著不是單靠食物。’”
5ዲያብሎስም ረጅም ወደ ሆነ ተራራ አውጥቶ የዓለምን መንግሥታት ሁሉ በቅጽበት አሳየው።
5魔鬼引他上到高處,霎時間把天下萬國指給他看,
6ዲያብሎስም። ይህ ሥልጣን ሁሉ ክብራቸውም ለእኔ ተሰጥቶአል ለምወደውም ለማንም እሰጠዋለሁና ለአንተ እሰጥሃለሁ፤
6對他說:“這一切權柄、榮華,我都可以給你;因為這些都交給了我,我願意給誰就給誰。
7ስለዚህ አንተ በእኔ ፊት ብትሰግድ፥ ሁሉ ለአንተ ይሆናል አለው።
7所以,只要你在我面前拜一拜,這一切就全是你的了。”
8ኢየሱስም መልሶ። ለጌታ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአል አለው።
8耶穌回答:“經上記著:‘當拜主你的 神,單要事奉他。’”
9ወደ ኢየሩሳሌም ደግሞ ወሰደው፤ በመቅደስም ጫፍ ላይ አቁሞ። ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝልሃል፥ እግርህንም በድንጋይ ከቶ እንዳትሰናከል በእጃቸው ያነሡሃል ተብሎ ተጽፎአልና የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ፥ ከዚህ ወደ ታች ራስህን ወርውር አለው።
9魔鬼又引他到耶路撒冷,叫他站在殿頂上,對他說:“你若是 神的兒子,就從這裡跳下去吧!
12ኢየሱስም መልሶ። ጌታን አምላክህን አትፈታተነው ተብሎአል አለው።
10因為經上記著:‘他為了你,會吩咐自己的使者保護你。’
13ዲያቢሎስም ፈተናውን ሁሉ ከጨረሰ በኋላ እስከ ጊዜው ከእርሱ ተለየ።
11又記著:‘用手托住你,免得你的腳碰到石頭。’”
14ኢየሱስም በመንፈስ ኃይል ወደ ገሊላ ተመለሰ፤ ስለ እርሱም በዙሪያው ባለችው አገር ሁሉ ዝና ወጣ።
12耶穌回答:“經上說:‘不可試探主你的 神。’”
15እርሱም በምኵራባቸው ያስተምር፥ ሁሉም ያመሰግኑት ነበር።
13魔鬼用盡了各種試探,就暫時離開了耶穌。
16ወዳደገበትም ወደ ናዝሬት መጣ፤ እንደ ልማዱም በሰንበት ቀን ወደ ምኵራብ ገባ፥ ሊያነብም ተነሣ።
14在加利利傳道(太4:12~17;可1:14~15)耶穌帶著聖靈的能力,回到加利利。他的名聲傳遍了周圍各地。
17የነቢዩንም የኢሳይያስን መጽሐፍ ሰጡት፥ መጽሐፉንም በተረተረ ጊዜ። የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና፤ ለታሰሩትም መፈታትን ለዕውሮችም ማየትን እሰብክ ዘንድ፥ የተጠቁትንም ነጻ አወጣ ዘንድ የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እሰብክ ዘንድ ልኮኛል ተብሎ የተጻፈበትን ስፍራ አገኘ።
15他在各會堂裡教導人,很受眾人的尊崇。
20መጽሐፉንም ጠቅልሎ ለአገልጋዩ ሰጠውና ተቀመጠ፤ በምኵራብም የነበሩት ሁሉ ትኵር ብለው ይመለከቱት ነበር።
16在本鄉遭人厭棄(太13:53~58;可6:1~6)耶穌來到拿撒勒自己長大的地方,照著習慣在安息日進入會堂,站起來要讀經。
21እርሱም። ዛሬ ይህ መጽሐፍ በጆሮአችሁ ተፈጸመ ይላቸው ጀመር።
17有人把以賽亞先知的書遞給他,他展開書卷找到一處,上面寫著:
22ሁሉም ይመሰክሩለት ነበር ከአፉም ከሚወጣው ከጸጋው ቃል የተነሣ እየተደነቁ። ይህ የዮሴፍ ልጅ አይደለምን? ይሉ ነበር።
18“主的靈在我身上,因為他膏我去傳福音給貧窮的人,差遣我去宣告被擄的得釋放,瞎眼的得看見,受壓制的得自由,
23እርሱም። ያለ ጥርጥር ይህን ምሳሌ። ባለ መድኃኒት ሆይ፥ ራስህን ፈውስ፤ በቅፍርናሆም እንዳደረግኸው የሰማነውን ሁሉ በዚህ በገዛ አገርህ ደግሞ አድርግ ትሉኛላችሁ አላቸው።
19又宣告主悅納人的禧年。”
24እንዲህም አለ። እውነት እላችኋለሁ፥ ነቢይ በገዛ አገሩ ከቶ አይወደድም።
20他把書卷捲好,交還侍役,就坐下。會堂裡眾人都注視他。
25ነገር ግን እውነት እላችኋለሁ፥ በኤልያስ ዘመን ሦስት ዓመት ከስድስት ወር ሰማይ ተዘግቶ ሳለ በምድር ሁሉ ብርቱ ራብ በነበረ ጊዜ፥ በእስራኤል ብዙ መበለቶች ነበሩ፤
21他就對他們說:“這段經文今天應驗在你們中間(“中間”原文作“耳中”)了。”
26ኤልያስም በሲዶና አገር ወዳለች ወደ ሰራፕታ ወደ አንዲት መበለት እንጂ ከእነርሱ ወደ አንዲቱ አልተላከም።
22眾人稱讚他,希奇他口中所出的恩言,並且說:“這不是約瑟的兒子嗎?”
27በነቢዩ በኤልሳዕ ዘመንም በእስራኤል ብዙ ለምጻሞች ነበሩ፥ ከሶርያዊው ከንዕማን በቀር ከእነርሱ አንድ ስንኳ አልነጻም።
23他說:“你們必向我說這俗語:‘醫生,治好你自己吧!’也必說:‘我們聽見你在迦百農所行的一切事,也該在你本鄉這裡行啊!’”
28በምኵራብም የነበሩ ሁሉ ይህን ሰምተው ቍጣ ሞላባቸው፥ ተነሥተውም ከከተማ ወደ ውጭ አወጡት፥
24他又說:“我實在告訴你們,沒有先知在他本鄉是受歡迎的。
29ይጥሉትም ዘንድ ከተማቸው ተሠርታባት ወደ ነበረች ወደ ተራራው አፋፍ ወሰዱት፤
25我對你們說實話,當以利亞的時候,三年六個月不下雨(“不下雨”原文作“天閉塞”),遍地大起饑荒,那時以色列中有許多寡婦,
30እርሱ ግን በመካከላቸው አልፎ ሄደ።
26以利亞沒有奉差遣往他們中間任何一個那裡去,只到西頓撒勒法的一個寡婦那裡。
31ወደ ገሊላ ከተማም ወደ ቅፍርናሆም ወረደ። በሰንበትም ያስተምራቸው ነበር፤
27以利沙先知的時候,以色列中有許多患痲風的人,其中除了敘利亞的乃縵,沒有一個得潔淨的。”
32ቃሉ በሥልጣን ነበርና በትምህርቱ ተገረሙ።
28會堂裡的眾人聽見這話,都怒氣填胸,
33በምኵራብም የርኵስ ጋኔን መንፈስ ያደረበት ሰው ነበረ፥ በታላቅ ድምፅም ጮኾ።
29起來趕他出城(這城原來建在山上),他們拉他到山崖,要把他推下去。
34ተው፥ የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ፥ ከአንተ ጋር ምን አለን? ልታጠፋን መጣህን? ማን እንደ ሆንህ አውቄሃለሁ፥ አንተ የእግዚአብሔር ቅዱሱ አለ።
30耶穌卻從他們中間走過,就離去了。
35ኢየሱስም። ዝም በል ከእርሱም ውጣ ብሎ ገሠጸው። ጋኔኑም በመካከላቸው ጥሎት ሳይጐዳው ከእርሱ ወጣ።
31在迦百農趕出污靈(可1:21~28)耶穌下到加利利的迦百農城,在安息日教導人。
36ሁሉንም መደነቅ ያዛቸው፥ እርስ በርሳቸውም። ይህ ቃል ምንድር ነው? በሥልጣንና በኃይል ርኵሳን መናፍስትን ያዝዛልና፥ ይወጡማል ብለው ተነጋገሩ።
32他們對他的教訓都很驚奇,因為他的話帶著權柄。
37ዝናም በዙሪያው ባለች አገር ወደ ስፍራው ሁሉ ስለ እርሱ ወጣ።
33會堂裡有一個被污鬼附著的人,大聲喊叫:
38በምኵራብም ተነሥቶ ወደ ስምዖን ቤት ገባ። የስምዖንም አማት በብርቱ ንዳድ ታማ ነበር ስለ እርስዋም ለመኑት።
34“哎!拿撒勒人耶穌,我們跟你有甚麼關係呢?你來毀滅我們嗎?我知道你是誰,你是 神的聖者。”
39በአጠገብዋም ቆሞ ንዳዱን ገሠጸውና ለቀቃት፤ ያንጊዜውንም ተነሥታ አገለገለቻቸው።
35耶穌斥責他說:“住口!從他身上出來!”鬼把那人摔倒在眾人中間,就從他身上出來了,沒有傷害他。
40ፀሐይም በገባ ጊዜ በልዩ ልዩ ደዌ የተያዙ በሽተኞችን ሁሉ ወደ እርሱ አመጡአቸው፤ እርሱም በእያንዳቸው ላይ እጁን ጭኖ ፈወሳቸው።
36眾人都驚駭,彼此談論說:“這是怎麼回事?他用權柄能力吩咐污靈,污靈竟出來了。”
41አጋንንትም ደግሞ። አንተ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ እያሉ እየጮኹም ከብዙዎች ይወጡ ነበር፤ ገሠጻቸውም ክርስቶስም እንደ ሆነ አውቀውት ነበርና እንዲናገሩ አልፈቀደላቸውም።
37耶穌的名聲,傳遍了周圍各地。
42በጸባም ጊዜ ወጥቶ ወደ ምድረ በዳ ሄደ፤ ሕዝቡም ይፈልጉት ነበር፤ ወደ እርሱም መጡ፥ ከእነርሱም ተለይቶ እንዳይሄድ ሊከለክሉት ወደዱ።
38治病趕鬼(太8:14~17;可1:29~34)他起身離開會堂,進入西門的家。西門的岳母正在發高熱,他們為她求耶穌。
43እርሱ ግን። ስለዚህ ተልኬአለሁና ለሌሎቹ ከተማዎች ደግሞ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል እሰብክ ዘንድ ይገባኛል አላቸው።
39耶穌站在她旁邊,斥責那熱病,熱就退了;她立刻起身服事他們。
44በገሊላም ምኵራቦች ይሰብክ ነበር።
40日落的時候,不論害甚麼病的人,都被帶到耶穌那裡;他一一為他們按手,醫好他們。
41又有鬼從好些人身上出來,喊著說:“你是 神的兒子。”耶穌斥責他們,不許他們說話,因為他們知道他是基督。
42往別的城傳道(可1:35~39)天一亮,耶穌出來,到曠野地方去。眾人尋找他,一直找到他那裡,要留住他,不要他離開他們。
43他卻說:“我也必須到別的城去傳 神國的福音,因為我是為了這緣故奉差遣的。”