Amharic: New Testament

聖經新譯本

Mark

11

1ወደ ኢየሩሳሌምም ከደብረ ዘይት አጠገብ ወዳሉቱ ወደ ቤተ ፋጌና ወደ ቢታንያ በቀረቡ ጊዜ፥ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን ልኮ።
1騎驢進耶路撒冷(太21:1~9;路19:28~38;約12:12~15)他們走近耶路撒冷,到了伯法其和伯大尼,來到橄欖山那裡,耶穌派了兩個門徒,
2በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ፥ ወዲያውም ወደ እርስዋ ገብታችሁ ከሰው ማንም ገና ያልተቀመጠበት ውርንጫ ታስሮ ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁ አምጡልኝ።
2對他們說:“你們往對面的村子裡去,一進去,就會看見一頭小驢拴在那裡,是沒有人騎過的,把牠解開牽來。
3ማንም። ስለ ምን እንዲህ ታደርጋላችሁ? ቢላችሁ። ለጌታ ያስፈልገዋል በሉት፥ ወዲያውም ደግሞ ወደዚህ ይሰደዋል አላቸው።
3如果有人問你們:‘為甚麼這樣作?’你們就說:‘主需要牠,並且很快會送還到這裡來。’”
4ሄዱም ውርንጫውንም በመንገድ መተላለፊያ በደጅ ውጭ ታስሮ አገኙት፥ ፈቱትም።
4門徒去了,就發現一頭小驢,拴在門外的街上,就把牠解開。
5በዚያም ከቆሙት አንዳንዶቹ። ውርንጫውን የምትፈቱት ምን ልታደርጉት ነው አሉአቸው።
5站在那裡的人有的問他們說:“你們為甚麼解牠?”
6እነርሱም ኢየሱስ እንዳዘዘ አሉአቸው፤ ተዉአቸውም።
6門徒照著耶穌所說的話回答他們,那些人就讓他們牽走了。
7ውርንጫውንም ወደ ኢየሱስ አመጡት፥ ልብሳቸውንም በላዩ ጣሉ፥ ተቀመጠበትም።
7門徒把小驢牽到耶穌那裡,把自己的衣服搭在上面,耶穌就騎了上去。
8ብዙ ሰዎችም ልብሳቸውን በመንገድ ላይ አነጠፉ፥ ሌሎችም ከዛፍ ቅጠሎችን እየቈረጡ ያነጥፉ ነበር።
8許多人把衣服鋪在路上,還有人從田野裡砍了些樹枝也鋪在路上。
9የሚቀድሙትም የሚከተሉትም። ሆሣዕና፤ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤
9前行後隨的人都喊著說:“‘和散那’,奉主名來的是應當稱頌的!
10በጌታ ስም የምትመጣ የአባታችን የዳዊት መንግሥት የተባረከች ናት፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር።
10那將要來臨的,我們祖先大衛的國是應當稱頌的!高天之上當唱‘和散那’!”
11ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወደ መቅደስ ገባ፤ ዘወር ብሎም ሁሉን ከተመለከተ በኋላ፥ ጊዜው መሽቶ ስለ ነበረ ከአሥራ ሁለቱ ጋር ወደ ቢታንያ ወጣ።
11耶穌到了耶路撒冷,進入聖殿,察看了一切,因為時候已經不早,就和十二門徒出城往伯大尼去。
12በማግሥቱም ከቢታንያ ሲወጡ ተራበ።
12咒詛無花果樹(太21:18~19)第二天他們從伯大尼出來,耶穌餓了。
13ቅጠልም ያላት በለስ ከሩቅ አይቶ ምናልባት አንዳች ይገኝባት እንደ ሆነ ብሎ መጣ፥ ነገር ግን የበለስ ወራት አልነበረምና መጥቶ ከቅጠል በቀር ምንም አላገኘባትም።
13他遠遠看見一棵長滿了葉子的無花果樹,就走過去,看看是否可以在樹上找到甚麼。到了樹下,除了葉子甚麼也找不著,因為這不是收無花果的時候。
14መልሶም። ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ አላት። ደቀ መዛሙርቱም ሰሙ።
14耶穌對樹說:“永遠再沒有人吃你的果子了!”他的門徒也聽見了。
15ወደ ኢየሩሳሌምም መጡ። ወደ መቅደስም ገብቶ በመቅደስ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ያወጣ ጀመር፥ የገንዘብ ለዋጮችንም ገበታዎች የርግብ ሻጭዎችንም ወንበሮች ገለበጠ፤
15潔淨聖殿(太21:12~17、20~22;路19:45~47;約2:13~16)他們來到耶路撒冷。耶穌進了聖殿,就把殿裡作買賣的人趕走,又推倒找換銀錢的人的桌子,和賣鴿子的人的凳子;
16ዕቃም ተሸክሞ ማንም በመቅደስ ሊያልፍ አልፈቀደም።
16不許人拿著器皿穿過聖殿。
17አስተማራቸውም። ቤቴ ለአሕዛብ ሁሉ የጸሎት ቤት ትባላለች ተብሎ የተጻፈ አይደለምን? እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት አላቸው።
17他又教訓眾人說:“經上不是寫著‘我的殿要稱為萬國禱告的殿’嗎?你們竟把它弄成賊窩了。”
18የካህናት አለቆችም ጻፎችም ሰምተው፥ ሕዝቡ ሁሉ በትምህርቱ ይገረሙ ስለ ነበር ይፈሩት ነበርና እንዴት አድርገው እንዲያጠፉት ፈለጉ።
18祭司長和經學家聽見了,就想辦法怎樣除掉耶穌,卻又怕他,因為群眾都希奇他的教訓。
19ማታ ማታም ከከተማ ወደ ውጭ ይወጣ ነበር።
19到了晚上,他們就到城外去。
20ማለዳም ሲያልፉ በለሲቱን ከሥርዋ ደርቃ አዩአት።
20早晨,他們經過的時候,看見那棵無花果樹連根都枯萎了。
21ጴጥሮስም ትዝ ብሎት። መምህር ሆይ፥ እነሆ፥ የረገምሃት በለስ ደርቃለች አለው።
21彼得想起來就對耶穌說:“拉比,請看,你所咒詛的無花果樹,已經枯萎了。”
22ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው። በእግዚአብሔር እመኑ።
22耶穌回答他們:“你們對 神要有信心(“你們對 神要有信心”有些抄本作“如果你們對 神有信心”)。
23እውነት እላችኋለሁ፥ ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠር፥ ይህን ተራራ። ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ቢል ይሆንለታል።
23我實在告訴你們,無論甚麼人對這座山說‘移開,投到海裡’,只要他心裡不懷疑,相信他所說的一定能夠成就,就必給他成就。
24ስለዚህ እላችኋለሁ፥ የጸለያችሁትን የለመናችሁትንም ሁሉ እንዳገኛችሁት እመኑ፥ ይሆንላችሁማል።
24所以我告訴你們,凡是你們禱告祈求的,只要相信能夠得到,就必得到。
25ለጸሎትም በቆማችሁ ጊዜ፥ በሰማያት ያለው አባታችሁ ደግሞ ኃጢአታችሁን ይቅር እንዲላችሁ፥ በማንም ላይ አንዳች ቢኖርባችሁ ይቅር በሉት።
25你們站著禱告的時候,如果有誰得罪了你們,就該饒恕他,好使你們的天父也饒恕你們的過犯。”
26እናንተ ግን ይቅር ባትሉ በሰማያት ያለው አባታችሁም ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም።
26(有些抄本有第26節:“如果你們不饒恕人,你們的天父也必不饒恕你們的過犯。”)
27ደግሞም ወደ ኢየሩሳሌም መጡ። እርሱም በመቅደስ ሲመላለስ፥ የካህናት አለቆችና ጻፎች ሽማግሌዎችም ወደ እርሱ መጥተው።
27質問耶穌憑甚麼權柄作事(太21:23~27;路20:1~8)他們又來到耶路撒冷。耶穌在殿裡行走的時候,祭司長、經學家和長老來到他跟前,
28እነዚህን በምን ሥልጣን ታደርጋለህ? ወይስ እነዚህን ለማድረግ ይህን ሥልጣን ማን ሰጠህ? አሉት።
28問他:“你憑甚麼權柄作這些事?誰給你權柄作這些事?”
29ኢየሱስም። እኔም አንዲት ነገር እጠይቃችኋለሁ፥ እናንተም መልሱልኝ፥ እኔም በምን ሥልጣን እነዚህን እንዳደርግ እነግራችኋለሁ።
29耶穌對他們說:“我要問你們一句話,你們回答了我,我就告訴你們我憑甚麼權柄作這些事。
30የዮሐንስ ጥምቀት ከሰማይ ነበረችን ወይስ ከሰው? መልሱልኝ አላቸው።
30約翰的洗禮是從天上來的,還是從人來的呢?你們回答我吧。”
31እርስ በርሳቸውም ሲነጋገሩ። ከሰማይ ነው ብንል። እንግዲያውስ ስለ ምን አላመናችሁበትም? ይለናል፤
31他們就彼此議論:“如果我們說‘是從天上來的’,他就會說‘那你們為甚麼不信他呢?’
32ነገር ግን። ከሰው ነው እንበልን? አሉ፤ ሁሉ ዮሐንስን በእውነት እንደ ነቢይ ያዩት ነበርና ሕዝቡን ፈሩ።
32如果我們說‘是從人來的’……”他們害怕群眾,因為眾人都認為約翰的確是先知。
33ለኢየሱስም መልሰው። አናውቅም አሉት ኢየሱስም። እኔም በምን ሥልጣን እነዚህን እንዳደርግ አልነግራችሁም አላቸው።
33於是他們回答耶穌:“我們不知道。”耶穌對他們說:“我也不告訴你們我憑甚麼權柄作這些事。”