Amharic: New Testament

聖經新譯本

Mark

3

1ደግሞም ወደ ምኵራብ ገባ፥ በዚያም እጁ የሰለለች ሰው ነበር፤
1治好手枯的人(太12:9~14;路6:6~11)耶穌又進了會堂,在那裡有一個人,他的一隻手枯乾了。
2ሊከሱትም፥ በሰንበት ይፈውሰው እንደ ሆነ ይጠባበቁት ነበር።
2眾人窺探他會不會在安息日醫治那個人,好去控告他。
3እጁ የሰለለችውንም ሰው። ተነሥተህ ወደ መካከል ና አለው።
3耶穌對那一隻手枯乾了的人說:“起來,站在當中!”
4በሰንበት በጎ ማድረግ ተፈቅዶአልን? ወይስ ክፉ? ነፍስ ማዳን ወይስ መግደል? አላቸው፤ እነርሱም ዝም አሉ።
4又對他們說:“在安息日哪一樣是可以作的呢:作好事還是壞事?救命還是害命?”他們一聲不響。
5ስለ ልባቸውም ድንዛዜ አዝኖ ዙሪያውን እየተመለከተ በቍጣ አያቸው፥ ሰውየውንም። እጅህን ዘርጋ አለው።
5耶穌怒目環視他們,因他們的心剛硬而難過,就對那人說:“伸出手來!”他把手一伸,手就復原了。
6ዘረጋትም፥ እጁም ዳነች። ፈሪሳውያንም ወጥተው ወዲያው እንዴት አድርገው እንዲያጠፉት ከሄሮድስ ወገን ጋር ተማከሩበት።
6法利賽人出來,立刻和希律黨人商量怎樣對付耶穌,好除掉他。
7ኢየሱስም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ባህር ፈቀቅ አለ፤ ከገሊላ የመጡም ብዙ ሰዎች ተከተሉት፤
7許多人到海邊找耶穌(太12:15~16;路6:17~19)耶穌和門徒退到海邊去,一大群從加利利來的人跟著他;
8እንዴት ትልቅ ነገርም እንዳደረገው ሰምተው ብዙ ሰዎች ከይሁዳ ከኢየሩሳሌምም ከኤዶምያስም ከዮርዳኖስ ማዶም ከጢሮስና ከሲዶና ምድርም ወደ እርሱ መጡ።
8還有許多人聽見他所作的一切事,就從猶太、耶路撒冷、以土邁、約旦河外和推羅、西頓一帶地方來到他跟前。
9ሰዎቹም እንዳያጋፉት ታንኳን ያቆዩለት ዘንድ ደቀ መዛሙርቱን አዘዛቸው፤
9因為人多,耶穌就吩咐門徒為他預備一隻小船,免得眾人擁擠他。
10ብዙ ሰዎችን አድኖ ነበርና፥ ስለዚህም ሥቃይ ያለባቸው ሁሉ እንዲዳስሱት ይወድቁበት ነበር።
10他醫好了許多人,所以凡有病的都擠過來要摸他。
11ርኵሳን መናፍስትም ባዩት ጊዜ በፊቱ ተደፍተው። አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ እያሉ ጮኹ።
11污靈每次看到他,就仆倒在他面前,大聲喊叫說:“你是 神的兒子!”
12እንዳይገልጡትም በጣም አዘዛቸው።
12耶穌再三嚴厲地吩咐他們,不要把他的身分張揚出去。
13ወደ ተራራም ወጣ፥ ራሱም የወደዳቸውን ወደ እርሱ ጠራ፥ ወደ እርሱም ሄዱ።
13選立十二使徒(太10:1~4;路6:12~16。參徒1:13)耶穌上了山,呼召自己所要的人,他們就來了。
14ከእርሱም ጋር እንዲኖሩና ለመስበክ እንዲልካቸው፥
14他選立了十二個人,稱他們為使徒(有些抄本無“稱他們為使徒”一句),要他們跟自己常在一起,好差遣他們去傳道,
15ድውዮችንም ሊፈውሱ አጋንንትንም ሊያወጡ ሥልጣን ይሆንላቸው ዘንድ አሥራ ሁለት አደረገ፤
15又有權柄趕鬼。
16ስምዖንንም ጴጥሮስ ብሎ ሰየመው፤
16他選立的十二個人是:西門(耶穌給他起名叫彼得),
17የዘብዴዎስንም ልጅ ያዕቆብን የያዕቆብንም ወንድም ዮሐንስን ቦአኔርጌስ ብሎ ሰየማቸው፥ የነጎድጓድ ልጆች ማለት ነው፤
17西庇太的兒子雅各,和雅各的弟弟約翰(耶穌給他們二人起名叫半尼其,就是“雷子”的意思),
18እንድርያስንም ፊልጶስንም በርተሎሜውስንም ማቴዎስንም ቶማስንም የእልፍዮስን ልጅ ያዕቆብንም ታዴዎስንም ቀነናዊውንም ስምዖንን፥
18安得烈、腓力、巴多羅邁、馬太、多馬、亞勒腓的兒子雅各、達太、激進派的西門,
19አሳልፎ የሰጠውንም የአስቆሮቱን ይሁዳን።
19以及加略人猶大,就是出賣耶穌的那個人。
20ወደ ቤትም መጡ፤ እንጀራም መብላት ስንኳ እስኪሳናቸው ድረስ እንደ ገና ብዙ ሰዎች ተሰበሰቡ።
20褻瀆聖靈的罪不得赦免(太12:22~32;路11:14~23,12:10)耶穌進了屋子,群眾又聚了來,以致他們連飯都不能吃,
21ዘመዶቹም ሰምተው። አበደ ብለዋልና ሊይዙት ወጡ።
21那些和他在一起的人聽見了,就出來抓住他,因為他們說他癲狂了。
22ከኢየሩሳሌም የወረዱ ጻፎችም። ብዔል ዜቡል አለበት፤ ደግሞ። በአጋንንት አለቃ አጋንንትን ያወጣል ብለው ተናገሩ።
22從耶路撒冷下來的經學家說:“他有別西卜附在身上!”又說:“他靠著鬼王趕鬼。”
23እነርሱንም ወደ እርሱ ጠርቶ በምሳሌ አላቸው። ሰይጣን ሰይጣንን ሊያወጣው እንዴት ይችላል?
23耶穌把他們叫來,用比喻對他們說:“撒但怎能趕逐撒但呢?
24መንግሥትም እርስ በርስዋ ከተለያየች ያች መንግሥት ልትቆም አትችልም፤
24一國若自相紛爭,那國就站立不住;
25ቤትም እርስ በርሱ ከተለያየ ያ ቤት ሊቆም አይችልም።
25一家若自相紛爭,那家就站立不住。
26ሰይጣንም ራሱን ተቃውሞ ከተለያየ፥ መጨረሻ ይሆንበታል እንጂ ሊቆም አይችልም።
26如果撒但自相攻打紛爭,不但站立不住,而且還要滅亡。
27ነገር ግን አስቀድሞ ኃይለኛውን ሳያስር ወደ ኃይለኛው ቤት ገብቶ ዕቃውን ሊበዘብዝ የሚችል የለም፥ ከዚያም ወዲያ ቤቱን ይበዘብዛል።
27誰都不能進入壯漢的家,搶奪他的財物,除非先把壯漢捆綁起來,才可以搶劫他的家。
28እውነት እላችኋለሁ፥ ለሰው ልጆች ኃጢአት ሁሉ የሚሳደቡትም ስድብ ሁሉ ይሰረይላቸዋል፤
28我實在告訴你們,世人的一切罪和一切褻瀆的話,都可以得到赦免;
29በመንፈስ ቅዱስ ላይ የሚሳደብ ሁሉ ግን የዘላለም ኃጢአት ዕዳ ይሆንበታል እንጂ ለዘላለም አይሰረይለትም።
29但褻瀆聖靈的,就永世不得赦免,他還要擔當罪惡到永遠。”
30ርኵስ መንፈስ አለበት ይሉ ነበርና።
30耶穌說這話,是因為他們說他有污靈附在身上。
31እናቱና ወንድሞቹም መጡ በውጭም ቆመው ወደ እርሱ ልከው አስጠሩት።
31誰是耶穌的母親和弟兄(太12:46~50;路8:19~21)耶穌的母親和弟弟來了,站在外面,傳話給他,叫他出來。
32ብዙ ሰዎችም በዙሪያው ተቀምጠው ነበሩና። እነሆ፥ እናትህ ወንድሞችህም በውጭ ቆመው ይፈልጉሃል አሉት።
32有許多人正圍坐在耶穌身邊,他們告訴他:“你看,你的母親和弟弟(有些抄本在此有“妹妹”一詞)在外面找你。”
33መልሶም። እናቴ ማን ናት? ወንድሞቼስ እነ ማን ናቸው? አላቸው።
33耶穌回答他們:“誰是我的母親,我的弟兄呢?”
34በዙሪያው ተቀምጠው ወደ ነበሩትም ተመለከተና። እነሆ እናቴ ወንድሞቼም።
34於是四面觀看那些圍坐的人,說:“你們看,我的母親!我的弟兄!
35የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ፥ እርሱ ወንድሜ ነው እኅቴም እናቴም አለ።
35凡遵行 神旨意的,就是我的弟兄姊妹和母親了。”