1ፈሪሳውያንና ከጻፎች ወገን ከኢየሩሳሌም የመጡትም ወደ እርሱ ተሰበሰቡ።
1不可因傳統廢棄 神的誡命(太15:1~20)有法利賽人和幾個經學家從耶路撒冷來,聚集到耶穌那裡。
2ከደቀ መዛሙርቱም አንዳንድ በርኵስ ማለት ባልታጠበ እጅ እንጀራ ሲበሉ አዩ።
2他們看見他的門徒有人用不潔的手,就是沒有洗過的手吃飯,
3ፈሪሳውያንና አይሁድም ሁሉ የሽማግሎችን ወግ ሲጠብቁ እጃቸውን ደኅና አድርገው ሳይታጠቡ አይበሉምና፥
3(原來法利賽人和所有的猶太人都拘守古人的傳統,如果不認真洗手,就不吃東西;
4ከገበያም ተመልሰው ካልታጠቡ አይበሉም፥ ጽዋንም ማድጋንም የናስ ዕቃንም አልጋንም እንደ ማጠብ ሌላ ነገር ሊጠብቁት የተቀበሉት ብዙ አለ።
4從街市回來,不先洗手,也不吃東西,還有許多別的傳統,他們都沿襲拘守,例如洗杯、洗罐、洗銅器等等。)
5ፈሪሳውያንም ጻፎችም። ደቀ መዛሙርትህ እንደ ሽማግሌዎች ወግ ስለ ምን አይሄዱም? ነገር ግን እጃቸውን ሳይታጠቡ እንጀራ ይበላሉ ብለው ጠየቁት።
5法利賽人和經學家問耶穌:“你的門徒為甚麼不遵行古人的傳統,用不潔的手吃飯呢?”
6እርሱ ግን እንዲህ አላቸው። ኢሳይያስ ስለ እናንተ ስለ ግብዞች። ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል ልቡ ግን ከእኔ በጣም የራቀ ነው፤
6耶穌對他們說:“以賽亞指著你們這班偽君子所說的預言是對的,經上記著:‘這人民用嘴唇尊敬我,心卻遠離我;
7የሰውም ሥርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል ተብሎ እንደ ተጻፈ በእውነት ትንቢት ተናገረ።
7他們把人的規條當作道理去教導人,所以拜我也是徒然。’
8የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ትታችሁ ጽዋን ማድጋንም እንደ ማጠብ የሰውን ወግ ትጠብቃላችሁ፥ ይህንም የመሰለ ብዙ ሌላ ነገር ታደርጋላችሁ።
8你們拘守著人的傳統,卻離棄了 神的誡命。”
9እንዲህም አላቸው። ወጋችሁን ትጠብቁ ዘንድ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እጅግ ንቃችኋል።
9耶穌又對他們說:“你們為了堅守自己的傳統,而巧妙地把 神的誡命拒絕了。
10ሙሴ። አባትህንና እናትህን አክብር፤ ደግሞ። አባቱን ወይም እናቱን የሰደበ ፈጽሞ ይሙት ብሎአልና።
10因為摩西說:‘當孝敬父母’,又說:‘咒罵父母的,必被處死。’
11እናንተ ግን ትላላችሁ። ሰው አባቱን ወይም እናቱን። ከእኔ የምትጠቀምበት ነገር ሁሉ ቍርባን ማለት መባ ነው ቢል፥
11你們倒說:‘人對父母說,我應該給你的供奉,已經作了各耳板’(各耳板意思是奉給 神的供物),
12ለአባቱና ለእናቱ ምንም እንኳ ሊያደርግ ወደ ፊት አትፈቅዱለትም፤
12你們就不讓那人再為父母作甚麼。
13ባስተላለፋችሁትም ወግ የእግዚአብሔርን ቃል ትሽራላችሁ፤ እንደዚሁም ይህን የሚመስል ብዙ ነገር ታደርጋላችሁ።
13這樣,你們藉著所領受的傳統,把 神的話廢棄了。你們還作了許多這一類的事。”
14ደግሞም ሕዝቡን ጠርቶ። ሁላችሁ እኔን ስሙ አስተውሉም።
14於是耶穌又把群眾叫過來,對他們說:“你們大家都要聽我說,也要明白:
15ከሰው የሚወጡት ሰውን የሚያረክሱ ናቸው እንጂ ከሰው ውጭ የሚገባውስ ሊያረክሰው የሚችል ምንም የለም።
15從外面進去的,不能使人污穢,從裡面出來的,才能使人污穢。”
16የሚሰማ ጆሮ ያለው ቢኖር ይስማ አላቸው።
16(有些抄本有第16節:“有耳可聽的,就應該聽。”)
17ከሕዝቡ ዘንድ ወደ ቤት ከገባ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ምሳሌውን ጠየቁት።
17耶穌離開群眾,進了屋子,門徒就來問他這比喻的意思。
18እርሱም። እናንተ ደግሞ እንደዚህ የማታስተውሉ ናችሁን? ከውጭ ወደ ሰው የሚገባ ሊያረክሰው ምንም እንዳይችል አትመለከቱምን?
18他對他們說:“連你們也是這樣不明白嗎?難道不知道從外面進去的,不能使人污穢嗎?
19ወደ ሆድ ገብቶ ወደ እዳሪ ይወጣል እንጂ ወደ ልብ አይገባምና፤ መብልን ሁሉ እያጠራ አላቸው።
19因為不是進到他的心,而是進到他的肚腹,再排泄到外面去。”(他這樣說是表示各樣食物都是潔淨的。)
20እርሱም አለ። ከሰው የሚወጣው ሰውን የሚያረክስ ያ ነው።
20接著他又說:“從人裡面出來的,才會使人污穢。
21ከውስጥ ከሰው ልብ የሚወጣ ክፉ አሳብ፥
21因為從裡面,就是從人的心裡,發出惡念、淫亂、偷盜、兇殺、
22ዝሙት፥ መስረቅ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ መጐምጀት፥ ክፋት፥ ተንኰል፥ መዳራት፥ ምቀኝነት፥ ስድብ፥ ትዕቢት፥ ስንፍና ናቸውና፤
22姦淫、貪心、邪惡、詭詐、放蕩、嫉妒、毀謗、驕傲、愚妄;
23ይህ ክፉው ሁሉ ከውስጥ ይወጣል ሰውን ያረክሰዋል።
23這一切惡事,是從人裡面出來的,都能使人污穢。”
24ከዚያም ተነሥቶ ወደ ጢሮስና ወደ ሲዶና አገር ሄደ። ወደ ቤትም ገብቶ ማንም እንዳያውቅበት ወደደ ሊሰወርም አልተቻለውም፤
24敘利亞婦人的信心(太15:21~28)耶穌從那裡動身到推羅(有些抄本在此有“和西頓”)境內去。進了一所房子,本來不想讓人知道,卻隱藏不住。
25ወዲያው ግን ታናሺቱ ልጅዋ ርኵስ መንፈስ ያደረባት አንዲት ሴት ስለ እርሱ ሰምታ መጣችና በእግሩ ላይ ተደፋች
25有一個女人,她的小女兒被污靈附著,她聽見了耶穌的事,就來俯伏在他腳前。
26ሴቲቱም ግሪክ፥ ትውልድዋም ሲሮፊኒቃዊት ነበረች፤ ከልጅዋ ጋኔን ያወጣላት ዘንድ ለመነችው።
26這女人是外族人,屬於敘利亞的腓尼基族。她求耶穌把鬼從她女兒身上趕出去。
27ኢየሱስ ግን። ልጆቹ በፊት ይጠግቡ ዘንድ ተዪ የልጆቹን እንጀራ ይዞ ለቡችሎች መጣል አይገባምናአላት።
27耶穌對她說:“應該先讓兒女吃飽。拿兒女的餅去丟給小狗吃是不好的。”
28እርስዋም መልሳ። አዎን፥ ጌታ ሆይ፥ ቡችሎች እንኳ ከማዕድ በታች ሆነው የልጆችን ፍርፋሪ ይበላሉ አለችው።
28那女人回答他:“主啊,是的,不過小狗在桌子底下,也可以吃孩子們掉下來的碎渣。”
29እርሱም። ስለዚህ ቃልሽ ሂጂ ጋኔኑ ከልጅሽ ወጥቶአል አላት።
29耶穌對她說:“就憑這句話,你回去吧,鬼已經從你女兒身上出去了。”
30ወደ ቤትዋም ሄዳ ጋኔኑ ወጥቶ ልጅዋም በአልጋ ላይ ተኝታ አገኘች።
30她回到家裡,看見小孩子躺在床上,鬼已經出去了。
31ደግሞም ከጢሮስ አገር ወጥቶ በሲዶና አልፎ አሥር ከተማ በሚባል አገር መካከል ወደ ገሊላ ባሕር መጣ።
31治好又聾又啞的人(太15:29~31)耶穌從推羅境內出去,經過西頓,回到低加波利地區的加利利海。
32ደንቆሮና ኰልታፋም የሆነ ሰው ወደ እርሱ አመጡ፥
32有人帶著一個又聾又啞的人到他那裡,求耶穌按手在他身上。
33እጁንም ይጭንበት ዘንድ ለመኑት። ከሕዝቡም ለይቶ ለብቻው ወሰደው፥ ጣቶቹንም በጆሮቹ አገባ እንትፍም ብሎ መላሱን ዳሰሰ፤
33耶穌把他從人群中帶到一邊,用指頭探他的耳朵,吐唾沫抹他的舌頭,
34ወደ ሰማይም አሻቅቦ አይቶ ቃተተና። ኤፍታህ አለው፥ እርሱም ተከፈት ማለት ነው።
34然後望著天,長長地歎了一口氣,對他說:“以法大!”意思是“開了吧”。
35ወዲያውም ጆሮቹ ተከፈቱ የመላሱም እስራት ተፈታ አጥርቶም ተናገረ።
35那人的耳朵就開了,舌頭也鬆了,說話也準確了。
36ለማንም አትንገሩ ብሎ አዘዛቸው እነርሱ ግን ባዘዛቸውም መጠን ይልቅ እጅግ አወሩት።
36耶穌囑咐他們不要告訴人。但他越是囑咐,他們卻越發傳揚。
37ያለ መጠንም ተገረሙና። ሁሉን ደኅና አድርጎአል፤ ደንቆሮችም እንዲሰሙ ዲዳዎችም እንዲናገሩ ያደርጋል አሉ።
37眾人非常驚訝說:“他所作的一切事都好極了;他竟然使聾子聽見,又使啞巴說話。”