Amharic: New Testament

聖經新譯本

Revelation

10

1ሌላም ብርቱ መልአክ ደመና ተጐናጽፎ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ በራሱም ላይ ቀስተ ደመና ነበረ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ እግሮቹም እንደ እሳት ዓምዶች ነበሩ፥
1天使與小書卷我又看見一位大力的天使從天上降下來,身披雲彩,頭上有彩虹,臉像太陽,兩腳像火柱一樣,
2የተከፈተችንም ታናሽ መጽሐፍ በእጁ ያዘ። ቀኝ እግሩንም በባሕር ላይ ግራውንም በምድር ላይ አኖረ፥ እንደሚያገሣም አንበሳ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።
2手裡拿著展開的小書卷。他的右腳踏在海上,左腳踏在地上,
3በጮኸም ጊዜ ሰባቱ ነጐድጓድ በየድምፃቸው ተናገሩ።
3大聲呼喊,好像獅子吼叫。他呼喊的時候,就有七雷發聲說話。
4ሰባቱ ነጐድጓድ በተናገሩ ጊዜ ልጽፍ አሰብሁ፤ ከሰማይም። ሰባቱ ነጐድጓድ የተናገሩትን ነገር በማኅተም ዝጋው አትጻፈውም የሚል ድምፅ ሰማሁ።
4七雷說話的時候,我正要寫下來,就聽見有聲音從天上出來,說:“七雷所說的你要封住,不可寫出來!”
5በባሕርና በምድርም ላይ ሲቆም ያየሁት መልአክ ቀኝ እጁን ወደ ሰማይ አሻቅቦ ዘረጋ፥
5我看見那站在海上和地上的天使,向天舉起右手來,
6ሰማይንና በእርሱም ያሉትን፥ ምድርንና በእርስዋም ያሉትን፥ ባሕርንና በእርሱም ያሉትን በፈጠረው፥ ከዘላለምም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ሆኖ በሚኖረው ምሎ።
6指著那活到永永遠遠,創造天和天上之物、地和地上之物、海和海中之物的 神起誓,說:“必不再延遲了!
7ወደ ፊት አይዘገይም፥ ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ሊነፋ ባለው ጊዜ ድምፁም በሚሰማበት ዘመን፥ ለባሪያዎቹ ለነቢያት የምስራች እንደ ሰበከላቸው የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል አለ።
7到第七位天使吹號的時候, 神向他的僕人眾先知所宣告的奧祕,就要實現了。”
8ከሰማይም የሰማሁት ድምፅ እንደ ገና ሲናገረኝና። ሂድና በባሕርና በምድር ላይ ከሚቆመው መልአክ በእጁ ያለችውን የተከፈተችውን መጽሐፍ ውሰድ ሲል ሰማሁ።
8我先前聽見那從天上來的聲音又對我說:“你去,把那站在海上和地上的天使手中展開的書卷拿過來。”
9ወደ መልአኩም ሄጄ። ታናሺቱን መጽሐፍ ስጠኝ አልሁት። እርሱም። ውሰድና ብላት፥ ሆድህንም መራራ ታደርገዋለች በአፍህ ግን እንደ ማር ትጣፍጣለች አለኝ።
9我就走到天使那裡,請他把小書卷給我。他對我說:“你拿著,吃下去。它必使你肚子苦澀,但是口裡卻好像蜜一樣甘甜。”
10ከመልአኩም እጅ ታናሺቱን መጽሐፍ ወስጄ በላኋት በአፌም እንደ ማር ጣፋጭ ሆነች፤ ከበላኋት በኋላም ሆዴ መራራ ሆነ።
10我把小書卷從天使手中拿過來,吃了,在口裡果然甘甜如蜜;但是吃完之後,我肚子就覺得苦澀。
11በብዙ ወገኖችና በአሕዛብም በቋንቋዎችም በነገሥታትም ላይ እንደ ገና ትንቢት ትናገር ዘንድ ይገባሃል ተባለልኝ።
11他們又對我說:“論到許多民族、邦國、方言和君王,你必須再說預言。”