1ለቅዱሳንም ገንዘብን ስለ ማዋጣት፥ ለገላትያ አብያተ ክርስቲያናት እንደ ደነገግሁት እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉ።
1Now concerning the collection for the saints, as I gave order to the churches of Galatia, so also do ye.
2እኔ ስመጣ ይህ የገንዘብ ማዋጣት ያን ጊዜ እንዳይሆን፥ ከእናንተ እያንዳንዱ በየሳምንቱ በፊተኛው ቀን እንደ ቀናው መጠን እያስቀረ በቤቱ ያስቀምጥ።
2Upon the first day of the week let each one of you lay by him in store, as he may prosper, that no collections be made when I come.
3ስመጣም ማናቸውም ቢሆኑ የታመኑ የሚመስሉአችሁ ሰዎች ቸርነታችሁን ወደ ኢየሩሳሌም ያደርሱ ዘንድ ደብዳቤ ሰጥቼ እልካቸዋለሁ፤
3And when I arrive, whomsoever ye shall approve, them will I send with letters to carry your bounty unto Jerusalem:
4እኔ ደግሞ ልሄድ የሚገባኝ ብሆን ከእኔ ጋር አብረው ይሄዳሉ።
4and if it be meet for me to go also, they shall go with me.
5በመቄዶንያም ሳልፍ ወደ እናንተ እመጣለሁ፤ በመቄዶንያ አድርጌ አልፋለሁና፤
5But I will come unto you, when I shall have passed through Macedonia; for I pass through Macedonia;
6እናንተም ወደምሄድበት ወደ ማናቸውም ስፍራ በጉዞዬ እንድትረዱኝ ምናልባት በእናንተ ዘንድ እቆይ ወይም እከርም ይሆናል።
6but with you it may be that I shall abide, or even winter, that ye may set me forward on my journey whithersoever I go.
7አሁን እግረ መንገዴን ሳልፍ ልጎበኛችሁ አልወድምና፤ ጌታ ቢፈቅደው የሆነውን ዘመን በእናንተ ዘንድ ልሰነብት ተስፋ አደርጋለሁና።
7For I do not wish to see you now by the way; for I hope to tarry a while with you, if the Lord permit.
8በኤፌሶን ግን እስከ በዓለ ኀምሳ ድረስ እሰነብታለሁ።
8But I will tarry at Ephesus until Pentecost;
9ሥራ የሞላበት ትልቅ በር ተከፍቶልኛልና ተቃዋሚዎችም ብዙ ናቸው።
9for a great door and effectual is opened unto me, and there are many adversaries.
10ጢሞቴዎስም የመጣ እንደ ሆነ በእናንተ ዘንድ ያለ ፍርሃት እንዲኖር ተጠንቀቁ፤ እንደ እኔ ደግሞ የጌታን ሥራ ይሠራልና፤ እንግዲህ ማንም አይናቀው።
10Now if Timothy come, see that he be with you without fear; for he worketh the work of the Lord, as I also do:
11ነገር ግን ከወንድሞቹ ጋር እጠብቀዋለሁና ወደ እኔ ይመጣ ዘንድ በሰላም በጉዞው እርዱት።
11let no man therefore despise him. But set him forward on his journey in peace, that he may come unto me: for I expect him with the brethren.
12ስለ ወንድማችን ስለ አጵሎስ ግን ከወንድሞቹ ጋር ወደ እናንተ ሊሄድ እጅግ አድርጌ ለምኜው ነበር፤ ዛሬም ለመምጣት ከቶ ፈቃድ አልነበረውም፥ ሲመቸው ግን ይመጣል።
12But as touching Apollos the brother, I besought him much to come unto you with the brethren: and it was not all [his] will to come now; but he will come when he shall have opportunity.
13ንቁ፥ በሃይማኖት ቁሙ፥ ጎልምሱ ጠንክሩ።
13Watch ye, stand fast in the faith, quit you like men, be strong.
14በእናንተ ዘንድ ሁሉ በፍቅር ይሁን።
14Let all that ye do be done in love.
15ወንድሞች ሆይ፥ የእስጢፋኖስ ቤተ ሰዎች የአካይያ በኩራት እንደ ሆኑ ቅዱሳንንም ለማገልገል ራሳቸውን እንደ ሰጡ ታውቃላችሁ፤
15Now I beseech you, brethren (ye know the house of Stephanas, that it is the firstfruits of Achaia, and that they have set themselves to minister unto the saints),
16እንደ እነርሱ ላሉትና አብሮ ለሚሠራ ለሚደክምም ሁሉ እናንተም እንድትገዙ እለምናችኋለሁ።
16that ye also be in subjection unto such, and to every one that helpeth in the work and laboreth.
17በእስጢፋኖስና በፈርዶናጥስ በአካይቆስም መምጣት ደስ ይለኛል፥ እናንተ ስለሌላችሁ የጎደለኝን ፈጽመዋልና፤ መንፈሴንና መንፈሳችሁን አሳርፈዋልና።
17And I rejoice at the coming of Stephanas and Fortunatus and Achaicus: for that which was lacking on your part they supplied.
18እንግዲህ እንደነዚህ ያሉትን እወቁአቸው።
18For they refreshed my spirit and yours: acknowledge ye therefore them that are such.
19የእስያ አብያተ ክርስቲያናት ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። አቂላና ጵርስቅላ በቤታቸው ካለች ቤተ ክርስቲያን ጋር በጌታ እጅግ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።
19The churches of Asia salute you. Aquila and Prisca salute you much in the Lord, with the church that is in their house.
20ወንድሞች ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። በተቀደሰ አሳሳም እርስ በርሳችሁ ሰላምታ ተሰጣጡ።
20All the brethren salute you. Salute one another with a holy kiss.
21እኔ ጳውሎስ ይህን ሰላምታ በገዛ እጄ ጽፌአለሁ።
21The salutation of me Paul with mine own hand.
22ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን የማይወድ ቢኖር የተረገመ ይሁን። ጌታችን ሆይ፥ ና።
22If any man loveth not the Lord, let him be anathema. Maranatha.
23የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።
23The grace of the Lord Jesus Christ be with you.
24ፍቅሬ በክርስቶስ ኢየሱስ ከሁላችሁ ጋር ነው። አሜን።
24My love be with you all in Christ Jesus. Amen.