1አብረንም እየሠራን የእግዚአብሔርን ጸጋ በከንቱ እንዳትቀበሉ ደግሞ እንለምናለን፤
1And working together [with him] we entreat also that ye receive not the grace of God in vain
2በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ በመዳንም ቀን ረዳሁህ ይላልና፤ እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ እነሆ፥ የመዳን ቀን አሁን ነው።
2(for he saith, At an acceptable time I hearkened unto thee, And in a day of salvation did I succor thee: behold, now is the acceptable time; behold, now is the day of salvation):
3አገልግሎታችንም እንዳይነቀፍ በአንዳች ነገር ማሰናከያ ከቶ አንሰጥም።
3giving no occasion of stumbling in anything, that our ministration be not blamed;
4ነገር ግን በሁሉ እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች ራሳችንን እናማጥናለን፤
4but in everything commending ourselves, as ministers of God, in much patience, in afflictions, in necessities, in distresses,
5በብዙ መጽናት፥ በመከራ፥ በችግር፥ በጭንቀት፥ በመገረፍ፥ በወኅኒ፥ በሁከት፥ በድካም፥ እንቅልፍ በማጣት፥
5in stripes, in imprisonments, in tumults, in labors, in watchings, in fastings;
6በመጦም፥ በንጽህና፥ በእውቀት፥ በትዕግሥት፥ በቸርነት፥ በመንፈስ ቅዱስ፥ ግብዝነት በሌለው ፍቅር፥ በእውነት ቃል፥
6in pureness, in knowledge, in long suffering, in kindness, in the Holy Spirit, in love unfeigned,
7በእግዚአብሔር ኃይል፥ ለቀኝና ለግራ በሚሆን በጽድቅ የጦር ዕቃ፥ በክብርና በውርደት፥
7in the word of truth, in the power of God; by the armor of righteousness on the right hand and on the left,
8በክፉ ወሬና በመልካም ወሬ ራሳችንን እናማጥናለን፤ አሳቾች ስንባል እውነተኞች ነን፤
8by glory and dishonor, by evil report and good report; as deceivers, and [yet] true;
9ያልታወቁ ስንባል የታወቅን ነን፤ የምንሞት ስንመስል እነሆ ሕያዋን ነን፤ የተቀጣን ስንሆን አንገደልም፤
9as unknown, and [yet] well known; as dying, and behold, we live; as chastened, and not killed;
10ኀዘንተኞች ስንሆን ዘወትር ደስ ይለናል፤ ድሆች ስንሆን ብዙዎችን ባለ ጠጎች እናደርጋለን፤ አንዳች የሌለን ስንሆን ሁሉ የእኛ ነው።
10as sorrowful, yet always rejoicing; as poor, yet making many rich; as having nothing, and [yet] possessing all things.
11እናንተ የቆሮንቶስ ሰዎች ሆይ፥ አፋችን ለእናንተ ተከፍቶአል ልባችንም ሰፍቶላችኋል፤
11Our mouth is open unto you, O Corinthians, our heart is enlarged.
12በእኛ አልጠበባችሁም በሆዳችሁ ግን ጠቦባችኋል፤
12Ye are not straitened in us, but ye are straitened in your own affections.
13ልጆቼ እንደ መሆናችሁ ግን እላችኋለሁ፥ እናንተ ደግሞ ብድራት መልሳችሁልን ተስፋፉ።
13Now for a recompense in like kind (I speak as unto [my] children), be ye also enlarged.
14ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው?
14Be not unequally yoked with unbelievers: for what fellowship have righteousness and iniquity? or what communion hath light with darkness?
15ክርስቶስስ ከቤልሆር ጋር ምን መስማማት አለው? ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ክፍል አለው?
15And what concord hath Christ with Belial? or what portion hath a believer with an unbeliever?
16ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም ከጣዖት ጋር ምን መጋጠም አለው? እኛ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነንና እንዲሁም እግዚአብሔር ተናገረ እንዲህ ሲል። በእነርሱ እኖራለሁ በመካከላቸውም እመላለሳለሁ፥ አምላካቸውም እሆናለሁ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።
16And what agreement hath a temple of God with idols? for we are a temple of the living God; even as God said, I will dwell in them, and walk in them; and I will be their God, and they shall be my people.
17ስለዚህም ጌታ። ከመካከላቸው ውጡና የተለያችሁ ሁኑ ርኵስንም አትንኩ ይላል፤ ሁሉንም የሚገዛ ጌታ። እኔም እቀበላችኋለሁ፥ ለእናንተም አባት እሆናለሁ እናንተም ለእኔ ወንድ ልጆችና ሴት ልጆች ትሆናላችሁ ይላል።
17Wherefore Come ye out from among them, and be ye separate, saith the Lord, And touch no unclean thing; And I will receive you,
18And will be to you a Father, And ye shall be to me sons and daughters, saith the Lord Almighty.