1ከፈሪሳውያንም ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱም በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ።
1Now there was a man of the Pharisees, named Nicodemus, a ruler of the Jews:
2መምህር ሆይ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህን ምልክቶች ሊያደርግ የሚችል የለምና መምህር ሆነህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን አለው።
2the same came unto him by night, and said to him, Rabbi, we know that thou art a teacher come from God; for no one can do these signs that thou doest, except God be with him.
3ኢየሱስም መልሶ። እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው።
3Jesus answered and said unto him, Verily, verily, I say unto thee, Except one be born anew, he cannot see the kingdom of God.
4ኒቆዲሞስም። ሰው ከሸመገለ በኋላ እንዴት ሊወለድ ይችላል? ሁለተኛ ወደ እናቱ ማኅፀን ገብቶ ይወለድ ዘንድ ይችላልን? አለው።
4Nicodemus saith unto him, How can a man be born when he is old? can he enter a second time into his mother's womb, and be born?
5ኢየሱስም መለሰ፥ እንዲህ ሲል። እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም።
5Jesus answered, Verily, verily, I say unto thee, Except one be born of water and the Spirit, he cannot enter into the kingdom of God!
6ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፥ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው።
6That which is born of the flesh is flesh; and that which is born of the Spirit is spirit.
7ዳግመኛ ልትወለዱ ያስፈልጋችኋል ስላልሁህ አታድንቅ።
7Marvel not that I said unto thee, Ye must be born anew.
8ነፋስ ወደሚወደው ይነፍሳል፥ ድምፁንም ትሰማለህ፥ ነገር ግን ከወዴት እንደ መጣ ወዴትም እንዲሄድ አታውቅም፤ ከመንፈስ የተወለደ ሁሉ እንዲሁ ነው።
8The wind bloweth where it will, and thou hearest the voice thereof, but knowest not whence it cometh, and whither it goeth: so is every one that is born of the Spirit.
9ኒቆዲሞስ መልሶ። ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? አለው።
9Nicodemus answered and said unto him, How can these things be?
10ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው። አንተ የእስራኤል መምህር ስትሆን ይህን አታውቅምን?
10Jesus answered and said unto him, Art thou the teacher of Israel, and understandest not these things?
11እውነት እውነት እልሃለሁ፥ የምናውቀውን እንናገራለን ያየነውንም እንመሰክራለን፥ ምስክራችንንም አትቀበሉትም።
11Verily, verily, I say unto thee, We speak that which we know, and bear witness of that which we have seen; and ye receive not our witness.
12ስለ ምድራዊ ነገር በነገርኋችሁ ጊዜ ካላመናችሁ፥ ስለ ሰማያዊ ነገር ብነግራችሁ እንዴት ታምናላችሁ?
12If I told you earthly things and ye believe not, how shall ye believe if I tell you heavenly things?
13ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው።
13And no one hath ascended into heaven, but he that descended out of heaven, [even] the Son of man, who is in heaven.
14ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል።
14And as Moses lifted up the serpent in the wilderness, even so must the Son of man be lifted up;
16በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።
15that whosoever believeth may in him have eternal life.
17ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ፥ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና።
16For God so loved the world, that he gave his only begotten Son, that whosoever believeth on him should not perish, but have eternal life.
18በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል።
17For God sent not the Son into the world to judge the world; but that the world should be saved through him.
19ብርሃንም ወደ ዓለም ስለ መጣ ሰዎችም ሥራቸው ክፉ ነበርና ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ስለ ወደዱ ፍርዱ ይህ ነው።
18He that believeth on him is not judged: he that believeth not hath been judged already, because he hath not believed on the name of the only begotten Son of God.
20ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና፥ ሥራውም እንዳይገለጥ ወደ ብርሃን አይመጣም፤
19And this is the judgment, that the light is come into the world, and men loved the darkness rather than the light; for their works were evil.
21እውነትን የሚያደርግ ግን ሥራው በእግዚአብሔር ተደርጎ እንደ ሆነ ይገለጥ ዘንድ ወደ ብርሃን ይመጣል።
20For every one that doeth evil hateth the light, and cometh not to the light, lest his works should be reproved.
22ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ይሁዳ አገር መጣ፥ በዚያም ከእነርሱ ጋር ተቀምጦ ያጠምቅ ነበር።
21But he that doeth the truth cometh to the light, that his works may be made manifest, that they have been wrought in God.
23ዮሐንስም ደግሞ በሳሌም አቅራቢያ በሄኖን በዚያ ብዙ ውኃ ነበርና ያጠምቅ ነበር፥
22After these things came Jesus and his disciples into the land of Judea; and there he tarried with them, and baptized.
24እየመጡም ይጠመቁ ነበር ዮሐንስ ገና ወደ ወኅኒ አልተጨመረም ነበርና።
23And John also was baptizing in Enon near to Salim, because there was much water there: and they came, and were baptized.
25ስለዚህም በዮሐንስ ደቀ መዛሙርትና በአይሁድ መካከል ስለ ማንጻት ክርክር ሆነ።
24For John was not yet cast into prison.
26ወደ ዮሐንስም መጥተው። መምህር ሆይ፥ በዮርዳኖስ ማዶ ከአንተ ጋር የነበረው አንተም የመሰከርህለት፥ እነሆ፥ እርሱ ያጠምቃል ሁሉም ወደ እርሱ ይመጣሉ አሉት።
25There arose therefore a questioning on the part of John's disciples with a Jew about purifying.
27ዮሐንስ መለሰ፥ እንዲህ ሲል። ከሰማይ ካልተሰጠው ሰው እንዳች ሊቀበል አይችልም።
26And they came unto John, and said to him, Rabbi, he that was with thee beyond the Jordan, to whom thou hast borne witness, behold, the same baptizeth, and all men come to him.
28እናንተ። እኔ ክርስቶስ አይደለሁም፥ ነገር ግን። ከእርሱ በፊት ተልኬአለሁ እንዳልሁ ራሳችሁ ትመሰክሩልኛላችሁ።
27John answered and said, A man can receive nothing, except it have been given him from heaven.
29ሙሽራይቱ ያለችው እርሱ ሙሽራ ነው፤ ቆሞ የሚሰማው ሚዜው ግን በሙሽራው ድምጽ እጅግ ደስ ይለዋል። እንግዲህ ይህ ደስታዬ ተፈጸመ።
28Ye yourselves bear me witness, that I said, I am not the Christ, but, that I am sent before him.
30እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ያስፈልጋል።
29He that hath the bride is the bridegroom: but the friend of the bridegroom, that standeth and heareth him, rejoiceth greatly because of the bridegroom's voice: this my joy therefore is made full.
31ከላይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው፤ ከምድር የሚሆነው የምድር ነው የምድሩንም ይናገራል። ከሰማይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው።
30He must increase, but I must decrease.
32ያየውንና የሰማውንም ይህን ይመሰክራል፥ ምስክሩንም የሚቀበለው የለም።
31He that cometh from above is above all: he that is of the earth is of the earth, and of the earth he speaketh: he that cometh from heaven is above all.
33ምስክሩን የተቀበለ እግዚአብሔር እውነተኛ እንደ ሆነ አተመ።
32What he hath seen and heard, of that he beareth witness; and no man receiveth his witness.
34እግዚአብሔር የላከው የእግዚአብሔርን ቃል ይናገራልና፤ እግዚአብሔር መንፈሱን ሰፍሮ አይሰጥምና።
33He that hath received his witness hath set his seal to [this], that God is true.
35አባት ልጁን ይወዳል ሁሉንም በእጁ ሰጥቶታል።
34For he whom God hath sent speaketh the words of God: for he giveth not the Spirit by measure.
36በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም።
35The Father loveth the Son, and hath given all things into his hand.
36He that believeth on the Son hath eternal life; but he that obeyeth not the Son shall not see life, but the wrath of God abideth on him.