1በክንክራኦስ ባለች ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የምትሆን እኅታችንን ፌቤንን አደራ ብያችኋለሁ፤
1I commend unto you Phoebe our sister, who is a servant of the church that is at Cenchreae:
2ለቅዱሳን እንደሚገባ በጌታ ተቀበሉአት፥ እርስዋ ለብዙዎች ለእኔም ለራሴ ደጋፊ ነበረችና፥ ከእናንተም በምትፈልገው በማናቸውም ነገር እርዱአት።
2that ye receive her in the Lord, worthily of the saints, and that ye assist her in whatsoever matter she may have need of you: for she herself also hath been a helper of many, and of mine own self.
3በክርስቶስ ኢየሱስ አብረውኝ ለሚሠሩ ለጵርስቅላና ለአቂላ ሰላምታ አቅርቡልኝ፤
3Salute Prisca and Aquila my fellow-workers in Christ Jesus,
4እነርሱም ስለ ነፍሴ ነፍሳቸውን ለሞት አቀረቡ፥ የአሕዛብም አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ የሚያመሰግኑአቸው ናቸው እንጂ እኔ ብቻ አይደለሁም፤
4who for my life laid down their own necks; unto whom not only I give thanks, but also all the churches of the Gentiles:
5በቤታቸውም ላለች ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ አቅርቡልኝ። ከእስያ ለክርስቶስ በኵራት ለሆነው ለምወደው ለአጤኔጦን ሰላምታ አቅርቡልኝ።
5and [salute] the church that is in their house. Salute Epaenetus my beloved, who is the first-fruits of Asia unto Christ.
6ስለ እናንተ ብዙ ለደከመች ለማርያ ሰላምታ አቅርቡልኝ።
6Salute Mary, who bestowed much labor on you.
7በሐዋርያት መካከል ስመ ጥሩዎች ለሆኑ፥ ደግሞም ክርስቶስን በማመን ለቀደሙኝ፥ አብረውኝም ለታሰሩ ለዘመዶቼ ለአንዲራኒቆንና ለዩልያን ሰላምታ አቅርቡልኝ።
7Salute Andronicus and Junias, my kinsmen, and my fellow-prisoners, who are of note among the apostles, who also have been in Christ before me.
8በጌታ ለምወደው ለጵልያጦን ሰላምታ አቅርቡልኝ።
8Salute Ampliatus my beloved in the Lord.
9በክርስቶስ አብሮን ለሚሠራ ለኢሩባኖን ለምወደውም ለስንጣክን ሰላምታ አቅርቡልኝ።
9Salute Urbanus our fellow-worker in Christ, and Stachys my beloved.
10በክርስቶስ መሆኑ ተፈትኖ ለተመሰገነው ለኤጤሌን ሰላምታ አቅርቡልኝ። ከአርስጣባሉ ቤተ ሰዎች ላሉት ሰላምታ አቅርቡልኝ።
10Salute Apelles the approved in Christ. Salute them that are of the [household] of Aristobulus.
11ለዘመዴ ለሄሮድዮና ሰላምታ አቅርቡልኝ። ከንርቀሱ ቤተ ሰዎች በጌታ ላሉት ሰላምታ አቅርቡልኝ።
11Salute Herodion my kinsman. Salute them of the [household] of Narcissus, that are in the Lord.
12በጌታ ሆነው ለሚደክሙ ለፕሮፊሞናና ለጢሮፊሞሳ ሰላምታ አቅርቡልኝ። በጌታ እጅግ ለደከመች ለተወደደች ለጠርሲዳ ሰላምታ አቅርቡልኝ።
12Salute Tryphaena and Tryphosa, who labor in the Lord. Salute Persis the beloved, who labored much in the Lord.
13በጌታ ሆኖ ለታወቀ ለሩፎን ለእኔና ለእርሱም እናት ሰላምታ አቅርቡልኝ።
13Salute Rufus the chosen in the Lord, and his mother and mine.
14ለአስቀሪጦንና ለአፍለሶንጳ ለሄሮሜንም ለጳጥሮባም ለሄርማንም ከእነርሱም ጋር ላሉ ወንድሞች ሰላምታ አቅርቡልኝ።
14Salute Asyncritus, Phlegon, Hermes, Patrobas, Hermas, and the brethren that are with them.
15ለፍሌጎንና ለዩልያ ለኔርያና ለእኅቱም ለአልንጦንም ከእነርሱ ጋር ላሉ ቅዱሳን ሁሉ ሰላምታ አቅርቡልኝ።
15Salute Philologus and Julia, Nereus and his sister, and Olympas, and all the saints that are with them.
16በተቀደሰ አሳሳም እርስ በርሳችሁ ሰላምታ ተሰጣጡ። የክርስቶስ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።
16Salute one another with a holy kiss. All the churches of Christ salute you.
17ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ እናንተ የተማራችሁትን ትምህርት የሚቃወሙትን መለያየትንና ማሰናከያን የሚያደርጉትን ሰዎች እንድትመለከቱ እለምናችኋለሁ፥ ከእነርሱ ዘንድ ፈቀቅ በሉ፤
17Now I beseech you, brethren, mark them that are causing the divisions and occasions of stumbling, contrary to the doctrine which ye learned: and turn away from them.
18እንዲህ ያሉት ለገዛ ሆዳቸው እንጂ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ አይገዙምና፥ በመልካምና በሚያቆላምጥ ንግግርም ተንኮል የሌለባቸውን ሰዎች ልብ ያታልላሉ።
18For they that are such serve not our Lord Christ, but their own belly; and by their smooth and fair speech they beguile the hearts of the innocent.
19መታዘዛችሁ ለሁሉ ተወርቶአልና፤ እንግዲህ በእናንተ ደስ ይለኛል፤ ነገር ግን ለበጎ ነገር ጥበበኞች ለክፉም የዋሆች እንድትሆኑ እወዳለሁ።
19For your obedience is come abroad unto all men. I rejoice therefore over you: but I would have you wise unto that which is good, and simple unto that which is evil.
20የሰላምም አምላክ ሰይጣንን ከእግራችሁ በታች ፈጥኖ ይቀጠቅጠዋል። የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።
20And the God of peace shall bruise Satan under your feet shortly. The grace of our Lord Jesus Christ be with you.
21አብሮኝ የሚሠራ ጢሞቴዎስ ዘመዶቼም ሉቂዮስና ኢያሶን ሱሲጴጥሮስም ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።
21Timothy my fellow-worker saluteth you; and Lucius and Jason and Sosipater, my kinsmen.
22ይህን መልእክት የጻፍሁ እኔ ጤርጥዮስ በጌታ ሰላምታ አቀርብላችኋለሁ።
22I Tertius, who write the epistle, salute you in the Lord.
23የእኔና የቤተ ክርስቲያን ሁሉ አስተናጋጅ ጋይዮስ ሰላምታ ያቀርብላችኋል። የከተማው መጋቢ ኤርስጦስ ወንድማችንም ቁአስጥሮስ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።
23Gaius my host, and of the whole church, saluteth you. Erastus the treasurer of the city saluteth you, and Quartus the brother.
24የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን፤ አሜን።
24[The grace of our Lord Jesus Christ be with you all. Amen.]
25እንግዲህ እንደ ወንጌሌ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስም እንደ ተሰበከ፥ ከዘላለም ዘመንም የተሰወረው አሁን ግን የታየው በነቢያትም መጻሕፍት የዘላለም እግዚአብሔር እንደ አዘዘ ለእምነት መታዘዝ ይሆን ዘንድ ለአሕዛብ ሁሉ የታወቀው ምሥጢር እንደ ተገለጠ መጠን ሊያበረታችሁ ለሚችለው፥
25Now to him that is able to establish you according to my gospel and the preaching of Jesus Christ, according to the revelation of the mystery which hath been kept in silence through times eternal,
27ብቻውን ጥበብ ላለው ለእግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።
26but now is manifested, and by the scriptures of the prophets, according to the commandment of the eternal God, is made known unto all the nations unto obedience of faith:
27to the only wise God, through Jesus Christ, to whom be the glory for ever. Amen.