1በዚያም ዘመን ንጉሡ ሄሮድስ መከራ ያጸናባቸው ዘንድ ከቤተ ክርስቲያኑ በአንዳንዶቹ ላይ እጁን ጫነባቸው።
1At that time Herod the king laid his hands on some of those of the assembly to do them hurt,
2የዮሐንስንም ወንድም ያዕቆብን በሰይፍ ገደለው።
2and slew James, the brother of John, with the sword.
3አይሁድንም ደስ እንዳሰኛቸው አይቶ ጨምሮ ጴጥሮስን ደግሞ ያዘው። የቂጣ በዓልም ወራት ነበረ።
3And seeing that it was pleasing to the Jews, he went on to take Peter also: (and they were the days of unleavened bread:)
4በያዘውም ጊዜ ወደ ወኅኒ አገባው ከፋሲካም በኋላ ወደ ሕዝብ ያወጣው ዘንድ አስቦ እያንዳንዱ አራት ወታደሮች ሆነው እንዲጠብቁት ለአራት ጭፍራ ክፍል አሳልፎ ሰጠው።
4whom having seized he put in prison, having delivered him to four quaternions of soldiers to keep, purposing after the passover to bring him out to the people.
5ጴጥሮስም በወኅኒ ይጠበቅ ነበር፤ ነገር ግን በቤተ ክርስቲያን ስለ እርሱ ወደ እግዚአብሔር ጸሎት አጥብቆ ይደረግ ነበር።
5Peter therefore was kept in the prison; but unceasing prayer was made by the assembly to God concerning him.
6ሄሮድስም ሊያወጣው ባሰበ ጊዜ፥ በዚያች ሌሊት ጴጥሮስ በሁለት ሰንሰለት ታስሮ ከሁለት ወታደሮች መካከል ተኝቶ ነበር፤ ጠባቂዎችም በደጁ ፊት ሆነው ወኅኒውን ይጠብቁ ነበር።
6And when Herod was going to bring him forth, that night Peter was sleeping between two soldiers, bound with two chains, and guards before the door kept the prison.
7እነሆም፥ የጌታ መልአክ ቀረበ በቤትም ውስጥ ብርሃን በራ፤ ጴጥሮስንም ጎድኑን መትቶ አነቃውና። ፈጥነህ ተነሣ አለው። ሰንሰለቶቹም ከእጁ ወደቁ።
7And lo, an angel of [the] Lord came there, and a light shone in the prison: and having smitten the side of Peter, he roused him up, saying, Rise up quickly. And his chains fell off his hands.
8መልአኩም። ታጠቅና ጫማህን አግባ አለው፥ እንዲሁም አደረገ።
8And the angel said to him, Gird thyself, and bind on thy sandals. And he did so. And he says to him, Cast thine upper garment about thee and follow me.
9ልብስህንም ልበስና ተከተለኝ አለው። ወጥቶም ተከተለው፤ ራእይንም የሚያይ ይመስለው ነበር እንጂ በመልአኩ የሚደረገው ነገር እውነት እንደ ሆነ አላወቀም።
9And going forth he followed [him] and did not know that what was happening by means of the angel was real, but supposed he saw a vision.
10የመጀመሪያውንና የሁለተኛውንም ዘብ አልፈው ወደ ከተማ ወደሚያወጣው ወደ ብረቱ መዝጊያ ደረሱ፤ እርሱም አውቆ ተከፈተላቸው፤ ወጥተውም አንዲት ስላች አለፉ ወዲያውም መልአኩ ከእርሱ ተለየ።
10And having passed through a first and second guard, they came to the iron gate which leads into the city, which opened to them of itself; and going forth they went down one street, and immediately the angel left him.
11ጴጥሮስም ወደ ልቡ ተመልሶ። ጌታ መልአኩን ልኮ ከሄሮድስ እጅና የአይሁድ ሕዝብ ይጠብቁት ከነበረው ሁሉ እንደ አዳነኝ አሁን በእውነት አወቅሁ አለ።
11And Peter, being come to himself, said, Now I know certainly that [the] Lord has sent forth his angel and has taken me out of the hand of Herod and all the expectation of the people of the Jews.
12ባስተዋለም ጊዜ እጅግ ሰዎች ተከማችተው ይጸልዩበት ወደ ነበረው ማርቆስ ወደ ተባለው ወደ ዮሐንስ እናት ወደ ማርያም ቤት መጣ።
12And having become clearly conscious [in himself], he came to the house of Mary, the mother of John who was surnamed Mark, where were many gathered together and praying.
13ጴጥሮስም የደጁን መዝጊያ ባንኳኳ ጊዜ ሮዴ የሚሉአት አንዲት ገረድ ትሰማ ዘንድ ቀረበች፤
13And when he had knocked at the door of the entry, a maid came to listen, by name Rhoda;
14የጴጥሮስ ድምፅ መሆኑንም ባወቀች ጊዜ ከደስታዋ የተነሣ ደጁን አልከፈተችም፥ ነገር ግን ወደ ውስጥ ሮጣ ጴጥሮስ በደጅ ፊት ቆሞ እንዳለ አወራች።
14and having recognised the voice of Peter, through joy did not open the entry, but running in, reported that Peter was standing before the entry.
15እነርሱም። አብደሻል አሉአት። እርስዋ ግን እንዲሁ እንደ ሆነ ታስረግጥ ነበር። እነርሱም። መልአኩ ነው አሉ።
15And they said to her, Thou art mad. But she maintained that it was so. And they said, It is his angel.
16ጴጥሮስ ግን ማንኳኳቱን አዘወተረ፤ ከፍተውም አዩትና ተገረሙ።
16But Peter continued knocking: and having opened, they saw him and were astonished.
17ግን ዝም እንዲሉ በእጁ ጠቅሶ ጌታ ከወኅኒ እንዴት እንዳወጣው ተረከላቸውና። ይህን ለያዕቆብና ለወንድሞች ንገሩ አላቸው። ወጥቶም ወደ ሌላ ስፍራ ሄደ።
17And having made a sign to them with his hand to be silent, he related [to them] how the Lord had brought him out of prison; and he said, Report these things to James and to the brethren. And he went out and went to another place.
18በነጋም ጊዜ። ጴጥሮስን ምን አግኝቶት ይሆን? ብለው በጭፍሮች ዘንድ ብዙ ሁከት ሆነ።
18And when it was day there was no small disturbance among the soldiers, what then was become of Peter.
19ሄሮድስም አስፈልጎ ባጣው ጊዜ ጠባቂዎችን መረመረ ይገድሉአቸውም ዘንድ አዘዘ፤ ከይሁዳም ወደ ቂሣርያ ወርዶ በዚያ ተቀመጠ።
19And Herod having sought him and not found him, having examined the guards, commanded [them] to be executed. And he went down from Judaea to Caesarea and stayed [there].
20ከጢሮስና ከሲዶና ሰዎችም ጋር ተጣልቶ ነበር፤ በአንድ ልብ ሆነውም ወደ እርሱ መጡ፥ የንጉሥንም ቢትወደድ ብላስጦስን እሺ አሰኝተው ዕርቅ ለመኑ፥ አገራቸው ከንጉሥ አገር ምግብ ያገኝ ነበረና።
20And he was in bitter hostility with [the] Tyrians and Sidonians; but they came to him with one accord, and, having gained Blastus the king's chamberlain, sought peace, because their country was nourished by the king's.
21በተቀጠረ ቀንም ሄሮድስ ልብሰ መንግሥቱን ለብሶ በዙፋን ተቀመጠ እነርሱንም ተናገራቸው፤
21And on a set day, clothed in royal apparel and sitting on the elevated seat [of honour], Herod made a public oration to them.
22ሕዝቡም። የእግዚአብሔር ድምፅ ነው የሰውም አይደለም ብለው ጮኹ።
22And the people cried out, A god's voice and not a man's.
23ለእግዚአብሔርም ክብር ስላልሰጠ ያን ጊዜ የጌታ መልአክ መታው በትልም ተበልቶ ሞተ።
23And immediately an angel of [the] Lord smote him, because he did not give the glory to God, and he expired, eaten of worms.
24የእግዚአብሔር ቃል ግን ያድግና ይበዛ ነበር።
24But the word of God grew and spread itself.
25በርናባስና ሳውልም አገልግሎታቸውን ፈጽመው ከኢየሩሳሌም ተመለሱ፥ ማርቆስ የተባለውን ዮሐንስንም ከእነርሱ ጋር ይዘውት መጡ።
25And Barnabas and Saul returned from Jerusalem, having fulfilled the service [entrusted to them], taking also with them John, surnamed Mark.