1የእግዚአብሔርና የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ያዕቆብ ለተበተኑ ለአሥራ ሁለቱ ወገኖች፤ ሰላም ለእናንተ ይሁን።
1James, bondman of God and of [the] Lord Jesus Christ, to the twelve tribes which [are] in the dispersion, greeting.
2ወንድሞቼ ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት
2Count it all joy, my brethren, when ye fall into various temptations,
4ትዕግሥትም ምንም የሚጎድላችሁ ሳይኖር ፍጹማንና ምሉዓን ትሆኑ ዘንድ ሥራውን ይፈጽም።
3knowing that the proving of your faith works endurance.
5ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፥ ለእርሱም ይሰጠዋል።
4But let endurance have [its] perfect work, that ye may be perfect and complete, lacking in nothing.
6ነገር ግን በምንም ሳይጠራጠር በእምነት ይለምን፤ የሚጠራጠር ሰው በነፋስ የተገፋና የተነቃነቀ የባሕርን ማዕበል ይመስላልና።
5But if any one of you lack wisdom, let him ask of God, who gives to all freely and reproaches not, and it shall be given to him:
7ሁለት አሳብ ላለው በመንገዱም ሁሉ ለሚወላውል ለዚያ ሰው ከጌታ ዘንድ አንዳች እንዲያገኝ አይምሰለው።
6but let him ask in faith, nothing doubting. For he that doubts is like a wave of the sea driven by the wind and tossed about;
9የተዋረደው ወንድም ግን በከፍታው፥ ባለ ጠጋም በውርደቱ ይመካ፤ እንደ ሣር አበባ ያልፋልና።
7for let not that man think that he shall receive anything from the Lord;
11ፀሐይ ከትኵሳት ጋር ይወጣልና፥ ሣርንም ያጠወልጋልና፥ አበባውም ይረግፋልና፥ የመልኩም ውበት ይጠፋልና፤ እንዲሁ ደግሞ ባለ ጠጋው በመንገዱ ይዝላል።
8[he is] a double-minded man, unstable in all his ways.
12በፈተና የሚጸና ሰው የተባረከ ነው፤ ከተፈተነ በኋላ ለሚወዱት ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን የሕይወትን አክሊል ይቀበላልና።
9But let the brother of low degree glory in his elevation,
13ማንም ሲፈተን። በእግዚአብሔር እፈተናለሁ አይበል፤ እግዚአብሔር በክፉ አይፈተንምና፤ እርሱ ራሱስ ማንንም አይፈትንም።
10and the rich in his humiliation, because as [the] grass's flower he will pass away.
14ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ይፈተናል።
11For the sun has risen with its burning heat, and has withered the grass, and its flower has fallen, and the comeliness of its look has perished: thus the rich also shall wither in his goings.
15ከዚህ በኋላ ምኞት ፀንሳ ኃጢአትን ትወልዳለች፤ ኃጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች።
12Blessed [is the] man who endures temptation; for, having been proved, he shall receive the crown of life, which He has promised to them that love him.
16የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ አትሳቱ።
13Let no man, being tempted, say, I am tempted of God. For God cannot be tempted by evil things, and himself tempts no one.
17በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፥ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ።
14But every one is tempted, drawn away, and enticed by his own lust;
18ለፍጥረቱ የበኵራት ዓይነት እንድንሆን በእውነት ቃል አስቦ ወለደን።
15then lust, having conceived, gives birth to sin; but sin fully completed brings forth death.
19ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤
16Do not err, my beloved brethren.
20የሰው ቍጣ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አይሠራምና።
17Every good gift and every perfect gift comes down from above, from the Father of lights, with whom is no variation nor shadow of turning.
21ስለዚህ ርኵሰትን ሁሉ የክፋትንም ትርፍ አስወግዳችሁ፥ ነፍሳችሁን ማዳን የሚችለውን በውስጣችሁም የተተከለውን ቃል በየዋህነት ተቀበሉ።
18According to his own will begat he us by the word of truth, that we should be a certain first-fruits of *his* creatures.
22ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ።
19So that, my beloved brethren, let every man be swift to hear, slow to speak, slow to wrath;
23ቃሉን የሚሰማ የማያደርገውም ቢኖር የተፈጥሮ ፊቱን በመስተዋት የሚያይን ሰው ይመስላል፤
20for man's wrath does not work God's righteousness.
24ራሱን አይቶ ይሄዳልና፥ ወዲያውም እንደ ምን እንደ ሆነ ይረሳል።
21Wherefore, laying aside all filthiness and abounding of wickedness, accept with meekness the implanted word, which is able to save your souls.
25ነገር ግን ነጻ የሚያወጣውን ፍጹሙን ሕግ ተመልክቶ የሚጸናበት፥ ሥራንም የሚሠራ እንጂ ሰምቶ የሚረሳ ያልሆነው፥ በሥራው የተባረከ ይሆናል።
22But be ye doers of [the] word and not hearers only, beguiling yourselves.
26አንደበቱን ሳይገታ ልቡን እያሳተ እግዚአብሔርን የሚያመልክ የሚመስለው ማንም ቢኖር የእርሱ አምልኮ ከንቱ ነው።
23For if any man be a hearer of [the] word and not a doer, *he* is like to a man considering his natural face in a mirror:
27ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው፤ ወላጆች የሌላቸውን ልጆች ባልቴቶችንም በመከራቸው መጠየቅ፥ በዓለምም ከሚገኝ እድፍ ሰውነቱን መጠበቅ ነው።
24for he has considered himself and is gone away, and straightway he has forgotten what he was like.
25But *he* that fixes his view on [the] perfect law, that of liberty, and abides in [it], being not a forgetful hearer but a doer of [the] work, *he* shall be blessed in his doing.
26If any one think himself to be religious, not bridling his tongue, but deceiving his heart, this man's religion is vain.
27Pure and undefiled religion before God and the Father is this: to visit orphans and widows in their affliction, to keep oneself unspotted from the world.