1ኢየሱስም ይህን ብሎ አትክልት ወዳለበት ስፍራ ወደ ቄድሮን ወንዝ ማዶ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወጣ፤ እርሱም ደቀ መዛሙርቱም በዚያ ገቡ።
1Jesus, having said these things, went out with his disciples beyond the torrent Cedron, where was a garden, into which he entered, he and his disciples.
2ኢየሱስም ደቀ መዛሙርቱም ብዙ ጊዜ ወደዚያ ስለ ተሰበሰቡ አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ ደግሞ ስፍራውን ያውቅ ነበር።
2And Judas also, who delivered him up, knew the place, because Jesus was often there, in company with his disciples.
3ስለዚህ ይሁዳ ጭፍሮችንና ከካህናት አለቆች ከፈሪሳውያንም ሎሌዎችን ተቀብሎ በችቦና በፋና በጋሻ ጦርም ወደዚያ መጣ።
3Judas therefore, having got the band, and officers of the chief priests and Pharisees, comes there with lanterns and torches and weapons.
4ኢየሱስም የሚመጣበትን ሁሉ አውቆ ወጣና። ማንን ትፈልጋላችሁ አላቸው።
4Jesus therefore, knowing all things that were coming upon him, went forth and said to them, Whom seek ye?
5የናዝሬቱን ኢየሱስን ብለው መለሱለት። ኢየሱስ። እኔ ነኝ አላቸው። አሳልፎ የሰጠውም ይሁዳ ደግሞ ከእነርሱ ጋር ቆሞ ነበር።
5They answered him, Jesus the Nazaraean. Jesus says to them, I am [he]. And Judas also, who delivered him up, stood with them.
6እንግዲህ። እኔ ነኝ ባላቸው ጊዜ ወደ ኋላ አፈግፍገው በምድር ወደቁ።
6When therefore he said to them, I am [he], they went away backward and fell to the ground.
7ደግሞም። ማንን ትፈልጋላችሁ? ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም። የናዝሬቱን ኢየሱስን አሉት።
7He demanded of them therefore again, Whom seek ye? And they said, Jesus the Nazaraean.
8ኢየሱስ መልሶ። እኔ ነኝ አልኋችሁ፤ እንግዲህ እኔን ትፈልጉ እንደ ሆናችሁ እነዚህ ይሂዱ ተዉአቸው አለ፤
8Jesus answered, I told you that I am [he]: if therefore ye seek me, let these go away;
9ይህም። ከእነዚህ ከሰጠኸኝ አንዱን ስንኳ አላጠፋሁም ያለው ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው።
9that the word might be fulfilled which he spoke, [As to] those whom thou hast given me, I have not lost one of them.
10ስምዖን ጴጥሮስም ሰይፍ ስለ ነበረው መዘዘው፥ የሊቀ ካህናቱንም ባርያ መትቶ ቀኝ ጆሮውን ቈረጠ፤ የባርያውም ስም ማልኮስ ነበረ።
10Simon Peter therefore, having a sword, drew it, and smote the bondman of the high priest and cut off his right ear; and the bondman's name was Malchus.
11ኢየሱስም ጴጥሮስን። ሰይፍህን ወደ ሰገባው ክተተው፤ አብ የሰጠኝን ጽዋ አልጠጣትምን? አለው።
11Jesus therefore said to Peter, Put the sword into the sheath; the cup which the Father has given me, shall I not drink it?
12እንግዲህ የሻለቃውና ጭፍሮቹ የአይሁድም ሎሌዎች ኢየሱስን ይዘው አሰሩት፥
12The band therefore, and the chiliarch, and the officers of the Jews, took Jesus and bound him:
13አስቀድመውም ወደ ሐና ወሰዱት፤ በዚያች ዓመት ሊቀ ካህናት ለነበረው ለቀያፋ አማቱ ነበርና።
13and they led him away to Annas first; for he was father-in-law to Caiaphas, who was high priest that year.
14ቀያፋም። አንድ ሰው ስለ ሕዝብ ይሞት ዘንድ ይሻላል ብሎ ለአይሁድ የመከራቸው ነበረ።
14But it was Caiaphas who counselled the Jews that it was better that one man should perish for the people.
15ስምዖን ጴጥሮስም ሌላውም ደቀ መዝሙር ኢየሱስን ተከተሉ። ያም ደቀ መዝሙር በሊቀ ካህናቱ ዘንድ የታወቀ ነበረ፥ ወደ ሊቀ ካህናቱም ግቢ ከኢየሱስ ጋር ገባ፤
15Now Simon Peter followed Jesus, and the other disciple. But that disciple was known to the high priest, and went in with Jesus into the palace of the high priest;
16ጴጥሮስ ግን በውጭ በበሩ ቆሞ ነበር። እንግዲህ በሊቀ ካህናቱ ዘንድ የታወቀው ሌላው ደቀ መዝሙር ወጣ ለበረኛይቱም ነግሮ ጴጥሮስን አስገባው።
16but Peter stood at the door without. The other disciple therefore, who was known to the high priest, went out and spoke to the porteress and brought in Peter.
17በረኛ የነበረችይቱም ገረድ ጴጥሮስን። አንተ ደግሞ ከዚህ ሰው ደቀ መዛሙርት አንዱ አይደለህምን? አለችው። እርሱ። አይደለሁም አለ።
17The maid therefore, who was porteress, says to Peter, Art thou also of the disciples of this man? He says, I am not.
18ብርድ ነበረና ባሮችና ሎሌዎች የፍም እሳት አንድደው ቆሙ ይሞቁም ነበር፤ ጴጥሮስም ደግሞ ከእነርሱ ጋር ቆሞ ይሞቅ ነበር።
18But the bondmen and officers, having made a fire of coals (for it was cold), stood and warmed themselves; and Peter was standing with them and warming himself.
19ሊቀ ካህናቱም ኢየሱስን ስለ ደቀ መዛሙርቱና ስለ ትምህርቱ ጠየቀው።
19The high priest therefore demanded of Jesus concerning his disciples and concerning his doctrine.
20ኢየስስም መልሶ። እኔ በግልጥ ለዓለም ተናገርሁ፤ አይሁድ ሁሉ በሚሰበሰቡበት በምኵራብና በመቅደስ እኔ ሁልጊዜ አስተማርሁ፥ በስውርም ምንም አልተናገርሁም።
20Jesus answered him, I spoke openly to the world; I taught always in [the] synagogue and in the temple, where all the Jews come together, and in secret I have spoken nothing.
21ስለምን ትጠይቀኛለህ? ለእነርሱ የተናገርሁትን የሰሙትን ጠይቅ፤ እነሆ፥ እነዚህ እኔ የነገርሁትን ያውቃሉ አለው።
21Why demandest thou of me? Demand of those who have heard, what I have spoken to them; behold, they know what I have said.
22ይህንም ሲል በዚያ ቆሞ የነበረው ከሎሌዎች አንዱ። ለሊቀ ካህናቱ እንዲህ ትመልሳለህን? ብሎ ኢየሱስን በጥፊ መታው።
22But as he said these things, one of the officers who stood by gave a blow on the face to Jesus, saying, Answerest thou the high priest thus?
23ኢየሱስም መልሶ። ክፉ ተናግሬ እንደ ሆንሁ ስለ ክፉ መስክር፤ መልካም ተናግሬ እንደ ሆንሁ ግን ሰለ ምን ትመታኛለህ? አለው።
23Jesus answered him, If I have spoken evil, bear witness of the evil; but if well, why smitest thou me?
24ስለዚህ ሐና እንደ ታሰረ ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ቀያፋ ሰደደው።
24Annas [then] had sent him bound to Caiaphas the high priest.
25ስምዖን ጴጥሮስም ቆሞ እሳት ይሞቅ ነበር። እንግዲህ። አንተ ደግሞ ከደቀ መዛሙርቱ አይደለህምን? አሉት። እርሱም። አይደለሁም ብሎ ካደ።
25But Simon Peter was standing and warming himself. They said therefore to him, Art thou also of his disciples? He denied, and said, I am not.
26ጴጥሮስ ጆሮውን የቈረጠው ዘመድ የሆነ ከሊቀ ካህናቱ ባሮች አንዱ። በአትክልቱ ከእርሱ ጋር እኔ አይቼህ አልነበረምን? አለው።
26One of the bondmen of the high priest, who was kinsman of him whose ear Peter cut off, says, Did not I see thee in the garden with him?
27ጴጥሮስም እንደ ገና ካደ፥ ወዲያውም ዶሮ ጮኸ።
27Peter denied therefore again, and immediately [the] cock crew.
28ኢየሱስንም ከቀያፋ ወደ ገዡ ግቢ ወሰዱት፤ ማለዳም ነበረ፤ እነርሱም የፋሲካ በግ ይበሉ ዘንድ እንጂ እንዳይረክሱ ወደ ገዡ ግቢ አልገቡም።
28They lead therefore Jesus from Caiaphas to the praetorium; and it was early morn. And *they* entered not into the praetorium, that they might not be defiled, but eat the passover.
29ስለዚህ ጲላጦስ ወደ ውጭ ወደ እነርሱ ወጥቶ። ይህን ሰው ስለ ምን ትከሱታላችሁ አላቸው።
29Pilate therefore went out to them and said, What accusation do ye bring against this man?
30እነርሱም መልሰው። ይህስ ክፉ አድራጊ ባይሆን ወደ አንተ አሳልፈን ባልሰጠነውም ነበር አሉት።
30They answered and said to him, If this [man] were not an evildoer, we should not have delivered him up to thee.
31ጲላጦስም። እናንተ ወስዳችሁ እንደ ሕጋችሁ ፍረዱበት አላቸው። አይሁድም። ለእኛስ ማንንም ልንገድል አልተፈቀደልንም አሉት፤
31Pilate therefore said to them, Take him, ye, and judge him according to your law. The Jews therefore said to him, It is not permitted to us to put any one to death;
32ኢየሱስ በምን ዓይነት ሞት ሊሞት እንዳለው ሲያመለክት የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው።
32that the word of Jesus might be fulfilled which he spoke, signifying what death he should die.
33ጲላጦስም እንደ ገና ወደ ገዡ ግቢ ገባና ኢየሱስን ጠርቶ። የአይሁድ ንጉሥ አንተ ነህን? አለው።
33Pilate therefore entered again into the praetorium and called Jesus, and said to him, Thou art the king of the Jews?
34ኢየሱስም መልሶ። አንተ ይህን የምትለው ከራስህ ነውን ወይስ ሌሎች ስለ እኔ ነገሩህን? አለው።
34Jesus answered [him], Dost thou say this of thyself, or have others said it to thee concerning me?
35ጲላጦስ መልሶ። እኔ አይሁዳዊ ነኝን? ወገኖችህና የካህናት አለቆች ለእኔ አሳልፈው ሰጡህ፤ ምን አድርገሃል? አለው።
35Pilate answered, Am I a Jew? Thy nation and the chief priests have delivered thee up to me: what hast thou done?
36ኢየሱስም መልሶ። መንግሥቴ ከዚህ ዓለም አይደለችም፤ መንግሥቴስ ከዚህ ዓለም ብትሆን፥ ወደ አይሁድ እንዳልሰጥ ሎሌዎቼ ይዋጉልኝ ነበር፤ አሁን ግን መንግሥቴ ከዚህ አይደለችም አለው።
36Jesus answered, My kingdom is not of this world; if my kingdom were of this world, my servants had fought that I might not be delivered up to the Jews; but now my kingdom is not from hence.
37ጲላጦስም። እንግዲያ ንጉሥ ነህን? አለው። ኢየሱስም መልሶ። እኔ ንጉሥ እንደ ሆንሁ አንተ ትላለህ። እኔ ለእውነት ልመሰክር ስለዚህ ተወልጃለሁ ስለዚህም ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤ ከእውነት የሆነ ሁሉ ድምፄን ይሰማል አለው።
37Pilate therefore said to him, Thou art then a king? Jesus answered, Thou sayest [it], that I am a king. I have been born for this, and for this I have come into the world, that I might bear witness to the truth. Every one that is of the truth hears my voice.
38ጲላጦስ። እውነት ምንድር ነው? አለው። ይህንም ብሎ ዳግመኛ ወደ አይሁድ ወጥቶ። እኔስ አንዲት በደል ስንኳ አላገኘሁበትም።
38Pilate says to him, What is truth? And having said this he went out again to the Jews, and says to them, I find no fault whatever in him.
39ነገር ግን በፋሲካ አንድ ልፈታላችሁ ልማድ አላችሁ፤ እንግዲህ የአይሁድን ንጉሥ ልፈታላችሁ ትወዳላችሁን? አላቸው።
39But ye have a custom that I release [some] one to you at the passover; will ye therefore that I release unto you the king of the Jews?
40ሁሉም ደግመው። በርባንን እንጂ ይህን አይደለም እያሉ ጮኹ። በርባን ግን ወንበዴ ነበረ።
40They cried therefore again all, saying, Not this [man], but Barabbas. Now Barabbas was a robber.