Amharic: New Testament

Darby's Translation

John

2

1በሦስተኛውም ቀን በገሊላ ቃና ሰርግ ነበረ፥ የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች፤
1And on the third day a marriage took place in Cana of Galilee, and the mother of Jesus was there.
2ኢየሱስም ደግሞ ደቀ መዛሙርቱም ወደ ሰርጉ ታደሙ።
2And Jesus also, and his disciples, were invited to the marriage.
3የወይን ጠጅም ባለቀ ጊዜ የኢየሱስ እናት። የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም አለችው።
3And wine being deficient, the mother of Jesus says to him, They have no wine.
4ኢየሱስም። አንቺ ሴት፥ ከአንቺ ጋር ምን አለኝ? ጊዜዬ ገና አልደረሰም አላት።
4Jesus says to her, What have I to do with thee, woman? mine hour has not yet come.
5እናቱም ለአገልጋዮቹ። የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ አለቻቸው።
5His mother says to the servants, Whatever he may say to you, do.
6አይሁድም እንደሚያደርጉት የማንጻት ልማድ ስድስት የድንጋይ ጋኖች በዚያ ተቀምጠው ነበር፥ እያንዳንዳቸውም ሁለት ወይም ሦስት እንስራ ይይዙ ነበር።
6Now there were standing there six stone water-vessels, according to the purification of the Jews, holding two or three measures each.
7ኢየሱስም። ጋኖቹን ውኃ ሙሉአቸው አላቸው። እስከ አፋቸውም ሙሉአቸው አላቸው። እስከ አፋቸውም ሞሉአቸው።
7Jesus says to them, Fill the water-vessels with water. And they filled them up to the brim.
8አሁን ቀድታችሁ ለአሳዳሪው ስጡት አላቸው፤ ሰጡትም።
8And he says to them, Draw out now, and carry [it] to the feast-master. And they carried [it].
9አሳዳሪውም የወይን ጠጅ የሆነውን ውሃ በቀመሰ ጊዜ ከወዴት እንደ መጣ አላወቀም፤ ውኃውን የቀዱት አገልጋዮች ግን ያውቁ ነበር፤ አሳዳሪው ሙሽራውን ጠርቶ።
9But when the feast-master had tasted the water which had been made wine (and knew not whence it was, but the servants knew who drew the water), the feast-master calls the bridegroom,
10ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል፥ ከሰከሩም በኋላ መናኛውን፤ አንተስ መልካሙን የወይን ጠጅ እስከ አሁን አቆይተሃል አለው።
10and says to him, Every man sets on first the good wine, and when [men] have well drunk, then the inferior; thou hast kept the good wine till now.
11ኢየሱስ ይህን የምልክቶች መጀመሪያ በገሊላ ቃና አደረገ፤ ክብሩንም ገለጠ፥ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ።
11This beginning of signs did Jesus in Cana of Galilee, and manifested his glory; and his disciples believed on him.
12ከዚህ በኋላ ከእናቱና ከወንድሞቹ ከደቀ መዛሙርቱም ጋር ወደ ቅፍርናሆም ወረደ፥ በዚያም ጥቂት ቀን ኖሩ።
12After this he descended to Capernaum, he and his mother and his brethren and his disciples; and there they abode not many days.
13የአይሁድ ፋሲካም ቀርቦ ነበር፥ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ።
13And the passover of the Jews was near, and Jesus went up to Jerusalem.
14በመቅደስም በሬዎችንና በጎችን ርግቦችንም የሚሸጡትን ገንዘብ ለዋጮችንም ተቀምጠው አገኘ፤
14And he found in the temple the sellers of oxen and sheep and doves, and the money-changers sitting;
15የገመድም ጅራፍ አበጅቶ ሁሉን በጎችንም በሬዎችንም ከመቅደስ አወጣቸው፥ የለዋጮችንም ገንዘብ አፈሰሰ ገበታዎቻቸውንም ገለበጠ፥
15and, having made a scourge of cords, he cast [them] all out of the temple, both the sheep and the oxen; and he poured out the change of the money-changers, and overturned the tables,
16ርግብ ሻጪዎችንም። ይህን ከዚህ ውሰዱ፤ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት አላቸው።
16and said to the sellers of doves, Take these things hence; make not my Father's house a house of merchandise.
17ደቀ መዛሙርቱም። የቤትህ ቅናት ይበላኛል ተብሎ እንደ ተጻፈ አሰቡ።
17[And] his disciples remembered that it is written, The zeal of thy house devours me.
18ስለዚህ አይሁድ መልሰው። ይህን ስለምታደርግ ምን ምልክት ታሳየናለህ? አሉት።
18The Jews therefore answered and said to him, What sign shewest thou to us, that thou doest these things?
19ኢየሱስም መልሶ። ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት፥ በሦስት ቀንም አነሣዋለሁ አላቸው።
19Jesus answered and said to them, Destroy this temple, and in three days I will raise it up.
20ስለዚህ አይሁድ። ይህ ቤተ መቅደስ ከአርባ ስድስት ዓመት ጀምሮ ይሠራ ነበር፥ አንተስ በሦስት ቀን ታነሣዋለህን? አሉት።
20The Jews therefore said, Forty and six years was this temple building, and thou wilt raise it up in three days?
21እርሱ ግን ስለ ሰውነቱ ቤተ መቅደስ ይል ነበር።
21But *he* spoke of the temple of his body.
22ስለዚህ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ይህን እንደ ተናገረ አሰቡና መጽሐፍንና ኢየሱስ የተናገረውን ቃል አመኑ።
22When therefore he was raised from among [the] dead, his disciples remembered that he had said this, and believed the scripture and the word which Jesus had spoken.
23በፋሲካ በዓልም በኢየሩሳሌም ሳለ፥ ያደረገውን ምልክት ባዩ ጊዜ ብዙ ሰዎች በስሙ አመኑ፤
23And when he was in Jerusalem, at the passover, at the feast, many believed on his name, beholding his signs which he wrought.
24ነገር ግን ኢየሱስ ሰዎችን ሁሉ ያውቅ ነበር፤ ስለ ሰውም ማንም ሊመሰክር አያስፈልገውም ነበርና አይተማመናቸውም ነበር፤ ራሱ በሰው ያለውን ያውቅ ነበርና።
24But Jesus himself did not trust himself to them, because he knew all [men],
25and that he had not need that any should testify of man, for himself knew what was in man.