Amharic: New Testament

Darby's Translation

Mark

13

1እርሱም ከመቅደስ ሲወጣ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ። መምህር ሆይ፥ እንዴት ያሉ ድንጋይዎችና እንዴት ያሉ ሕንጻዎች እንደ ሆኑ እይ አለው።
1And as he was going out of the temple, one of his disciples says to him, Teacher, see what stones and what buildings!
2ኢየሱስም መልሶ። እነዚህን ታላላቅ ሕንጻዎች ታያለህን? ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም አለው።
2And Jesus answering said to him, Seest thou these great buildings? not a stone shall be left upon a stone, which shall not be thrown down.
3በመቅደስም ትይዩ በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ጴጥሮስና ያዕቆብ ዮሐንስም እንድርያስም።
3And as he sat on the mount of Olives opposite the temple, Peter and James and John and Andrew asked him privately,
4ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል? ይህስ ሁሉ ይፈጸም ዘንድ እንዳለው ምልክቱ ምንድር ነው? ብለው ለብቻቸው ጠየቁት።
4Tell us, when shall these things be, and what is the sign when all these things are going to be fulfilled?
5ኢየሱስም መልሶ እንዲህ ይላቸው ጀመር። ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ።
5And Jesus answering them began to say, Take heed lest any one mislead you.
6ብዙዎች። እኔ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፥ ብዙዎችንም ያስታሉ።
6For many shall come in my name, saying, It is *I*, and shall mislead many.
7ጦርንም የጦርንም ወሬ በሰማችሁ ጊዜ አትደንግጡ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና፥ ነገር ግን መጨረሻው ገና ነው።
7But when ye shall hear of wars and rumours of wars, be not disturbed, for [this] must happen, but the end is not yet.
8ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፤ በልዩ ልዩ ስፍራ የምድር መናወጥ ይሆናል፤ ራብ ይሆናል፤ እነዚህ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው።
8For nation shall rise up against nation, and kingdom against kingdom; and there shall be earthquakes in [different] places, and there shall be famines and troubles: these things [are the] beginnings of throes.
9እናንተ ግን ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤ ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል በምኵራብም ትገረፋላችሁ ምስክርም ይሆንባቸው ዘንድ ስለ እኔ በገዥዎችና በነገሥታት ፊት ትቆማላችሁ።
9But *ye*, take heed to yourselves, for they shall deliver you up to sanhedrims and to synagogues: ye shall be beaten and brought before rulers and kings for my sake, for a testimony to them;
10አስቀድሞም ወንጌል ለአሕዛብ ሁሉ ይሰበክ ዘንድ ይገባል።
10and the gospel must first be preached to all the nations.
11ሲጐትቱአችሁና አሳልፈው ሲሰጡአችሁም ምን እንድትናገሩ አስቀድማችሁ አትጨነቁ፥ ዳሩ ግን በዚያች ሰዓት የሚሰጣችሁን ተናገሩ፤ የሚነግረው መንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ እናንተ አይደላችሁምና።
11But when they shall lead you away to deliver you up, be not careful beforehand as to what ye shall say, [nor prepare your discourse]: but whatsoever shall be given you in that hour, that speak; for *ye* are not the speakers, but the Holy Spirit.
12ወንድምም ወንድሙን አባትም ልጁን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፥ ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ ይነሣሉ። ይገድሉአቸውማል፤
12But brother shall deliver up brother to death, and father child; and children shall rise up against parents, and cause them to be put to death.
13በሁሉም ዘንድ ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።
13And ye will be hated of all on account of my name; but he that has endured to the end, *he* shall be saved.
14ነገር ግን በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋት ርኵሰት በማይገባው ስፍራ ቆሞ ብታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፥ በዚያን ጊዜ በይሁዳ ያሉ ወደ ተራሮች ይሽሹ፥
14But when ye shall see the abomination of desolation standing where it should not, (he that reads let him consider [it],) then let those in Judaea flee to the mountains;
15በሰገነትም ያለ ወደ ቤት አይውረድ ከቤቱም አንዳች ይወስድ ዘንድ አይግባ፥
15and him that is upon the housetop not come down into the house, nor enter [into it] to take away anything out of his house;
16በእርሻም ያለ ልብሱን ይወስድ ዘንድ ወደ ኋላው አይመለስ።
16and him that is in the field not return back to take his garment.
17በዚያን ወራትም ለርጉዞችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው።
17But woe to those that are with child and to those that give suck in those days!
18ነገር ግን ሽሽታችሁ በክረምት እንዳይሆን ጸልዩ፤
18And pray that it may not be in winter time;
19በዚያን ወራት እግዚአብሔር ከፈጠረው ከፍጥረት መጀመሪያ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ያልሆነ ደግሞም የማይሆን የመከራ ዓይነት ይሆናልና።
19for those days shall be distress such as there has not been the like since [the] beginning of creation which God created, until now, and never shall be;
20ጌታስ ወራቶቹን ባያሳጥር፥ ሥጋ የለበሰ ሁሉ ባልዳነም፤ ነገር ግን ስለ መረጣቸው ምርጦች ወራቶቹን አሳጠረ።
20and if [the] Lord had not cut short those days, no flesh should have been saved; but on account of the elect whom he has chosen, he has cut short those days.
21በዚያን ጊዜም ማንም። እነሆ፥ ክርስቶስ ከዚህ አለ፥ ወይም። እነሆ፥ ከዚያ አለ ቢላችሁ አትመኑ፤
21And then if any one say to you, Lo, here [is] the Christ, or Lo, there, believe [it] not.
22ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፥ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ ያስቱ ዘንድ ምልክትና ድንቅ ያደርጋሉ።
22For false Christs and false prophets will arise, and give signs and wonders to deceive, if possible, even the elect.
23እናንተ ግን ተጠንቀቁ፤ እነሆ፥ አስቀድሜ ሁሉን ነገርኋችሁ።
23But do *ye* take heed: behold, I have told you all things beforehand.
24በዚያን ወራት ግን ከዚያ መከራ በኋላ ፀሐይ ይጨልማል ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፥
24But in those days, after that distress, the sun shall be darkened and the moon shall not give its light;
25ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፥ የሰማያትም ኃይላት ይናወጣሉ።
25and the stars of heaven shall be falling down, and the powers which are in the heavens shall be shaken;
26በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ በብዙ ኃይልና ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል።
26and then shall they see the Son of man coming in clouds with great power and glory;
27በዚያን ጊዜም መላእክትን ይልካል ከአራቱ ነፋሳትም ከምድር ዳርቻ እስከ ሰማይ ዳርቻ የተመረጡትን ይሰበስባቸዋል።
27and then shall he send his angels and shall gather together his elect from the four winds, from end of earth to end of heaven.
28ምሳሌውንም ከበለስ ተማሩ፤ ጫፍዋ ሲለሰልስ ቅጠልዋም ሲያቈጠቍጥ፥ ያን ጊዜ በጋ እንደ ቀረበ ታውቃላችሁ፤
28But learn the parable from the fig-tree: when its branch already becomes tender and puts forth the leaves, ye know that the summer is near.
29እንዲሁ ደግሞ እናንተ ይህን ሁሉ መሆኑን ስታዩ ቀርቦ በደጅ እንደ ሆነ እወቁ።
29Thus also *ye*, when ye see these things happening, know that it is near, at the doors.
30እውነት እላችኋለሁ፥ ይህ ሁሉ እስኪሆን ድረስ ይህ ትውልድ አያልፍም።
30Verily I say unto you, This generation shall in no wise pass away, till all these things take place.
31ሰማይና ምድር ያልፋሉ ቃሌ ግን አያልፍም።
31The heaven and the earth shall pass away, but my words shall in no wise pass away.
32ስለዚያች ቀን ወይም ስለዚያች ሰዓት ግን የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን ከአባት በቀር የሚያውቅ የለም።
32But of that day or of that hour no one knows, neither the angels who are in heaven, nor the Son, but the Father.
33ጊዜው መቼ እንዲሆን አታውቁምና ተጠንቀቁ፤ ትጉ፤ ጸልዩም።
33Take heed, watch and pray, for ye do not know when the time is:
34ቤቱን ትቶ ወደ ሌላ አገር እንደ ሄደ ሰው ነው፥ ለባሮቹም ሥልጣን ለእያንዳንዱም ሥራውን ሰጥቶ በረኛውን እንዲተጋ አዘዘ።
34[it is] as a man gone out of the country, having left his house and given to his bondmen the authority, and to each one his work, and commanded the doorkeeper that he should watch.
35እንግዲህ በማታ ቢሆን ወይም በእኩለ ሌሊት ወይም ዶሮ ሲጮኽ ወይም በማለዳ ቢሆን ባለቤቱ መቼ እንዲመጣ አታውቁምና
35Watch therefore, for ye do not know when the master of the house comes: evening, or midnight, or cock-crow, or morning;
36ድንገት መጥቶ ተኝታችሁ እንዳያገኛችሁ ስለዚህ ትጉ።
36lest coming suddenly he find you sleeping.
37ለእናንተም የምነግራችሁ ለሁሉ እላለሁ፤ ትጉ።
37But what I say to you, I say to all, Watch.