Amharic: New Testament

Darby's Translation

Revelation

11

1በትር የሚመስል መለኪያ ለእኔ ተሰጠኝ፥ እንዲህም ተባለልኝ። ተነሥተህ የእግዚአብሔርን መቅደስና መሠዊያውን በዚያም የሚሰግዱትን ለካ።
1And there was given to me a reed like a staff, saying, Rise, and measure the temple of God, and the altar, and them that worship in it.
2በመቅደሱም ውጭ ያለው እድሞ ለአሕዛብ ተሰጥቶአልና ተወው አትለካውም፤ እነርሱም አርባ ሁለት ወር የተቀደሰችውን ከተማ ይረግጡአታል።
2And the court which [is] without the temple cast out, and measure it not; because it has been given [up] to the nations, and the holy city shall they tread under foot forty-two months.
3ለሁለቱም ምስክሮቼ ማቅ ለብሰው ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን ትንቢት ሊናገሩ እሰጣለሁ።
3And I will give [power] to my two witnesses, and they shall prophesy a thousand two hundred [and] sixty days, clothed in sackcloth.
4እነዚህ በምድር ጌታ ፊት የሚቆሙ ሁለቱ ወይራዎችና ሁለቱ መቅረዞች ናቸው።
4These are the two olive trees and the two lamps which stand before the Lord of the earth;
5ማንምም ሊጐዳቸው ቢወድ እሳት ከአፋቸው ይወጣል ጠላቶቻቸውንም ይበላል፤ ማንም ሊጐዳቸው ቢወድም እንዲሁ ሊገደል ይገባዋል።
5and if any one wills to injure them, fire goes out of their mouth, and devours their enemies. And if any one wills to injure them, thus must he be killed.
6እነዚህ ትንቢት በሚናገሩበት ወራት ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማይን ሊዘጉ ሥልጣን አላቸው፥ ውኃዎችንም ወደ ደም ሊለውጡ በሚፈልጉበትም ጊዜ ሁሉ በመቅሠፍት ሁሉ ምድርን ሊመቱ ሥልጣን አላቸው።
6These have power to shut the heaven that no rain may fall during the days of their prophecy; and they have power over the waters to turn them into blood, and to smite the earth as often as they will with every plague.
7ምስክራቸውን ከፈጸሙ በኋላ ከጥልቁ የሚወጣው አውሬ ይዋጋቸዋል ያሸንፋቸውማል ይገድላቸውማል።
7And when they shall have completed their testimony, the beast who comes up out of the abyss shall make war with them, and shall conquer them, and shall kill them:
8በድናቸውም በታላቂቱ ከተማ አደባባይ ይተኛል እርስዋም በመንፈሳዊ ምሳሌ ሰዶምና ግብጽ የተባለች ደግሞ ጌታቸው የተሰቀለባት ናት።
8and their body [shall be] on the street of the great city, which is called spiritually Sodom and Egypt, where also their Lord was crucified.
9ከወገኖችና ከነገዶችም ከቋንቋዎችም ከአሕዛብም የሆኑ ሰዎች ሦስት ቀን ተኵል በድናቸውን ይመለከታሉ፥ በድናቸውም ወደ መቃብር ሊገባ አይፈቅዱም።
9And [men] of the peoples and tribes and tongues and nations see their body three days and a half, and they do not suffer their bodies to be put into a sepulchre.
10እነዚህም ሁለት ነቢያት በምድር የሚኖሩትን ስለ ሣቀዩ በምድር የሚኖሩት በእነርሱ ላይ ደስ ይላቸዋል በደስታም ይኖራሉ እርስ በርሳቸውም ስጦታ ይሰጣጣሉ።
10And they that dwell upon the earth rejoice over them, and are full of delight, and shall send gifts one to another, because these, the two prophets, tormented them that dwell upon the earth.
11ከሦስቱ ቀን ተኵልም በኋላ ከእግዚአብሔር የወጣ የሕይወት መንፈስ ገባባቸው በእግሮቻቸውም ቆሙ፥ ታላቅም ፍርሃት በሚመለከቱት ላይ ወደቀባቸው።
11And after the three days and a half [the] spirit of life from God came into them, and they stood upon their feet; and great fear fell upon those beholding them.
12በሰማይም። ወደዚህ ውጡ የሚላቸውን ታላቅ ድምፅ ሰሙ፤ ጠላቶቻቸውም እየተመለከቱአቸው ወደ ሰማይ በደመና ወጡ።
12And I heard a great voice out of the heaven saying to them, Come up here; and they went up to the heaven in the cloud, and their enemies beheld them.
13በዚያም ሰዓት ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፥ ከከተማይቱም አሥረኛው እጅ ወደቀ፥ በመናወጥም ሰባት ሺህ ሰዎች ተገደሉ፥ የቀሩትንም ፍርሃት ያዛቸው፥ ለሰማዩም አምላክ ክብር ሰጡ።
13And in that hour there was a great earthquake, and the tenth of the city fell, and seven thousand names of men were slain in the earthquake. And the remnant were filled with fear, and gave glory to the God of the heaven.
14ሁለተኛው ወዮ አልፎአል፤ እነሆ፥ ሦስተኛው ወዮ በቶሎ ይመጣል።
14The second woe has passed; behold, the third woe comes quickly.
15ሰባተኛው መልአክ ነፋ፤ በሰማይም። የዓለም መንግሥት ለጌታችንና ለእርሱ ለክርስቶስ ሆነች፥ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣል
15And the seventh angel sounded [his] trumpet: and there were great voices in the heaven, saying, The kingdom of the world of our Lord and of his Christ is come, and he shall reign to the ages of ages.
16የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ሆኑ። በእግዚአብሔርም ፊት በዙፋኖቻቸው የተቀመጡ ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በግምባራቸው ተደፍተው
16And the twenty-four elders, who sit on their thrones before God, fell upon their faces, and worshipped God,
17ለእግዚአብሔር እየሰገዱ እንዲህ አሉ። ያለህና የነበርህ ሁሉን የምትገዛ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ትልቁን ኃይልህን ስለ ያዝህ ስለ ነገሥህም እናመሰግንሃለን፤
17saying, We give thee thanks, Lord God Almighty, [He] who is, and who was, that thou hast taken thy great power and hast reigned.
18አሕዛብም ተቈጡ፥ ቍጣህም መጣ፥ በሙታንም ትፈርድ ዘንድ ዘመን መጣ፥ ለባሪያዎችህም ለነቢያትና ለቅዱሳን ስምህንም ለሚፈሩት ለታናናሾችና ለታላላቆችም ዋጋቸውን ትሰጥ ዘንድ፥ ምድርንም የሚያጠፉትን ታጠፋ ዘንድ ዘመን መጣ።
18And the nations have been full of wrath, and thy wrath is come, and the time of the dead to be judged, and to give the recompense to thy servants the prophets, and to the saints, and to those who fear thy name, small and great; and to destroy those that destroy the earth.
19በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ፥ የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ፥ መብረቅና ድምፅም ነጐድጓድም የምድርም መናወጥ ታላቅም በረዶ ሆነ።
19And the temple of God in the heaven was opened, and the ark of his covenant was seen in his temple: and there were lightnings, and voices, and thunders, and an earthquake, and great hail.