Amharic: New Testament

Darby's Translation

Revelation

22

1በአደባባይዋም መካከል ከእግዚአብሔርና ከበጉ ዙፋን የሚወጣውን እንደ ብርሌ የሚያንጸባርቀውን የሕይወትን ውኃ ወንዝ አሳየኝ።
1And he shewed me a river of water of life, bright as crystal, going out of the throne of God and of the Lamb.
2በወንዙም ወዲያና ወዲህ በየወሩ እያፈራ አሥራ ሁለት ፍሬ የሚሰጥ የሕይወት ዛፍ ነበረ፥ የዛፉም ቅጠሎች ለሕዝብ መፈወሻ ነበሩ።
2In the midst of its street, and of the river, on this side and on that side, [the] tree of life, producing twelve fruits, in each month yielding its fruit; and the leaves of the tree for healing of the nations.
3ከእንግዲህም ወዲህ መርገም ከቶ አይሆንም። የእግዚአብሔርና የበጉም ዙፋን በእርስዋ ውስጥ ይሆናል፥ ባሪያዎቹም ያመልኩታል፥ ፊቱንም ያያሉ፥
3And no curse shall be any more; and the throne of God and of the Lamb shall be in it; and his servants shall serve him,
4ስሙም በግምባሮቻቸው ይሆናል።
4and they shall see his face; and his name [is] on their foreheads.
5ከእንግዲህም ወዲህ ሌሊት አይሆንም፥ ጌታ አምላክም በእነርሱ ላይ ያበራላቸዋልና የመብራት ብርሃንና የፀሐይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም፤ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣሉ።
5And night shall not be any more, and no need of a lamp, and light of [the] sun; for [the] Lord God shall shine upon them, and they shall reign to the ages of ages.
6እርሱም። እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛዎች ናቸው፥ የነቢያትም መናፍስት ጌታ አምላክ በቶሎ ሊሆን የሚገባውን ነገር ለባሪያዎቹ እንዲያሳይ መልአኩን ሰደደ።
6And he said to me, These words [are] faithful and true; and [the] Lord God of the spirits of the prophets has sent his angel to shew to his bondmen the things which must soon come to pass.
7እነሆም፥ በቶሎ እመጣለሁ። የዚህን መጽሐፍ ትንቢት ቃል የሚጠብቅ ብፁዕ ነው አለኝ።
7And behold, I come quickly. Blessed [is] he who keeps the words of the prophecy of this book.
8ይህንም ያየሁትና የሰማሁት እኔ ዮሐንስ ነኝ። በሰማሁትና ባየሁትም ጊዜ ይህን ባሳየኝ በመልአኩ እግር ፊት እሰግድ ዘንድ ተደፋሁ።
8And I, John, [was] he who heard and saw these things. And when I heard and saw, I fell down to do homage before the feet of the angel who shewed me these things.
9እርሱም። እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር ከወንድሞችህም ከነቢያት ጋር የዚህንም መጽሐፍ ቃል ከሚጠብቁ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ አለኝ።
9And he says to me, See [thou do it] not. I am thy fellow-bondman, and [the fellow-bondman] of thy brethren the prophets, and of those who keep the words of this book. Do homage to God.
10ለእኔም። ዘመኑ ቀርቦአልና የዚህን መጽሐፍ ትንቢት ቃል በማኅተም አትዝጋው።
10And he says to me, Seal not the words of the prophecy of this book. The time is near.
11ዓመፀኛው ወደ ፊት ያምፅ፥ ርኵሱም ወደ ፊት ይርከስ፥ ጻድቁም ወደ ፊት ጽድቅ ያድርግ፥ ቅዱሱም ወደፊት ይቀደስ አለ።
11Let him that does unrighteously do unrighteously still; and let the filthy make himself filthy still; and let him that is righteous practise righteousness still; and he that is holy, let him be sanctified still.
12እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ።
12Behold, I come quickly, and my reward with me, to render to every one as his work shall be.
13አልፋና ዖሜጋ፥ ፊተኛውና ኋለኛው፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ።
13*I* [am] the Alpha and the Omega, [the] first and [the] last, the beginning and the end.
14ወደ ሕይወት ዛፍ ለመድረስ ሥልጣን እንዲኖራቸው በደጆችዋም ወደ ከተማይቱም እንዲገቡ ልብሳቸውን የሚያጥቡ ብፁዓን ናቸው።
14Blessed [are] they that wash their robes, that they may have right to the tree of life, and that they should go in by the gates into the city.
15ውሻዎችና አስማተኞች ሴሰኛዎችም ነፍሰ ገዳዮችም ጣዖትንም የሚያመልኩት ውሸትንም የሚወዱና የሚያደርጉ ሁሉ በውጭ አሉ።
15Without [are] the dogs, and the sorcerers, and the fornicators, and the murderers, and the idolaters, and every one that loves and makes a lie.
16እኔ ኢየሱስ በአብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ይህን እንዲመሰክርላችሁ መልአኬን ላክሁ። እኔ የዳዊት ሥርና ዘር ነኝ፥ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ።
16*I* Jesus have sent mine angel to testify these things to you in the assemblies. *I* am the root and offspring of David, the bright [and] morning star.
17መንፈሱና ሙሽራይቱም። ና ይላሉ። የሚሰማም። ና ይበል። የተጠማም ይምጣ፥ የወደደም የሕይወትን ውኃ እንዲያው ይውሰድ።
17And the Spirit and the bride say, Come. And let him that hears say, Come. And let him that is athirst come; he that will, let him take [the] water of life freely.
18በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን የትንቢት ቃል ለሚሰማ ሁሉ እኔ እመሰክራለሁ፤ ማንም በዚህ ላይ አንዳች ቢጨምር እግዚአብሔር በዚህ መጽሐፍ የተጻፉትን መቅሠፍቶች ይጨምርበታል፤
18*I* testify to every one who hears the words of the prophecy of this book, If any one shall add to these things, God shall add to him the plagues which are written in this book.
19ማንምም በዚህ በትንቢት መጽሐፍ ከተጻፉት ቃሎች አንዳች ቢያጎድል፥ በዚህ መጽሐፍ ከተጻፉት ከሕይወት ዛፍና ከቅድስቲቱ ከተማ እግዚአብሔር ዕድሉን ያጎድልበታል።
19And if any one take from the words of the book of this prophecy, God shall take away his part from the tree of life, and out of the holy city, which are written in this book.
20ይህን የሚመሰክር። አዎን፥ በቶሎ እመጣለሁ ይላል። አሜን፥ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ና።
20He that testifies these things says, Yea, I come quickly. Amen; come, Lord Jesus.
21የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከሁላችን ጋር ይሁን፤ አሜን።
21The grace of the Lord Jesus Christ [be] with all the saints.