Amharic: New Testament

World English Bible

Hebrews

3

1ስለዚህ፥ ከሰማያዊው ጥሪ ተካፋዮች የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞች ሆይ፥ የሃይማኖታችንን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስን ተመልከቱ፤
1Therefore, holy brothers, partakers of a heavenly calling, consider the Apostle and High Priest of our confession, Jesus;
2ሙሴ ደግሞ በቤቱ ሁሉ የታመነ እንደሆነ፥ እርሱ ለሾመው የታመነ ነበረ።
2who was faithful to him who appointed him, as also was Moses in all his house.
3ቤትን የሚያዘጋጀው ከቤቱ ይልቅ የሚበልጥ ክብር እንዳለው መጠን፥ እንዲሁ እርሱ ከሙሴ ይልቅ የሚበልጥ ክብር የተገባው ሆኖ ተቆጥሮአልና።
3For he has been counted worthy of more glory than Moses, inasmuch as he who built the house has more honor than the house.
4እያንዳንዱ ቤት በአንድ ሰው ተዘጋጅቶአልና፥ ሁሉን ያዘጋጀ ግን እግዚአብሔር ነው።
4For every house is built by someone; but he who built all things is God.
5ሙሴስ በኋላ ስለሚነገረው ነገር ምስክር ሊሆን በቤቱ ሁሉ እንደ ሎሌ የታመነ ነበረ፥ ክርስቶስ ግን እንደ ልጅ በቤቱ ላይ የታመነ ነው፤
5Moses indeed was faithful in all his house as a servant, for a testimony of those things which were afterward to be spoken,
6እኛም የምንደፍርበትን የምንመካበትንም ተስፋ እስከ መጨረሻው አጽንተን ብንጠብቅ ቤቱ ነን።
6but Christ is faithful as a Son over his house; whose house we are, if we hold fast our confidence and the glorying of our hope firm to the end.
7ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እንደሚል።
7Therefore, even as the Holy Spirit says, “Today if you will hear his voice,
8ዛሬ ድምፁን ብትሰሙት፥ አባቶቻችሁ እኔን የፈተኑበት የመረመሩበትም አርባ ዓመትም ሥራዬን ያዩበት በምድረ በዳ በፈተና ቀን በማስመረር እንደ ሆነ፥ ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ።
8don’t harden your hearts, as in the rebellion, like as in the day of the trial in the wilderness,
10ስለዚህ ያን ትውልድ ተቆጥቼ። ዘወትር በልባቸው ይስታሉ መንገዴን ግን አላወቁም አልሁ፤
9where your fathers tested me by proving me, and saw my works for forty years.
11እንዲሁ። ወደ ዕረፍቴ አይገቡም ብዬ በቍጣዬ ማልሁ።
10Therefore I was displeased with that generation, and said, ‘They always err in their heart, but they didn’t know my ways;’
12ወንድሞች ሆይ፥ ምናልባት ሕያው እግዚአብሔርን የሚያስክዳችሁ ክፉና የማያምን ልብ ከእናንተ በአንዳችሁ እንዳይኖር ተጠንቀቁ፤
11as I swore in my wrath, ‘They will not enter into my rest.’”
13ነገር ግን ከእናንተ ማንም በኃጢአት መታለል እልከኛ እንዳይሆን፥ ዛሬ ተብሎ ሲጠራ ሳለ፥ በእያንዳንዱ ቀን እርስ በርሳችሁ ተመካከሩ፤
12Beware, brothers, lest perhaps there be in any one of you an evil heart of unbelief, in falling away from the living God;
14የመጀመሪያ እምነታችንን እስከ መጨረሻው አጽንተን ብንጠብቅ፥ የክርስቶስ ተካፋዮች ሆነናልና፤
13but exhort one another day by day, so long as it is called “today”; lest any one of you be hardened by the deceitfulness of sin.
15እየተባለ። ዛሬ ድምጹን ብትሰሙት፥ በማስመረር እንደሆነ ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ።
14For we have become partakers of Christ, if we hold fast the beginning of our confidence firm to the end:
16ሰምተው ያስመረሩት እነማን ነበሩ? በሙሴ ተመርተው ከግብጽ የወጡ ሁሉ አይደሉምን?
15while it is said, “Today if you will hear his voice, don’t harden your hearts, as in the rebellion.”
17አርባ አመትም የተቆጣባቸው እነማን ነበሩ? ሬሳቸው በምድረ በዳ የወደቀ፥ ኃጢአትን ያደረጉት እነርሱ አይደሉምን?
16For who, when they heard, rebelled? No, didn’t all those who came out of Egypt by Moses?
18ካልታዘዙትም በቀር ወደ እረፍቱ እንዳይገቡ የማለባቸው እነማን ነበሩ?
17With whom was he displeased forty years? Wasn’t it with those who sinned, whose bodies fell in the wilderness?
19ባለማመናቸውም ጠንቅ ሊገቡ እንዳልተቻላቸው እናያለን።
18To whom did he swear that they wouldn’t enter into his rest, but to those who were disobedient?
19We see that they were not able to enter in because of unbelief.