1በዚያን ጊዜ ጻፎችና ፈሪሳውያን ከኢየሩሳሌም ወደ ኢየሱስ ቀረቡና።
1Then Pharisees and scribes came to Jesus from Jerusalem, saying,
2ደቀ መዛሙርትህ ስለ ምን የሽማግሎችን ወግ ይተላለፋሉ? እንጀራ ሲበሉ እጃቸውን አይታጠቡምና አሉት።
2“Why do your disciples disobey the tradition of the elders? For they don’t wash their hands when they eat bread.”
3እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው። እናንተስ ስለ ወጋችሁ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ስለ ምን ትተላለፋላችሁ?
3He answered them, “Why do you also disobey the commandment of God because of your tradition?
4እግዚአብሔር። አባትህንና እናትህን አክብር፤ ደግሞ። አባቱን ወይም እናቱን የሰደበ ፈጽሞ ይሙት ብሎአልና፤
4 For God commanded, ‘Honor your father and your mother,’ Exodus 20:12; Deuteronomy 5:16 and, ‘He who speaks evil of father or mother, let him be put to death.’ Exodus 21:17; Leviticus 20:9
5እናንተ ግን። አባቱን ወይም እናቱን። ከእኔ የምትጠቀምበት መባ ነው የሚል ሁሉ፥
5 But you say, ‘Whoever may tell his father or his mother, “Whatever help you might otherwise have gotten from me is a gift devoted to God,”
6አባቱን ወይም እናቱን አያከብርም ትላላችሁ፤ ስለ ወጋችሁም የእግዚአብሔርን ቃል ሻራችሁ።
6 he shall not honor his father or mother.’ You have made the commandment of God void because of your tradition.
7እናንተ ግብዞች፥ ኢሳይያስ ስለ እናንተ።
7 You hypocrites! Well did Isaiah prophesy of you, saying,
8ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል፥ ልቡ ግን ከእኔ በጣም የራቀ ነው፤
8 ‘These people draw near to me with their mouth, and honor me with their lips; but their heart is far from me.
9የሰውም ሥርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል ብሎ በእውነት ትንቢት ተናገረ።
9 And in vain do they worship me, teaching as doctrine rules made by men.’” Isaiah 29:13
10ሕዝቡንም ጠርቶ። ስሙ አስተውሉም፤
10He summoned the multitude, and said to them, “Hear, and understand.
11ሰውን የሚያረክሰው ወደ አፍ የሚገባ አይደለም፥ ከአፍ የሚወጣው ግን ሰውን የሚያረክሰው ይህ ነው አላቸው።
11 That which enters into the mouth doesn’t defile the man; but that which proceeds out of the mouth, this defiles the man.”
12በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ቀርበው። ፈሪሳውያን ይህን ቃል ሰምተው እንደ ተሰናከሉ አወቅህን? አሉት።
12Then the disciples came, and said to him, “Do you know that the Pharisees were offended, when they heard this saying?”
13እርሱ ግን መልሶ። የሰማዩ አባቴ ያልተከለው ተክል ሁሉ ይነቀላል።
13But he answered, “Every plant which my heavenly Father didn’t plant will be uprooted.
14ተዉአቸው፤ ዕውሮችን የሚመሩ ዕውሮች ናቸው፤ ዕውርም ዕውርን ቢመራው ሁለቱም ወደ ጉድጓድ ይወድቃሉ አለ።
14 Leave them alone. They are blind guides of the blind. If the blind guide the blind, both will fall into a pit.”
15ጴጥሮስም መልሶ። ምሳሌውን ተርጕምልን አለው።
15Peter answered him, “Explain the parable to us.”
16ኢየሱስም እንዲህ አለ። እናንተ ደግሞ እስካሁን የማታስተውሉ ናችሁን?
16So Jesus said, “Do you also still not understand?
17ወደ አፍ የሚገባ ሁሉ ወደ ሆድ አልፎ ወደ እዳሪ እንዲጣል አትመለከቱምን?
17 Don’t you understand that whatever goes into the mouth passes into the belly, and then out of the body?
18ከአፍ የሚወጣ ግን ከልብ ይወጣል፥ ሰውንም የሚያረክሰው ያ ነው።
18 But the things which proceed out of the mouth come out of the heart, and they defile the man.
19ከልብ ክፉ አሳብ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ ዝሙት፥ መስረቅ፥ በውሸት መመስከር፥ ስድብ ይወጣልና።
19 For out of the heart come forth evil thoughts, murders, adulteries, sexual sins, thefts, false testimony, and blasphemies.
20ሰውን የሚያረክሰው ይህ ነው እንጂ፥ ባልታጠበ እጅ መብላትስ ሰውን አያረክሰውም።
20 These are the things which defile the man; but to eat with unwashed hands doesn’t defile the man.”
21ኢየሱስም ከዚያ ወጥቶ ወደ ጢሮስና ወደ ሲዶና አገር ሄደ።
21Jesus went out from there, and withdrew into the region of Tyre and Sidon.
22እነሆም፥ ከነናዊት ሴት ከዚያ አገር ወጥታ። ጌታ ሆይ፥ የዳዊት ልጅ፥ ማረኝ፤ ልጄን ጋኔን ክፉኛ ይዞአታል ብላ ጮኸች።
22Behold, a Canaanite woman came out from those borders, and cried, saying, “Have mercy on me, Lord, you son of David! My daughter is severely demonized!”
23እርሱ ግን አንዳች አልመለሰላትም። ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው። በኋላችን ትጮኻለችና አሰናብታት እያሉ ለመኑት።
23But he answered her not a word. His disciples came and begged him, saying, “Send her away; for she cries after us.”
24እርሱም መልሶ። ከእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች በቀር አልተላክሁም አለ።
24But he answered, “I wasn’t sent to anyone but the lost sheep of the house of Israel.”
25እርስዋ ግን መጥታ። ጌታ ሆይ፥ እርዳኝ እያለች ሰገደችለት።
25But she came and worshiped him, saying, “Lord, help me.”
26እርሱ ግን መልሶ። የልጆችን እንጀራ ይዞ ለቡችሎች መጣል አይገባም አለ።
26But he answered, “It is not appropriate to take the children’s bread and throw it to the dogs.”
27እርስዋም። አዎን ጌታ ሆይ፤ ቡችሎችም እኮ ከጌቶቻቸው ማዕድ የወደቀውን ፍርፋሪ ይበላሉ አለች።
27But she said, “Yes, Lord, but even the dogs eat the crumbs which fall from their masters’ table.”
28በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ። አንቺ ሴት፥ እምነትሽ ታላቅ ነው፤ እንደወደድሽ ይሁንልሽ አላት። ልጅዋም ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ዳነች።
28Then Jesus answered her, “Woman, great is your faith! Be it done to you even as you desire.” And her daughter was healed from that hour.
29ኢየሱስም ከዚያ አልፎ ወደ ገሊላ ባሕር አጠገብ መጣ፥ ወደ ተራራም ወጥቶ በዚያ ተቀመጠ።
29Jesus departed there, and came near to the sea of Galilee; and he went up into the mountain, and sat there.
30ብዙ ሕዝብም አንካሶችን፥ ዕውሮችንም፥ ዲዳዎችንም፥ ጉንድሾችንም፥ ሌሎችንም ብዙ ይዘው ወደ እርሱ ቀረቡ፥ በኢየሱስም እግር አጠገብ ጣሉአቸው፤ ፈወሳቸውም፤
30Great multitudes came to him, having with them the lame, blind, mute, maimed, and many others, and they put them down at his feet. He healed them,
31ስለዚህም ሕዝቡ ዲዳዎች ሲናገሩ፥ ጉንድሾችም ሲድኑ፥ አንካሶችም ሲሄዱ፥ ዕውሮችም ሲያዩ አይተው ተደነቁ፤ የእስራኤልንም አምላክ አከበሩ።
31so that the multitude wondered when they saw the mute speaking, injured whole, lame walking, and blind seeing—and they glorified the God of Israel.
32ኢየሱስም ደቀ መዛሙርቱን ጠርቶ። ሕዝቡ ከእኔ ጋር እስካሁን ሦስት ቀን ውለዋልና የሚበሉት ስለ ሌላቸው አዝንላቸዋለሁ፤ በመንገድም እንዳይዝሉ ጦማቸውን ላሰናብታቸው አልወድም አላቸው።
32Jesus summoned his disciples and said, “I have compassion on the multitude, because they continue with me now three days and have nothing to eat. I don’t want to send them away fasting, or they might faint on the way.”
33ደቀ መዛሙርቱም። ይህን ያህል ሕዝብ የሚያጠግብ ይህን ያህል እንጀራ በምድረ በዳ ከወዴት እናገኛለን? አሉት።
33The disciples said to him, “Where should we get so many loaves in a deserted place as to satisfy so great a multitude?”
34ኢየሱስም። ስንት እንጀራ አላችሁ? አላቸው። እነርሱም። ሰባት፥ ጥቂትም ትንሽ ዓሣ አሉት።
34Jesus said to them, “How many loaves do you have?” They said, “Seven, and a few small fish.”
35ሕዝቡም በምድር ላይ እንዲቀመጡ አዘዘ፤
35He commanded the multitude to sit down on the ground;
36ሰባቱንም እንጀራ ዓሣውንም ይዞ አመሰገነ ቈርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፥ ደቀ መዛሙርቱም ለሕዝቡ።
36and he took the seven loaves and the fish. He gave thanks and broke them, and gave to the disciples, and the disciples to the multitudes.
37ሁሉም በሉና ጠገቡ፥ የተረፈውንም ቁርስራሽ ሰባት ቅርጫት ሙሉ አነሡ።
37They all ate, and were filled. They took up seven baskets full of the broken pieces that were left over.
38የበሉትም ከሴቶችና ከልጆች በቀር አራት ሺህ ወንዶች ነበሩ።
38Those who ate were four thousand men, besides women and children.
39ሕዝቡንም ካሰናበተ በኋላ ወደ ታንኳይቱ ገብቶ ወደ መጌዶል አገር መጣ።
39Then he sent away the multitudes, got into the boat, and came into the borders of Magdala.