Lithuanian

Amharic: New Testament

2 Peter

3

1Mylimieji, tai jau antras laiškas, kurį jums rašau. Šiuose laiškuose žadinu jūsų tyras mintis prisiminimais,
1ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የምጽፍላችሁ መልእክት ይህች ሁለተኛይቱ ናት። በቅዱሳን ነቢያትም ቀድሞ የተባለውን ቃል በሐዋርያቶቻችሁም ያገኛችኋትን የጌታንና የመድኃኒትን ትእዛዝ እንድታስቡ በሁለቱ እያሳሰብኋችሁ ቅን ልቡናችሁን አነቃቃለሁ።
2kad atsimintumėte šventųjų pranašų iš anksto paskelbtus žodžius ir mūsų­Viešpaties ir Gelbėtojo apaštalų­įsakymą.
3በመጨረሻው ዘመን እንደ ራሳቸው ምኞት የሚመላለሱ ዘባቾች በመዘበት እንዲመጡ ይህን በፊት እወቁ፤
3Pirmiausia žinokite, kad paskutinėmis dienomis pasirodys šaipūnai, gyvenantys savo geiduliais
4እነርሱም። የመምጣቱ የተስፋ ቃል ወዴት ነው? አባቶች ከሞቱባት ጊዜ፥ ከፍጥረት መጀመሪያ ይዞ ሁሉ እንዳለ ይኖራልና ይላሉ።
4ir kalbantys: “Kur Jo atėjimo pažadas? Juk nuo to laiko, kai užmigo protėviai, visa pasilieka kaip buvę nuo sutvėrimo pradžios”.
5ሰማያት ከጥንት ጀምረው ምድርም በእግዚአብሔር ቃል ከውኃ ተጋጥማ በውኃ መካከል እንደ ነበሩ ወደው አያስተውሉምና፤
5Mat jiems, to norintiems, yra paslėpta, kad nuo seno buvo dangūs ir žemė, iš vandens ir per vandenį sutvarkyta Dievo žodžiu.
6በዚህም ምክንያት ያን ጊዜ የነበረ ዓለም በውኃ ሰጥሞ ጠፋ፤
6Todėl ir ano meto pasaulis žuvo, vandeniu užtvindytas.
7አሁን ያሉ ሰማያትና ምድር ግን እግዚአብሔርን የማያመልኩት ሰዎች እስከሚጠፉበት እስከ ፍርድ ቀን ድረስ ተጠብቀው በዚያ ቃል ለእሳት ቀርተዋል።
7O dabartiniai dangūs ir žemė tuo pačiu žodžiu palaikomi ugniai, saugomi teismo dienai ir bedievių žmonių žuvimui.
8እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ፥ በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት፥ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን እንደ ሆነ ይህን አንድ ነገር አትርሱ።
8Tačiau, mylimieji, vienas dalykas neturi likti jūsų nepastebėtas: viena diena pas Viešpatį yra kaip tūkstantis metų, ir tūkstantis metų­kaip viena diena.
9ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፥ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል።
9Viešpats nedelsia ištesėti savo pažado, kaip kai kurie mano, bet kantriai elgiasi su mumis, nenorėdamas, kad kuris pražūtų, bet kad visi atsiverstų.
10የጌታው ቀን ግን እንደ ሌባ ሆኖ ይመጣል፤ በዚያም ቀን ሰማያት በታላቅ ድምፅ ያልፋሉ፥ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኵሳት ይቀልጣል፥ ምድርም በእርስዋም ላይ የተደረገው ሁሉ ይቃጠላል።
10O Viešpaties diena ateis kaip vagis naktį. Tada dangūs praeis su smarkiu ūžesiu, elementai sutirps karštyje, ir žemė su savo kūriniais sudegs.
11ይህ ሁሉ እንዲህ የሚቀልጥ ከሆነ፥ የእግዚአብሔርን ቀን መምጣት እየጠበቃችሁና እያስቸኰላችሁ፥ በቅዱስ ኑሮ እግዚአብሔርንም በመምሰል እንደ ምን ልትሆኑ ይገባችኋል? ስለዚያ ቀን ሰማያት ተቃጥለው ይቀልጣሉ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኵሳት ይፈታል፤
11Jeigu visa taip suirs, tai kaip reikėtų pasižymėti šventu elgesiu ir dievotumu jums,
13ነገር ግን ጽድቅ የሚኖርባትን አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር እንደ ተስፋ ቃሉ እንጠብቃለን።
12laukiantiems ir skubinantiems Dievo dienos atėjimą, kai dangūs suirs liepsnose ir elementai sutirps iš karščio!
14ስለዚህ፥ ወዳጆች ሆይ፥ ይህን እየጠበቃችሁ ያለ ነውርና ያለ ነቀፋ ሆናችሁ በሰላም በእርሱ እንድትገኙ ትጉ፥
13Tačiau mes pagal Jo pažadą laukiame naujo dangaus ir naujos žemės, kuriuose gyvena teisumas.
15የጌታችንም ትዕግሥት መዳናችሁ እንደ ሆነ ቍጠሩ። እንዲህም የተወደደው ወንድማችን ጳውሎስ ደግሞ እንደ ተሰጠው ጥበብ መጠን ጻፈላችሁ፥ በመልእክቱም ሁሉ ደግሞ እንደ ነገረ ስለዚህ ነገር ተናገረ።
14Todėl, mylimieji, šito laukdami, stenkitės, kad Jis rastų jus taikoje, nesuteptus ir nepeiktinus.
16በእነዚያ ዘንድ ለማስተዋል የሚያስቸግር ነገር አለ፥ ያልተማሩትና የማይጸኑትም ሰዎች ሌሎችን መጻሕፍት እንደሚያጣምሙ እነዚህን ደግሞ ለገዛ ጥፋታቸው ያጣምማሉ።
15Mūsų Viešpaties kantrumą laikykite išgelbėjimu, kaip jums parašė ir mūsų mylimas brolis Paulius pagal jam duotą išmintį;
17እንግዲህ እናንተ፥ ወዳጆች ሆይ፥ ይህን አስቀድማችሁ ስለምታውቁ፥ በዓመፀኞቹ ስሕተት ተስባችሁ ከራሳችሁ ጽናት እንዳትወድቁ ተጠንቀቁ፤
16jis taip kalba apie šituos dalykus visuose laiškuose. Juose esama sunkiai suprantamų dalykų, kuriuos neišmokyti ir svyruojantys iškraipo, aiškindami, kaip ir kitus Raštus, savo pačių pražūčiai.
18ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ለእርሱ አሁንም እስከ ዘላለምም ቀን ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።
17Tad jūs, mylimieji, iš anksto tai žinodami, saugokitės, kad, nedorėlių paklydimo traukiami, nenupultumėte nuo savo stiprybės.
18Aukite malone ir mūsų Viešpaties ir Gelbėtojo Jėzaus Kristaus pažinimu. Jam šlovė dabar ir per amžius! Amen.