Lithuanian

Amharic: New Testament

Hebrews

6

1Todėl, palikę pradinį Kristaus mokymą, veržkimės prie tobulumo, užuot vėl dėję pamatus iš atsivertimo nuo negyvų darbų, iš tikėjimo Dievu,
1ስለዚህ የክርስቶስን ነገር መጀመሪያ የሚናገረውን ቃል ትተን ወደ ፍጻሜ እንሂድ፤ መሠረትን ደግመን አንመሥርት፥ እርሱም ከሞተ ሥራ ንስሐና በእግዚአብሔር እምነት፥ ስለ ጥምቀቶችና እጆችንም ስለ መጫን ስለ ሙታንም ትንሣኤ ስለ ዘላለም ፍርድም ትምህርት ነው።
2iš mokymo apie krikštus, rankų uždėjimo, mirusiųjų prikėlimo ir amžinybės teismo.
3እግዚአብሔርም ቢፈቅድ ይህን እናደርጋለን።
3Jei Dievas leis, ir tai padarysime.
4አንድ ጊዜ ብርሃን የበራላቸውን ሰማያዊውንም ስጦታ የቀመሱትን ከመንፈስ ቅዱስም ተካፋዮች ሆነው የነበሩትን
4Kurie kartą jau buvo apšviesti, paragavo dangiškos dovanos, tapo Šventosios Dvasios dalininkais,
5መልካሙንም የእግዚአብሔርን ቃልና ሊመጣ ያለውን የዓለም ኃይል የቀመሱትን
5paragavo gerojo Dievo žodžio bei ateinančio amžiaus jėgų
6በኋላም የካዱትን እንደገና ለንስሐ እነርሱን ማደስ የማይቻል ነው፤ ለራሳቸው የእግዚአብሔርን ልጅ ይሰቅሉታልና ያዋርዱትማልና።
6ir atpuolė, tų nebeįmanoma vėl grąžinti naujai atgailai, nes jie kryžiuoja sau Dievo Sūnų ir išstato Jį viešai paniekai.
7ብዙ ጊዜ በእርስዋ ላይ የሚወርደውን ዝናብ የምትጠጣ መሬት፥ ለሚያርሱአትም ደግሞ የምትጠቅምን አትክልት የምታበቅል፥ ከእግዚአብሔር በረከትን ታገኛለችና፤
7Jeigu žemė sugeria dažną lietų ir iš jos želia želmenys, naudingi tiems, kurie ją dirba, tai ji susilaukia Dievo palaiminimo,
8እሾህና ኵርንችትን ግን ብታወጣ፥ የተጣለች ናት ለመረገምም ትቀርባለች፥ መጨረሻዋም መቃጠል ነው።
8bet jeigu ji teželdo erškėčius bei usnis, tai ji niekam tikusi, greitai bus prakeikta ir galiausiai sudeginta.
9ስለ እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ ምንም እንኳ እንዲሁ ብንናገር፥ አብልጦ የሚሻለውና ለመዳን የሚሆነው እንዲሆንላችሁ ተረድተናል።
9Nors taip kalbame, bet jums, mylimieji, tikimės geresnių, vedančių į išgelbėjimą dalykų.
10እግዚአብሔር፥ ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ እስከ አሁንም ስለምታገለግሉአቸው፥ ያደረጋችሁትን ሥራ ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመፀኛ አይደለምና።
10Dievas nėra neteisingas, kad pamirštų jūsų darbą ir meilės triūsą, kurį parodėte Jo vardui, kai tarnavote ir tebetarnaujate šventiesiems.
11በእምነትና በትዕግሥትም የተስፋውን ቃል የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንዳትሆኑ፥ ተስፋ እስኪሞላ ድረስ እያንዳንዳችሁ ያን ትጋት እስከ መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን።
11Todėl trokštame, kad kiekvienas iš jūsų rodytų ankstesnį uolumą iki galo, kol pasieks visišką vilties užtikrintumą,­
13እግዚአብሔርም ለአብርሃም ተስፋ በሰጠው ጊዜ። በእውነት እየባረክሁ እባርክሃለሁ እያበዛሁም አበዛሃለሁ ብሎ፥ ከእርሱ በሚበልጥ በማንም ሊምል ስላልቻለ፥ በራሱ ማለ፤
12kad neaptingtumėte, bet būtumėte sekėjai tų, kurie tikėjimu ir kantrybe paveldi pažadus.
15እንዲሁም እርሱ ከታገሰ በኋላ ተስፋውን አገኘ።
13Kai Dievas davė Abraomui pažadą, neturėdamas kuo aukštesniu prisiekti, prisiekė savimi,
16ሰዎች ከእነርሱ በሚበልጠው ይምላሉና፥ ለማስረዳትም የሆነው መሐላ የሙግት ሁሉ ፍጻሜ ይሆናል፤
14sakydamas: “Iš tiesų, Aš laiminte palaiminsiu tave, dauginte padauginsiu tave”.
17ስለዚህም እግዚአብሔር፥ የተስፋውን ቃል ለሚወርሱ ፈቃዱ እንደ ማይለወጥ አብልጦ ሊያሳያቸው ስለ ፈቀደ፥ እግዚአብሔር ሊዋሽ በማይቻል በሁለት በማይለወጥ ነገር፥ በፊታችን ያለውን ተስፋ ለመያዝ ለሸሸን ለእኛ ብርቱ መጽናናት ይሆንልን ዘንድ፥ በመሓላ በመካከል ገባ፤
15Ir Abraomas, kantriai laukdamas, gavo, kas buvo pažadėta.
19ይህም ተስፋ እንደ ነፍስ መልሕቅ አለን እርሱም እርግጥና ጽኑ የሆነ ወደ መጋረጃውም ውስጥ የገባ ነው፤
16Žmonės prisiekia aukštesniais dalykais ir kiekvieno ginčo pabaigoje patvirtinimui imasi priesaikos.
20በዚያም ኢየሱስ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ሊቀ ካህናት የሆነው፥ ስለ እኛ ቀዳሚ ሆኖ ገባ።
17Todėl Dievas, norėdamas stipriau pabrėžti pažado paveldėtojams savo valios nekintamumą, pridėjo priesaiką.
18Tad du nekintami dalykai, kuriuose neįmanoma, kad Dievas meluotų, tvirtai guodžia mus, atradusius prieglobstį mums skirtoje viltyje.
19Ji mums yra tarsi saugus ir tvirtas sielos inkaras, prasiskverbiantis pro uždangą vidun,
20kur už mus kaip pirmtakas įžengė Jėzus, tapęs amžiams vyriausiuoju Kunigu Melchizedeko būdu.