1Од Павла, слуге Божјег, а апостола Исуса Христа по вери изабраних Божјих и по познању истине побожности,
1የእግዚአብሔር ባሪያና የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ፥ በእግዚአብሔር ለተመረጡት እምነት እንዲሆንላቸው በዘላለምም ሕይወት ተስፋ እንደ አምልኮት ያለውን እውነት እንዲያውቁ የተላከ፤ ስለዚህም ሕይወት የማይዋሽ እግዚአብሔር ከዘላለም ዘመናት በፊት ተስፋ ሰጠ፥
2За наду вечног живота, који обећа нелажни Бог пре времена вечних,
3በዘመኑም ጊዜ፥ መድኃኒታችን እግዚአብሔር እንዳዘዘ፥ ለእኔ አደራ በተሰጠኝ ስብከት ቃሉን ገለጠ፤
3А јави у времена своја реч своју проповедањем, које је мени поверено по заповести Спаситеља нашег Бога,
4በሃይማኖት ኅብረት እውነተኛ ልጄ ለሚሆን ለቲቶ፤ ከእግዚአብሔር አብ ከመድኃኒታችንም ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ምሕረት ሰላምም ይሁን።
4Титу, правом сину по вери нас обојице, благодат, милост, мир од Бога Оца и Господа Исуса Христа, Спаса нашег.
5ስለዚህ ምክንያት የቀረውን እንድታደራጅ በየከተማውም፥ እኔ አንተን እንዳዘዝሁ፥ ሽማግሌዎችን እንድትሾም በቀርጤስ ተውሁህ፤
5Зато те оставих у Криту да поправиш шта је недовршено, и да поставиш по свим градовима свештенике, као што ти ја заповедих,
6የማይነቀፍና የአንዲት ሚስት ባል የሚሆን፥ የሚያምኑም ልጆች ያሉት፥ ስለ መዳራትም ወይም ስለ አለመታዘዝ የማይከሰስ ማንም ቢኖር፥ ሹመው።
6Ако је ко без мане, једне жене муж, и има верну децу, коју не коре за курварство или за непокорност.
7ኤጲስ ቆጶስ፥ እንደ እግዚአብሔር መጋቢ፥ የማይነቀፍ ሊሆን ይገባዋልና፤ የማይኮራ፥ የማይቆጣ፥ የማይሰክር፥ የማይጨቃጨቅ፥ ነውረኛ ረብ የማይወድ፥
7Јер владика треба да је без мане, као Божји пристав; не који себи угађа, не гневљив, не пијаница, не бојац, не лаком на погани добитак;
8ነገር ግን እንግዳ ተቀባይ፥ በጎ የሆነውን ነገር የሚወድ፥ ጠንቃቃ፥ ጻድቅ፥ ቅዱስ፥ ራሱን የሚገዛ ይሁን፤
8Него гостољубив, благ, поштен, праведан, свет, чист;
9ሕይወት በሚገኝበት ትምህርት ደግሞ ሊመክር ተቃዋሚዎቹንም ሊወቅስ ይችል ዘንድ፥ እንደተማረው በታመነ ቃል ይጽና።
9Који се држи верне речи по науци, да буде кадар и саветовати са здравом науком, и покарати оне који се противе.
10የማይታዘዙና ከንቱ የሚናገሩ የሚያታልሉ ይልቁንም ከተገረዙት ወገን የሚሆኑ ብዙ ናቸውና፤
10Јер има много непослушних, празноговорљивих, и умом преварених, а особито који су из обрезања,
11እነዚህም ስለ ነውረኛ ረብ የማይገባውን እያስተማሩ ቤቶችን በሞላው ስለ ሚገለብጡ፥ አፋቸውን መዝጋት ይገባል።
11Којима треба уста затворити; који целе куће изопачују учећи шта не треба, поганог добитка ради.
12የገዛ ራሳቸው ነቢይ የሆነ ከእነርሱ አንዱ። የቀርጤስ ሰዎች ዘወትር ውሸተኞች፥ ክፉዎች አራዊት፥ በላተኞች፥ ሥራ ፈቶች ናቸው ብሎአል።
12А рече неко од њих, њихов пророк: Крићани свагда лажљиви, зли зверови, беспослени трбуси.
13ይህ ምስክር እውነተኛ ነው። ስለዚህ ምክንያት የአይሁድን ተረትና ከእውነት ፈቀቅ የሚሉትን ሰዎች ትእዛዝ ሳያዳምጡ፥ በሃይማኖት ጤናሞች እንዲሆኑ በብርቱ ውቀሳቸው።
13Сведочанство је ово истинито; заради тог узрока карај их без штеђења, да буду здрави у вери,
15ሁሉ ለንጹሖች ንጹሕ ነው፤ ለርኵሳንና ለማያምኑ ግን ንጹሕ የሆነ ምንም የለም፥ ነገር ግን አእምሮአቸውም ሕሊናቸውም ረክሶአል።
14Не слушајући јеврејске гаталице ни заповести људи који се одвраћају од истине.
16እግዚአብሔርን እንዲያውቁ በግልጥ ይናገራሉ፥ ዳሩ ግን የሚያስጸይፉና የማይታዘዙ ለበጎ ሥራም ሁሉ የማይበቁ ስለ ሆኑ፥ በሥራቸው ይክዱታል።
15Чистима је све чисто; а поганима и невернима ништа није чисто, него је опогањен њихов и ум и савест.
16Говоре да познају Бога, а делима Га се одричу; јер су мрски и непослушни, и ни за какво добро дело ваљани.