Young`s Literal Translation

Amharic: New Testament

2 Corinthians

5

1For we have known that if our earthly house of the tabernacle may be thrown down, a building from God we have, an house not made with hands — age-during — in the heavens,
1ድንኳን የሚሆነው ምድራዊ መኖሪያችን ቢፈርስ፥ በሰማይ ያለ በእጅ ያልተሠራ የዘላለም ቤት የሚሆን ከእግዚአብሔር የተሠራ ሕንጻ እንዳለን እናውቃለንና።
2for also in this we groan, with our dwelling that is from heaven earnestly desiring to clothe ourselves,
2በዚህ ውስጥ በእውነት እንቃትታለንና፥
3if so be that, having clothed ourselves, we shall not be found naked,
3ከሰማይም የሚሆነውን መኖሪያችንን እንድንለብስ እንናፍቃለንና ለብሰን ራቁታችንን አንገኝም።
4for we also who are in the tabernacle do groan, being burdened, seeing we wish not to unclothe ourselves, but to clothe ourselves, that the mortal may be swallowed up of the life.
4በእውነትም የሚሞተው በሕይወት ይዋጥ ዘንድ ልንለብስ እንጂ ልንገፈፍ የማንወድ ስለ ሆነ፥ በድንኳኑ ያለን እኛ ከብዶን እንቃትታለን።
5And He who did work us to this self-same thing [is] God, who also did give to us the earnest of the Spirit;
5ነገር ግን ለዚሁ የሠራን እግዚአብሔር ነው እርሱም የመንፈሱን መያዣ ሰጠን።
6having courage, then, at all times, and knowing that being at home in the body, we are away from home from the Lord, —
6እንግዲህ ሁልጊዜ ታምነን፥ በእምነት እንጂ በማየት አንመላለስምና በሥጋ ስናድር ከጌታ ተለይተን በስደት እንዳለን የምናውቅ ከሆንን፥
7for through faith we walk, not through sight —
8ታምነናል ይልቁንም ከሥጋ ተለይተን በስደት መኖር በጌታም ዘንድ ማደር ደስ ይለናል።
8we have courage, and are well pleased rather to be away from the home of the body, and to be at home with the Lord.
9ስለዚህ ደግሞ ብናድር ወይም ተለይተን ብንሆን እርሱን ደስ የምናሰኝ ልንሆን እንቀናለን።
9Wherefore also we are ambitious, whether at home or away from home, to be well pleasing to him,
10መልካም ቢሆን ወይም ክፉ እንዳደረገ፥ እያንዳንዱ በሥጋው የተሠራውን በብድራት ይቀበል ዘንድ ሁላችን በክርስቶስ በፍርድ ወንበር ፊት ልንገለጥ ይገባናልና።
10for all of us it behoveth to be manifested before the tribunal of the Christ, that each one may receive the things [done] through the body, in reference to the things that he did, whether good or evil;
11እንግዲህ የጌታን ፍርሃት አውቀን ሰዎችን እናስረዳለን ለእግዚአብሔር ግን የተገለጥን ነን፤ በሕሊናችሁም ደግሞ የተገለጥን እንደ ሆንን ተስፋ አደርጋለሁ።
11having known, therefore, the fear of the Lord, we persuade men, and to God we are manifested, and I hope also in your consciences to have been manifested;
12በመልክ እንጂ በልብ ለማይመኩ የምትመልሱላቸው መልስ እንዲኖራችሁ፥ በእኛ ልትመኩ ምክንያት እንሰጣችኋለን እንጂ ራሳችንን ደግሞ ለእናንተ የምናመሰግን አይደለንም።
12for not again ourselves do we recommend to you, but we are giving occasion to you of glorifying in our behalf, that ye may have [something] in reference to those glorifying in face and not in heart;
13እብዶች ብንሆን፥ ለእግዚአብሔር ነው፤ ባለ አእምሮዎች ብንሆን፥ ለእናንተ ነው።
13for whether we were beside ourselves, [it was] to God; whether we be of sound mind — [it is] to you,
14ይህን ስለቆረጥን የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናልና፤ አንዱ ስለ ሁሉ ሞተ፤ እንግዲያስ ሁሉ ሞቱ፤
14for the love of the Christ doth constrain us, having judged thus: that if one for all died, then the whole died,
15በሕይወትም ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ።
15and for all he died, that those living, no more to themselves may live, but to him who died for them, and was raised again.
16ስለዚህ እኛ ከአሁን ጀምሮ ማንንም በሥጋ እንደሚሆን አናውቅም፤ ክርስቶስንም በሥጋ እንደ ሆነ ያወቅነው ብንሆን እንኳ፥ አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ እንደዚህ አናውቀውም።
16So that we henceforth have known no one according to the flesh, and even if we have known Christ according to the flesh, yet now we know him no more;
17ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።
17so that if any one [is] in Christ — [he is] a new creature; the old things did pass away, lo, become new have the all things.
18ነገር ግን የሆነው ሁሉ፥ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን፥ ከእግዚአብሔር ነው፤
18And the all things [are] of God, who reconciled us to Himself through Jesus Christ, and did give to us the ministration of the reconciliation,
19እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ።
19how that God was in Christ — a world reconciling to Himself, not reckoning to them their trespasses; and having put in us the word of the reconciliation,
20እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን።
20in behalf of Christ, then, we are ambassadors, as if God were calling through us, we beseech, in behalf of Christ, `Be ye reconciled to God;`
21እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው።
21for him who did not know sin, in our behalf He did make sin, that we may become the righteousness of God in him.