1And I say, so long time as the heir is a babe, he differeth nothing from a servant — being lord of all,
1ነገር ግን እላለሁ፥ ወራሹ ሕፃን ሆኖ ባለበት ዘመን ሁሉ፥ ምንም የሁሉ ጌታ ቢሆን ከቶ ከባሪያ አይለይም፥
2but is under tutors and stewards till the time appointed of the father,
2ነገር ግን አባቱ እስከ ቀጠረለት ቀን ድረስ ከጠባቂዎችና ከመጋቢዎች በታች ነው።
3so also we, when we were babes, under the elements of the world were in servitude,
3እንዲሁ እኛ ደግሞ ሕፃናት ሆነን ሳለን ከዓለም መጀመሪያ ትምህርት በታች ተገዝተን ባሪያዎች ነበርን፤
4and when the fulness of time did come, God sent forth His Son, come of a woman, come under law,
4ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤
5that those under law he may redeem, that the adoption of sons we may receive;
5እንደ ልጆች እንሆን ዘንድ፥ ከሕግ በታች ያሉትን ይዋጅ ዘንድ።
6and because ye are sons, God did send forth the spirit of His Son into your hearts, crying, `Abba, Father!`
6ልጆችም ስለ ሆናችሁ እግዚአብሔር አባ አባት ብሎ የሚጮኽ የልጁን መንፈስ በልባችሁ ውስጥ ላከ።
7so that thou art no more a servant, but a son, and if a son, also an heir of God through Christ.
7ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ልጅ ነህ እንጂ ባሪያ አይደለህም፤ ልጅም ከሆንህ ደግሞ በክርስቶስ የእግዚአብሔር ወራሽ ነህ።
8But then, indeed, not having known God, ye were in servitude to those not by nature gods,
8ነገር ግን በዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን ሳታውቁ በባሕርያቸው አማልክት ለማይሆኑ ባሪያዎች ሆናችሁ ተገዛችሁ፤
9and now, having known God — and rather being known by God — how turn ye again unto the weak and poor elements to which anew ye desire to be in servitude?
9አሁን ግን እግዚአብሔርን ስታውቁ ይልቅስ በእግዚአብሔር ስትታወቁ እንደ ገና ወደ ደካማ ወደሚናቅም ወደ መጀመሪያ ትምህርት እንዴት ትመለሳላችሁ? እንደ ገና ባሪያዎች ሆናችሁ ዳግመኛ ለዚያ ልትገዙ ትወዳላችሁን?
10days ye observe, and months, and times, and years!
10ቀንንና ወርን ዘመንንም ዓመትንም በጥንቃቄ ትጠብቃላችሁ።
11I am afraid of you, lest in vain I did labour toward you.
11ምናልባት በከንቱ ለእናንተ ደክሜአለሁ ብዬ እፈራችኋለሁ።
12Become as I [am] — because I also [am] as ye brethren, I beseech you; to me ye did no hurt,
12ወንድሞች ሆይ፥ እኔ ደግሞ እንደ እናንተ ሆኜአለሁና። እንደ እኔ ሁኑ ብዬ እለምናችኋለሁ። አንዳችም አልበደላችሁኝም።
13and ye have known that through infirmity of the flesh I did proclaim good news to you at the first,
13በመጀመሪያ ወንጌልን በሰበክሁላችሁ ጊዜ ከሥጋ ድካም የተነሣ እንደ ነበረ ታውቃላችሁ፥
14and my trial that [is] in my flesh ye did not despise nor reject, but as a messenger of God ye did receive me — as Christ Jesus;
14በሥጋዬም ፈተና የሆነባችሁን ነገር አልናቃችሁትምና አልተጸየፋችሁትም ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር መልአክ አዎን እንደ ክርስቶስ ኢየሱስ ተቀበላችሁኝ።
15what then was your happiness? for I testify to you, that if possible, your eyes having plucked out, ye would have given to me;
15እንግዲህ ደስ ማሰኘታችሁ ወዴት አለ? ቢቻልስ ዓይኖቻችሁን አውጥታችሁ በሰጣችሁኝ ብዬ እመሰክርላችኋለሁ።
16so that your enemy have I become, being true to you?
16እንኪያስ እውነቱን ስለ ነገርኋችሁ ጠላት ሆንሁባችሁን?
17they are zealous for you — [yet] not well, but they wish to shut us out, that for them ye may be zealous;
17በብርቱ ይፈልጉአችኋል፥ ለመልካም አይደለም ነገር ግን በብርቱ ትፈልጉአቸው ዘንድ በውጭ ሊያስቀሩአችሁ ይወዳሉ።
18and [it is] good to be zealously regarded, in what is good, at all times, and not only in my being present with you;
18ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ በምኖርበት ጊዜ ብቻ ሳይሆን ሁልጊዜ በመልካም ነገር ተፈላጊ ብትሆኑ መልካም ነው።
19my little children, of whom again I travail in birth, till Christ may be formed in you,
19ልጆቼ ሆይ፥ ክርስቶስ በእናንተ እስኪሣል ድረስ ዳግመኛ ስለ እናንተ ምጥ ይዞኛል።
20and I was wishing to be present with you now, and to change my voice, because I am in doubt about you.
20ስለ እናንተ አመነታለሁና አሁን በእናንተ ዘንድ ሆኜ ድምፄን ልለውጥ በወደድሁ።
21Tell me, ye who are willing to be under law, the law do ye not hear?
21እናንተ ከሕግ በታች ልትኖሩ የምትወዱ፥ ሕጉን አትሰሙምን? እስኪ ንገሩኝ።
22for it hath been written, that Abraham had two sons, one by the maid-servant, and one by the free-woman,
22አንዱ ከባሪያይቱ አንዱም ከጨዋይቱ የሆኑ ሁለት ልጆች ለአብርሃም እንደ ነበሩት ተጽፎአልና።
23but he who [is] of the maid-servant, according to flesh hath been, and he who [is] of the free-woman, through the promise;
23ነገር ግን የባሪያይቱ ልጅ እንደ ሥጋ ተወልዶአል፥ የጨዋይቱ ግን በተስፋው ቃል ተወልዶአል።
24which things are allegorized, for these are the two covenants: one, indeed, from mount Sinai, to servitude bringing forth, which is Hagar;
24ይህም ነገር ምሳሌ ነው፤ እነዚህ ሴቶች እንደ ሁለቱ ኪዳኖች ናቸውና። ከደብረ ሲና የሆነችው አንዲቱ ለባርነት ልጆችን ትወልዳለች፥ እርስዋም አጋር ናት።
25for this Hagar is mount Sinai in Arabia, and doth correspond to the Jerusalem that now [is], and is in servitude with her children,
25ይህችም አጋር በዓረብ ምድር ያለችው ደብረ ሲና ናት፤ አሁንም ያለችውን ኢየሩሳሌምን ትመስላለች፥ ከልጆችዋ ጋር በባርነት ናትና።
26and the Jerusalem above is the free-woman, which is mother of us all,
26ላይኛይቱ ኢየሩሳሌም ግን በነጻነት የምትኖር ናት እርስዋም እናታችን ናት።
27for it hath been written, `Rejoice, O barren, who art not bearing; break forth and cry, thou who art not travailing, because many [are] the children of the desolate — more than of her having the husband.`
27አንቺ የማትወልጅ መካን፥ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ አምጠሽ የማታውቂ፥ እልል በዪና ጩኺ፤ ባል ካላቱ ይልቅ የብቸኛይቱ ልጆች በዝተዋልና ተብሎ ተጽፎአል።
28And we, brethren, as Isaac, are children of promise,
28እኛም፥ ወንድሞች ሆይ፥ እንደ ይስሐቅ የተስፋ ቃል ልጆች ነን።
29but as then he who was born according to the flesh did persecute him according to the spirit, so also now;
29ነገር ግን እንደ ሥጋ የተወለደው እንደ መንፈስ የተወለደውን በዚያን ጊዜ እንዳሳደደው ዛሬም እንዲሁ ነው።
30but what saith the Writing? `Cast forth the maid-servant and her son, for the son of the maid-servant may not be heir with the son of the free-woman;`
30ነገር ግን መጽሐፍ ምን ይላል? የባሪያይቱ ልጅ ከጨዋይቱ ልጅ ጋር አይወርስምና ባሪያይቱን ከልጅዋ ጋር አውጣት።
31then, brethren, we are not a maid-servant`s children, but the free-woman`s.
31ስለዚህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ የጨዋይቱ ልጆች ነን እንጂ የባሪያይቱ አይደለንም።