1ወንድሞች ሆይ፥ ይህን ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ። አባቶቻችን ሁሉ ከደመና በታች ነበሩ ሁሉም በባሕር መካከል ተሻገሩ፤
1以史為鑒弟兄們,我不願意你們不知道,我們的祖宗都曾經在雲下,都曾經從海中經過,
2ሁሉም ሙሴን ይተባበሩ ዘንድ በደመናና በባሕር ተጠመቁ፤
2都曾經在雲裡在海裡受洗歸於摩西。
3ሁሉም ያን መንፈሳዊ መብል በሉ ሁሉም ያን መንፈሳዊ መጠጥ ጠጡ፤
3他們都吃了一樣的靈糧,
4ይከተላቸው ከነበረው ከመንፈሳዊ ዓለት ጠጥተዋልና፥ ያም ዓለት ክርስቶስ ነበረ።
4都喝了一樣的靈水;他們所喝的,是從那隨著他們的靈磐石那裡來的,這磐石就是基督。
5እግዚአብሔር ግን ከእነርሱ በሚበዙት ደስ አላለውም፥ በምድረ በዳ ወድቀዋልና።
5但他們大多數的人,都得不到 神的喜悅,因此他們都死在曠野。
6እነዚህም ክፉ ነገር እንደ ተመኙ እኛ ደግሞ እንዳንመኝ ይህ ምሳሌ ሆነልን።
6這些事都是我們的鑒戒,叫我們不要貪戀惡事,像他們那樣。
7ሕዝብም ሊበሉ ሊጠጡም ተቀመጡ ሊዘፍኑም ተነሡ ተብሎ እንደ ተጻፈ ከእነርሱ አንዳንዶቹ እንዳደረጉት ጣዖትን የምታመልኩ አትሁኑ።
7你們也不可拜偶像,像他們有些人那樣;正如經上所記:“人民坐下吃喝,起來玩樂。”
8ከእነርሱም አንዳንዶቹ እንደ ሴሰኑ በአንድ ቀንም ሁለት እልፍ ከሦስት ሺህ እንደ ወደቁ አንሴስን።
8我們也不可淫亂,像他們有些人那樣,一天就死了二萬三千人。
9ከእነርሱም አንዳንዶቹ ጌታን እንደ ተፈታተኑት በእባቦቹም እንደ ጠፉ ጌታን አንፈታተን።
9我們也不可試探主,像他們有些人那樣,結果就被蛇咬死了。
10ከእነርሱም አንዳንዶቹ እንዳንጎራጎሩ በሚያጠፋውም እንደ ጠፉ አታንጐርጕሩ።
10你們也不可發怨言,像他們有些人那樣,就被那毀滅者所滅。
11ይህም ሁሉ እንደ ምሳሌ ሆነባቸው፥ እኛንም የዘመናት መጨረሻ የደረሰብንን ሊገሥጸን ተጻፈ።
11這些事發生在他們身上,作為鑒戒,並且記下來,為了要警戒我們這些末世的人。
12ስለዚህ እንደ ቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ።
12所以,那自以為站得穩的,應當謹慎,免得跌倒。
13ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል።
13你們所受的試探,無非是人受得起的; 神是信實的,他必不容許你們受試探過於你們抵受得住的,而且在受試探的時候,必定給你們開一條出路,使你們能忍受得住。
14ስለዚህ፥ ወዳጆቼ ሆይ፥ ጣዖትን ከማምለክ ሽሹ።
14不可喝主的杯又喝鬼的杯所以,我所親愛的,你們要遠避拜偶像的事。
15ልባሞች እንደ መሆናችሁ እላለሁ፤ በምለው ነገር እናንተ ፍረዱ።
15我是對明白事理的人說的,我所說的你們要自己判斷。
16የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? የምንቆርሰውስ እንጀራ ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን?
16我們為福杯祝禱的時候,難道不是共享基督的血嗎?我們擘餅的時候,難道不是共享基督的身體嗎?
17አንድ እንጀራ ስለ ሆነ፥ እኛ ብዙዎች ስንሆን አንድ ሥጋ ነን፤ ሁላችን ያን አንዱን እንጀራ እንካፈላለንና።
17因為事實上只有一個餅,我們人數雖多,還是一個身體,因為我們都是分享同一個餅。
18በሥጋ የሆነውን እስራኤል ተመልከቱ፤ መሥዋዕቱን የሚበሉ የመሠዊያው ማኅበረተኞች አይደሉምን?
18你們看看以色列人,那些吃祭物的不就是與祭壇有分嗎?
19እንግዲህ ምን እላለሁ? ለጣዖት የተሠዋ ምናምን ነው እላለሁን? ወይስ ጣዖት ምናምን እንዲሆን እላለሁን?
19我說的是甚麼意思呢?偶像算得甚麼,還是祭過偶像的食物算得甚麼?
20አይደለም፤ ነገር ግን አሕዛብ የሚሠዉት ለአጋንንት እንዲሆን እንጂ ለእግዚአብሔር እንዳይሠዉ እላለሁ፤ ከአጋንንትም ጋር ማኅበረተኞች እንድትሆኑ አልወድም።
20我是說,教外人所祭的是鬼,不是獻給 神;我卻不願意你們與鬼來往。
21የጌታን ጽዋና የአጋንንትን ጽዋ ልትጠጡ አትችሉም፤ ከጌታ ማዕድና ከአጋንንት ማዕድ ልትካፈሉ አትችሉም።
21你們不能喝主的杯又喝鬼的杯,你們不能參加主的筵席又參加鬼的筵席。
22ወይስ ጌታን እናስቀናውን? እኛስ ከእርሱ ይልቅ እንበረታለንን?
22難道我們要激起主的忿怒嗎?我們比他更強嗎?
23ሁሉ ተፈቅዶልኛል፥ ሁሉ ግን የሚጠቅም አይደለም፤ ሁሉ ተፈቅዶልኛል፥ ነገር ግን ሁሉ የሚያንጽ አይደለም።
23凡事都要榮耀 神甚麼事情都可以作,但不是都有益處。甚麼事情都可以作,但不是都能造就人。
24እያንዳንዱ የባልንጀራውን ጥቅም እንጂ አንድ ስንኳ የራሱን ጥቅም አይፈልግ።
24人不要求自己的好處,卻要求別人的好處。
25በሥጋ ገበያ የሚሸጠውን ሁሉ ከሕሊና የተነሣ ሳትመራመሩ ብሉ፤
25肉食市場所賣的一切,你們只管吃,不要為了良心的緣故問甚麼,
26ምድርና በእርስዋ የሞላባት ሁሉ የጌታ ነውና።
26因為地和地上所充滿的都是屬於主的。
27ከማያምኑ ሰዎች አንዱም ቢጠራችሁ ልትሄዱም ብትወዱ ከሕሊና የተነሣ ሳትመራመሩ የሚያቀርቡላችሁን ሁሉ ብሉ።
27如果有不信的人邀請你們吃飯,你們也願意去,凡擺在你們面前的,都可以吃,不要為了良心的緣故問甚麼。
28ማንም ግን። ይህ ለጣዖት የተሠዋ ነው ቢላችሁ ከዚያ ካስታወቃችሁና ከሕሊና የተነሣ አትብሉ፤
28但是如果有人告訴你們:“這是獻過祭的食物。”那麼,為了那告訴你們的人,也為了良心的緣故,就不要吃。
29ስለ ባልንጀራህ ሕሊና እንጂ ስለ ገዛ ሕሊናህ አልናገርም። አርነቴ በሌላ ሰው ሕሊና የሚፈርድ Avረ ስለ ምንድር ነው?
29我說的良心,不是你的,而是他的。為甚麼我的自由要受別人的良心論斷呢?
30እኔም በጸጋ ብበላ፥ በነገሩ ስለማመሰግንበት ስለ ምን እሰደባለሁ?
30我若存著感恩的心吃了,為甚麼我因著我所感恩的食物被人毀謗呢?
31እንግዲህ የምትበሉ ወይም የምትጠጡ ብትሆኑ ወይም ማናቸውን ነገር ብታደርጉ ሁሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት።
31所以,你們或吃喝,或作甚麼,一切都要為 神的榮耀而行。
32እኔ ደግሞ ብዙዎቹ ይድኑ ዘንድ ለጥቅማቸው እንጂ የራሴን ጥቅም ሳልፈልግ በሁሉ ነገር ሰውን ሁሉ ደስ እንደማሰኝ፥ ለአይሁድም ለግሪክም ሰዎች ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንም ማሰናከያ አትሁኑ።
32無論是猶太人,是希臘人,是 神的教會,你們總不可使他們跌倒;
33就好像我所作的一切,都是要使大家喜悅,不是要求自己的好處,而是要求別人的好處,為了要使他們得救。