1ስለ መንፈሳዊ ነገርም፥ ወንድሞች ሆይ፥ ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ።
1屬靈的恩賜弟兄們,關於屬靈的恩賜,我不願意你們不明白。
2አሕዛብ ሳላችሁ በማናቸውም ጊዜ እንደምትመሩ ድምፅ ወደሌላቸው ወደ ጣዖታት እንደ ተወሰዳችሁ ታውቃላችሁ።
2你們知道,你們還是教外人的時候,總是受迷惑被引誘,去拜那不能說話的偶像。
3ስለዚህ ማንም በእግዚአብሔር መንፈስ ሲናገር። ኢየሱስ የተረገመ ነው የሚል እንደሌለ፥ በመንፈስ ቅዱስም ካልሆነ በቀር። ኢየሱስ ጌታ ነው ሊል አንድ እንኳ እንዳይችል አስታውቃችኋለሁ።
3所以我要你們知道,被 神的靈感動而說話的人,沒有一個會說“耶穌是可咒詛的”;除非是被聖靈感動,也沒有人能說“耶穌是主”。
4የጸጋም ስጦታ ልዩ ልዩ ነው መንፈስ ግን አንድ ነው፤
4恩賜有許多種,卻是同一位聖靈所賜的;
5አገልግሎትም ልዩ ልዩ ነው ጌታም አንድ ነው፤
5服事的職分有許多種,但是同一位主;
6አሠራርም ልዩ ልዩ ነው፥ ሁሉን በሁሉ የሚያደርግ እግዚአብሔር ግን አንድ ነው።
6工作的方式也有許多種,但仍是一位 神,是他在眾人裡面作成一切。
7ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን መግለጥ ለእያንዳንዱ ለጥቅም ይሰጠዋል።
7聖靈顯現在各人的身上,為的是要使人得著益處。
8ለአንዱ ጥበብን መናገር በመንፈስ ይሰጠዋልና፥ ለአንዱም በዚያው መንፈስ እውቀትን መናገር ይሰጠዋል፥
8有人藉著聖靈領受了智慧的言語,又有人靠著同一位聖靈領受了知識的言語,
9ለአንዱም በዚያው መንፈስ እምነት፥ ለአንዱም በአንዱ መንፈስ የመፈወስ ስጦታ፥ ለአንዱም ተአምራትን ማድረግ፥
9又有人因著同一位聖靈領受了信心,還有人因著這位聖靈領受了醫病的恩賜,
10ለአንዱም ትንቢትን መናገር፥ ለአንዱም መናፍስትን መለየት፥ ለአንዱም በልዩ ዓይነት ልሳን መናገር፥ ለአንዱም በልሳኖች የተነገረውን መተርጎም ይሰጠዋል፤
10另有人可以行神蹟,另有人可以講道,另有人可以辨別諸靈,也有人能說各種的方言,也有人能翻譯方言。
11ይህን ሁሉ ግን ያ አንዱ መንፈስ እንደሚፈቅድ ለእያንዳንዱ ለብቻው እያካፈለ ያደርጋል።
11這一切都是這同一位聖靈所作的,他按照自己的意思個別地分給各人。
12አካልም አንድ እንደ ሆነ ብዙም ብልቶች እንዳሉበት ነገር ግን የአካል ብልቶች ሁሉ ብዙዎች ሳሉ አንድ አካል እንደ ሆኑ፥ ክርስቶስ ደግሞ እንዲሁ ነው፤
12正如身體是一個,卻有許多肢體,而且肢體雖然很多,身體仍是一個;基督也是這樣。
13አይሁድ ብንሆን የግሪክ ሰዎችም ብንሆን ባሪያዎችም ብንሆን ጨዋዎችም ብንሆን እኛ ሁላችን በአንድ መንፈስ አንድ አካል እንድንሆን ተጠምቀናልና። ሁላችንም አንዱን መንፈስ ጠጥተናል።
13我們無論是猶太人,是希臘人,是作奴隸的,是自由的,都在那一位聖靈裡受了洗,成為一個身體,都飲了那一位聖靈。
14አካል ብዙ ብልቶች እንጂ አንድ ብልት አይደለምና።
14原來身體有許多肢體,並不是只有一個肢體。
15እግር። እኔ እጅ አይደለሁምና የአካል ክፍል አይደለሁም ብትል፥ ይህን በማለትዋ የአካል ክፍል መሆንዋ ይቀራልን?
15假如腳說:“我不是手,所以我不屬於身體。”它不能因此就不屬於身體。
16ጆሮም። እኔ ዓይን አይደለሁምና የአካል ክፍል አይደለሁም ቢል፥ ይህን በማለቱ የአካል ክፍል መሆኑ ይቀራልን?
16假如耳朵說:“我不是眼睛,所以我不屬於身體。”它也不能因此就不屬於身體。
17አካል ሁሉ ዓይን ቢሆን መስማት ወዴት በተገኘ? ሁሉም መስማት ቢሆን ማሽተት ወዴት በተገኘ?
17假如整個身體只是眼睛,怎樣聽呢?假如整個身體只是耳朵,怎樣聞味呢?
18አሁን ግን እግዚአብሔር እንደ ወደደ ብልቶችን እያንዳንዳቸው በአካል አድርጎአል።
18但現在 神按照自己的意思,把肢體一一放在身體上。
19ሁሉም አንድ ብልት ቢሆንስ አካል ወዴት በሆነ?
19假如所有的只是一個肢體,怎能算是身體呢?
20ዳሩ ግን አሁን ብልቶች ብዙዎች ናቸው አካል ግን አንድ ነው።
20但現在肢體雖然很多,身體卻只是一個。
21ዓይን እጅን። አታስፈልገኝም ልትለው አትችልም፥ ወይም ራስ ደግሞ እግሮችን። አታስፈልጉኝም ሊላቸው አይችልም።
21眼睛不能對手說:“我不需要你。”頭也不能對腳說:“我不需要你們。”
22ነገር ግን ደካሞች የሚመስሉ የአካል ብልቶች ይልቁን የሚያስፈልጉ ናቸው፤
22相反地,身體上那些似乎比較軟弱的肢體,更是不可缺少的。
23ከአካልም ብልቶች ያልከበሩ ሆነው የሚመስሉን በሚበዛ ክብር እናለብሳቸዋለን፥ በምናፍርባቸውም ብልቶቻችን ክብር ይጨመርላቸዋል፤
23我們認為身體上不大體面的部分,就更加要把它裝飾得體面;不大美觀的部分,就更加要使它美觀。
24ክብር ያላቸው ብልቶቻችን ግን ይህ አያስፈልጋቸውም። ነገር ግን ብልቶች እርስ በርሳቸው በትክክል ይተሳሰቡ ዘንድ እንጂ በአካል መለያየት እንዳይሆን፥ ለጎደለው ብልት የሚበልጥ ክብር እየሰጠ እግዚአብሔር አካልን አገጣጠመው።
24我們身體上美觀的部分,就不需要這樣了。但 神卻這樣把身體組成了:格外地把體面加給比較有缺欠的肢體,
26አንድም ብልት ቢሣቀይ ብልቶች ሁሉ ከእርሱ ጋር ይሣቀያሉ፤ አንድ ብልትም ቢከበር ብልቶች ሁሉ ከእርሱ ጋር ደስ ይላቸዋል።
25好使肢體能夠互相照顧,免得身體上有了分裂。
27እናንተም የክርስቶስ አካል ናችሁ እያንዳንዳችሁም ብልቶች ናችሁ።
26如果一個肢體受苦,所有的肢體就一同受苦;如果一個肢體得榮耀,所有的肢體就一同快樂。
28እግዚአብሔርም በቤተ ክርስቲያን አንዳንዶቹን አስቀድሞ ሐዋርያትን፥ ሁለተኛም ነቢያትን፥ ሦስተኛም አስተማሪዎችን፥ ቀጥሎም ተአምራት ማድረግን፥ ቀጥሎም የመፈወስን ስጦታ፥ እርዳታንም፥ አገዛዝንም፥ የልዩ ልዩ ዓይነት ልሳኖችንም አድርጎአል።
27你們就是基督的身體,並且每一個人都是作肢體的。
29ሁሉ ሐዋርያት ናቸውን? ሁሉስ ነቢያት ናቸውን? ሁሉስ አስተማሪዎች ናቸውን? ሁሉስ ተአምራትን ይሠራሉን?
28 神在教會裡所設立的,第一是使徒,第二是先知,第三是教師,其次是行神蹟的,再其次是有醫病恩賜的,幫助人的,治理事的,說各種方言的。
30ሁሉስ የመፈወስ ስጦታ አላቸውን? ሁሉስ በልሳኖች ይናገራሉን? ሁሉስ ይተረጉማሉን?
29難道都是使徒嗎?都是先知嗎?都是教師嗎?都是行神蹟的嗎?
31ነገር ግን የሚበልጠውን የጸጋ ስጦታ በብርቱ ፈልጉ። ደግሞም ከሁሉ የሚበልጥ መንገድ አሳያችኋለሁ።
30都是有醫病恩賜的嗎?都是說方言的嗎?都是翻譯方言的嗎?
31你們卻要熱切地追求那些更大的恩賜。現在我要把更高的道路指示你們。