Amharic: New Testament

聖經新譯本

Hebrews

12

1እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።
1專一注視耶穌所以,我們既然有這麼多的見證人,像雲彩圍繞著我們,就應該脫下各樣的拖累,和容易纏住我們的罪,以堅忍的心奔跑那擺在我們面前的賽程;
3በነፍሳችሁ ዝላችሁ እንዳትደክሙ፥ ከኃጢአተኞች በደረሰበት እንዲህ ባለ መቃወም የጸናውን አስቡ።
2專一注視耶穌,就是我們信心的創始者和完成者。他因為那擺在面前的喜樂,就忍受了十字架,輕看了羞辱,現在就坐在 神寶座的右邊。
4ከኃጢአት ጋር እየተጋደላችሁ ገና ደምን እስከ ማፍሰስ ድረስ አልተቃወማችሁም፤
3這位忍受罪人那樣頂撞的耶穌,你們要仔細思想,免得疲倦灰心。
5እንደ ልጆችም ከእናንተ ጋር። ልጄ ሆይ፥ የጌታን ቅጣት አታቅልል፥ በሚገሥጽህም ጊዜ አትድከም፤ ጌታ የሚወደውን ይቀጣዋልና፥ የሚቀበለውንም ልጅ ሁሉ ይገርፈዋል ብሎ የሚነጋገረውን ምክር ረስታችኋል።
4主必管教他所愛的你們與罪惡鬥爭,還沒有對抗到流血的地步;
7ለመቀጣት ታገሡ፤ እግዚአብሔር እንደ ልጆች ያደርግላችኋልና፤ አባቱ የማይቀጣው ልጅ ማን ነው?
5你們又忘記了那勸你們好像勸兒子的話,說:“我兒!你不可輕看主的管教,受責備的時候也不要灰心;
8ነገር ግን ሁሉ የቅጣት ተካፋይ ሆኖአልና ያለ ቅጣት ብትኖሩ ዲቃላዎች እንጂ ልጆች አይደላችሁም።
6因為主所愛的,他必管教,他又鞭打所收納的每一個兒子。”
9ከዚህም በላይ የቀጡን የሥጋችን አባቶች ነበሩን እናፍራቸውም ነበር፤ እንዴትስ ይልቅ ለመናፍስት አባት አብልጠን ልንገዛና በሕይወት ልንኖር በተገባን?
7為了接受管教,你們要忍受,因為 神待你們好像待兒子一樣;哪有兒子不受父親管教的呢?
10እነርሱ መልካም ሆኖ እንደ ታያቸው ለጥቂት ቀን ይቀጡን ነበርና፥ እርሱ ግን ከቅድስናው እንድንካፈል ለጥቅማችን ይቀጣናል።
8作兒子的都受過管教。如果你們沒有受管教,就是私生子,不是兒子了。
11ቅጣት ሁሉ ለጊዜው የሚያሳዝን እንጂ ደስ የሚያሰኝ አይመስልም፥ ዳሩ ግን በኋላ ለለመዱት የሰላምን ፍሬ እርሱም ጽድቅን ያፈራላቸዋል።
9還有,肉身的父親管教我們,我們尚且敬重他們;何況那萬靈的父,我們不是更要順服他而得生嗎?
12ስለዚህ የላሉትን እጆች የሰለሉትንም ጉልበቶች አቅኑ፤
10肉身的父親照著自己的意思管教我們,只有短暫的日子;唯有 神管教我們,是為著我們的好處,使我們在他的聖潔上有分。
13ያነከሰውም እንዲፈወስ እንጂ እንዳይናጋ፥ ለእግራችሁ ቅን መንገድ አድርጉ።
11但是一切管教,在當時似乎不覺得快樂,反覺得痛苦;後來卻為那些經過這種操練的人,結出平安的果子來,就是義。
14ከሰው ሁሉ ጋር ሰላምን ተከታተሉ ትቀደሱም ዘንድ ፈልጉ፥ ያለ እርሱ ጌታን ሊያይ የሚችል የለምና።
12把下垂的手發軟的腿挺起來所以,你們要把下垂的手和發軟的腿挺直起來;
15የእግዚአብሔር ጸጋ ለማንም እንዳይጎድለው፥ ብዙዎቹም የሚረክሱበት አንድ መራራ ሥር ወደ ላይ በቅሎ እንዳያስጨንቅ፥ ሴሰኛም የሚሆን እንዳይገኝ፥
13也要把你們所走的道路修直,使瘸子不至於扭腳,反而得到復原。
16ወይም ስለ አንድ መብል በኵርነቱን እንደ ሸጠ እንደ ዔሳው ለዚህ ዓለም የሚመች ሰው እንዳይሆን ተጠንቀቁ።
14你們要竭力尋求與眾人和睦,並且要竭力追求聖潔。如果沒有聖潔,誰也不能見主。
17ከዚያ በኋላ እንኳ በረከቱን ሊወርስ በወደደ ጊዜ እንደ ተጣለ ታውቃላችሁና፤ በእንባ ተግቶ ምንም ቢፈልገው ለንስሐ ስፍራ አላገኘምና።
15你們要小心,免得有人失去了 神的恩典;免得有苦根長起來纏繞你們,因而污染了許多人;
18ሊዳሰስ ወደሚችል ወደሚቃጠልም እሳት ወደ ጭጋግም ወደ ጨለማም ወደ ዐውሎ ነፋስም ወደ መለከት ድምፅም ወደ ቃሎችም ነገር አልደረሳችሁምና፤
16又免得有人成為淫亂的和貪戀世俗的,好像以掃一樣,為了一點點食物,竟把自己長子的名分出賣了。
19ያንም ነገር የሰሙት ሌላ ቃል እንዳይጨመርባቸው ለመኑ፤
17你們知道,後來以掃想要承受祝福,卻被拒絕了;他雖然帶著眼淚尋求,還是沒有反悔的餘地。
20እንስሳ እንኳ ተራራውን ቢነካ ተወግሮ ይሙት የምትለውን ትእዛዝ ሊታገሡ አልቻሉምና፤
18不可違背那警戒人的 神你們不是來到那座摸得著的山。那裡有烈火、密雲、幽暗、暴風、
21ሙሴም። እጅግ እፈራለሁ እንቀጠቀጥማለሁ እስኪል ድረስ የሚታየው እጅግ የሚያስፈራ ነበር፤
19號筒的響聲和說話的聲音;那些聽見這聲音的人,都請求 神不要再向他們多說話;
22ነገር ግን ወደ ጽዮን ተራራና ወደ ሕያው እግዚአብሔር ከተማ ደርሳችኋል፥ ወደ ሰማያዊቱም ኢየሩሳሌም፥ በደስታም ወደ ተሰበሰቡት ወደ አእላፋት መላእክት፥
20因為他們擔當不起那命令:“就是走獸挨近這山,也要用石頭把牠打死。”
23በሰማያትም ወደ ተጻፉ ወደ በኵራት ማኅበር፥ የሁሉም ዳኛ ወደሚሆን ወደ እግዚአብሔር፥ ፍጹማንም ወደ ሆኑት ወደ ጻድቃን መንፈሶች፥
21當時,顯出的景象是那麼可怕,連摩西也說:“我非常恐懼戰兢。”
24የአዲስም ኪዳን መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ፥ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ መርጨት ደም ደርሳችኋል።
22你們卻是來到錫安山和永活的 神的城,就是天上的耶路撒冷;在那裡有千萬的天使聚集,
25ለሚናገረው እምቢ እንዳትሉ ተጠንቀቁ፤ እነዚያ በምድር ላስረዳቸው እምቢ ባሉ ጊዜ ካላመለጡ፥ ከሰማይ ከመጣው ፈቀቅ የምንል እኛስ እንዴት እናመልጣለን?
23有名字登記在天上眾長子的教會,有審判眾人的 神,有被成全的義人的靈魂,
26በዚያም ጊዜ ድምፁ ምድርን አናወጠ፥ አሁን ግን። አንድ ጊዜ ደግሜ እኔ ሰማይን አናውጣለሁ እንጂ ምድርን ብቻ አይደለም ብሎ ተስፋ ሰጥቶአል።
24有新約的中保耶穌,還有他所灑的血。這血所傳的信息比亞伯的血所傳的更美。
27ዳሩ ግን። አንድ ጊዜ ደግሜ የሚል ቃል፥ የማይናወጡት ጸንተው እንዲኖሩ፥ የሚናወጡት የተፈጠሩ እንደሚሆኑ ይለወጡ ዘንድ ያሳያል።
25你們要謹慎,不要棄絕那位說話的,因為從前的人棄絕了那位在地上警戒他們的,尚且不能逃罪;何況現在我們背棄那位從天上警戒我們的呢?
28ስለዚህ የማይናወጥን መንግሥት ስለምንቀበል በማክበርና በፍርሃት እግዚአብሔርን ደስ እያሰኘን የምናመልክበትን ጸጋ እንያዝ፤
26當時他的聲音震動了地;現在他卻應許說:“下一次,我不但要震動地,還要震動天。”
29አምላካችን በእውነት የሚያጠፋ እሳት ነውና።
27“下一次”這句話,是表明那些被震動的,要像被造之物那樣被除去,好使那些不能震動的可以留存,
28因此,我們既然領受了不能震動的國,就應該感恩,照著 神所喜悅的,用虔誠敬畏的心事奉他;
29因為我們的 神是烈火。