1እንግዲህ ወደ ዕረፍቱ ለመግባት ተስፋ ገና ቀርቶልን ከሆነ፥ ምናልባት ከእናንተ ማንም የማይበቃ መስሎ እንዳይታይ እንፍራ።
1信的人可以進入安息所以,那進入安息的應許,既然還給我們留著,我們就應該戰戰兢兢,恐怕我們中間有人像是被淘汰了。
2ለእነዚያ ደግሞ እንደ ተነገረ ለእኛ የምስራች ተሰብኮልናልና፤ ዳሩ ግን የሰሙት ቃል ከሰሚዎቹ ጋር በእምነት ስላልተዋሐደ አልጠቀማቸውም።
2因為有福音傳給我們,像傳給他們一樣,只是他們所聽見的道,對他們沒有益處,因為他們沒有用信心與所聽見的打成一片(“沒有用信心與所聽見的打成一片”,有古卷作“沒有用信心與聽從這道的人打成一片”)。
3ሥራው ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ምንም እንኳ ቢፈጸም። እንዲህ። ወደ ዕረፍቴ አይገቡም ብዬ በቁጣዬ ማልሁ እንዳለ፥ እኛስ ያመንን ወደ ዕረፍቱ እንገባለን።
3然而我們信了的人,就可以進入那安息。正如 神所說:“我在烈怒中起誓說,他們絕不可進入我的安息!”其實 神的工作,從創立世界以來已經完成了。
4ስለ ሰባተኛው ቀን በአንድ ስፍራ። እግዚአብሔርም በሰባተኛው ቀን ከሥራው ሁሉ ዐረፈ ብሎአልና፤
4因為論到第七日,他在聖經某一處說:“在第七日 神歇了他的一切工作。”
5በዚህ ስፍራም ደግሞ። ወደ ዕረፍቴ አይገቡም።
5但在這裡又說:“他們絕不可進入我的安息。”
6እንግዲህ አንዳንዶች በዚያ እንዲገቡ ስለ ቀሩ፥ ቀድሞም የምስራች የተሰበከላቸው ባለመታዘዝ ጠንቅ ስላልገቡ።
6既然這安息還留著要讓一些人進去,但那些以前聽過福音的人,因為不順從不得進去;
7ዛሬ ድምፁን ብትሰሙት ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ በፊት እንደ ተባለ፥ ይህን ከሚያህል ዘመን በኋላ በዳዊት ሲናገር። ዛሬ ብሎ አንድ ቀን እንደ ገና ይቀጥራል።
7所以 神就再定一個日子,就是過了很久以後,藉著大衛所說的“今天”,就像前面引用過的:“如果你們今天聽從他的聲音,就不要硬著心。”
8ኢያሱ አሳርፎአቸው ኖሮ ቢሆንስ፥ ከዚያ በኋላ ስለ ሌላ ቀን ባልተናገረ ነበር።
8如果約書亞已經使他們享受了安息, 神後來就不會再提到別的日子了。
9እንግዲያስ የሰንበት ዕረፍት ለእግዚአብሔር ሕዝብ ቀርቶላቸዋል።
9這樣看來,為了 神的子民,必定另外有一個“安息日”的安息保留下來。
10ወደ ዕረፍቱ የገባ፥ እግዚአብሔር ከሥራው እንዳረፈ፥ እርሱ ደግሞ ከሥራው አርፎአልና።
10因為那進入 神安息的人,就歇了自己的工作,好像 神歇了自己的工作一樣。
11እንግዲህ እንደዚያ እንደ አለመታዘዝ ምሳሌ ማንም እንዳይወድቅ ወደዚያ ዕረፍት ለመግባት እንትጋ።
11所以,我們要竭力進入那安息,免得有人隨著那不順從的樣子就跌倒了。
12የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል፤
12 神的道是活的、有效的 神的道是活的,是有效的,比一切兩刃的劍更鋒利,甚至可以刺入剖開靈與魂,關節與骨髓,並且能夠辨明心中的思想和意念。
13እኛን በሚቆጣጠር በእርሱ ዓይኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተራቆተና የተገለጠ ነው እንጂ፥ በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም።
13被造的在 神面前沒有一樣不是顯明的,萬有在他的眼前都是赤露敞開的;我們必須向他交帳。
14እንግዲህ በሰማያት ያለፈ ትልቅ ሊቀ ካህናት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ስላለን፥ ጸንተን ሃይማኖታችንን እንጠብቅ።
14我們的大祭司耶穌我們既然有一位偉大的、經過了眾天的大祭司,就是 神的兒子耶穌,就應該堅持所宣認的信仰。
15ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ፥ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንም።
15因為我們的大祭司並不是不能同情我們的軟弱,他像我們一樣,也曾在各方面受過試探,只是他沒有犯罪。
16እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ።
16所以,我們只管坦然無懼地來到施恩的寶座前,為的是要領受憐憫,得到恩惠,作為及時的幫助。