1ሊቀ ካህናት ሁሉ ስለ ኃጢአት መባንና መስዋዕትን ሊያቀርብ ከሰው ተመርጦ ለእግዚአብሔር በሆነው ነገር ሁሉ ስለ ሰው ይሾማልና፤
1每一個大祭司都是從人間選出來,奉派替人辦理與 神有關的事,為的是要獻上禮物和贖罪的祭物。
2እርሱ ራሱም ደግሞ ድካምን ስለሚለብስ፥ ላልተማሩትና ለሚስቱት ሊራራላቸው ይችላል፤
2他能夠溫和地對待那些無知和迷誤的人,因為他自己也被軟弱所困。
3በዚህም ምክንያት ስለ ሕዝብ እንደሚያቀርብ እንዲሁ ስለ ራሱ ደግሞ መስዋዕትን ስለ ኃጢአት ሊያቀርብ ይገባዋል።
3因此,他怎樣為人民的罪獻祭,也應該怎樣為自己的罪獻祭。
4እንደ አሮንም በእግዚአብሔር ከተጠራ በቀር ማንም ክብሩን ለራሱ የሚወስድ የለም።
4沒有人可以自己取得這大祭司的尊榮,只有像亞倫一樣,蒙 神選召的才可以。
5እንዲሁ ክርስቶስ ደግሞ ሊቀ ካህናት ሊሆን ራሱን አላከበረም ነገር ግን። አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ ያለው እርሱ ነው፤
5照樣,基督也沒有自己爭取作大祭司的尊榮,而是曾經對他說:“你是我的兒子,我今日生了你”的 神榮耀了他;
6እንደዚህም በሌላ ስፍራ ደግሞ። አንተ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ካህን ነህ ይላል።
6就像他在另一處說:“你是照著麥基洗德的體系,永遠作祭司的。”
7እርሱም በስጋው ወራት ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፥ እግዚአብሔርንም ስለ መፍራቱ ተሰማለት፤
7基督在世的時候,曾經流淚大聲禱告懇求那位能救他脫離死亡的 神;因著他的敬虔,就蒙了應允。
8ምንም ልጅ ቢሆን፥ ከተቀበለው መከራ መታዘዝን ተማረ፤
8他雖然是兒子,還是因著所受的苦難學會了順從。
9ከተፈጸመም በኋላ በእግዚአብሔር እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ሊቀ ካህናት ተብሎ ስለ ተጠራ፥ ለሚታዘዙለት ሁሉ የዘላለም መዳን ምክንያት ሆነላቸው።
9他既然順從到底,就成了所有順從他的人得到永遠救恩的根源;
11ስለ እርሱም የምንናገረው ብዙ ነገር አለን፥ ጆሮቻችሁም ስለ ፈዘዙ በቃል ልንተረጕመው ጭንቅ ነው።
10而且蒙 神照著麥基洗德的體系,稱他為大祭司。
12ከጊዜው የተነሳ አስተማሪዎች ልትሆኑ ሲገባችሁ፥ አንድ ሰው ስለ እግዚአብሔር ቃላት መጀመሪያ ያለውን የሕፃንነትን ትምህርት እንዲያስተምራችሁ እንደ ገና ያስፈልጋችኋልና፤ የሚያስፈልጋችሁም ወተት ነው እንጂ ጠንካራ ምግብ አይደለም።
11勸勉信徒要長大成人論到這些事,我們有很多話要說,可是很難解釋;因為你們已經遲鈍了,聽不進去。
13ወተት የሚጋት ሁሉ ሕፃን ስለ ሆነ የጽድቅን ቃል አያውቅምና፤
12到這個時候,你們應該已經作老師了;可是你們還需要有人再把 神道理的初步教導你們。你們成了只能吃奶而不能吃乾糧的人!
14ጠንካራ ምግብ ግን መልካሙንና ክፉውን ለመለየት በስራቸው የለመደ ልቡና ላላቸው ለፍጹማን ሰዎች ነው።
13凡是吃奶的,還是個嬰孩,對公義的道理沒有經歷;
14只有長大成人的,才能吃乾糧,他們的官能因為操練純熟,就能分辨是非了。