Amharic: New Testament

聖經新譯本

John

14

1ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ።
1耶穌是道路真理生命“你們心裡不要難過,你們應當信 神,也應當信我。
2በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና፤
2在我父的家裡,有許多住的地方;如果沒有,我怎麼會告訴你們我去是要為你們預備地方呢?(下半節或譯:“如果沒有,我早就對你們說了,因為我去是為你們預備地方。”)
3ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ፥ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ።
3我若去為你們預備地方,就必再來接你們到我那裡去,好使我在哪裡,你們也在哪裡。
4ወደምሄድበትም ታውቃላችሁ፥ መንገዱንም ታውቃላችሁ።
4我去的地方,你們知道那條路。”
5ቶማስም። ጌታ ሆይ፥ ወደምትሄድበት አናውቅም፤ እንዴትስ መንገዱን እናውቃለን? አለው።
5多馬說:“主啊,我們不知道你去的地方,怎能知道那條路呢?”
6ኢየሱስም። እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።
6耶穌對他說:“我就是道路、真理、生命,如果不是藉著我,沒有人能到父那裡去。
7እኔንስ ብታውቁኝ አባቴን ደግሞ ባወቃችሁ ነበር። ከአሁንም ጀምራችሁ ታውቁታላችሁ አይታችሁትማል አለው።
7如果你們認識我,就必認識我的父;從今以後,你們認識他,並且看見了他。”
8ፊልጶስ። ጌታ ሆይ፥ አብን አሳየንና ይበቃናል አለው።
8腓力說:“主啊,請把父顯示給我們,我們就滿足了。”
9ኢየሱስም አለው። አንተ ፊልጶስ፥ ይህን ያህል ዘመን ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን? እኔን ያየ አብን አይቶአል፤ እንዴትስ አንተ። አብን አሳየን ትላለህ?
9耶穌說:“腓力,我跟你們在一起這麼久了,你還不認識我嗎?那看見了我的就是看見了父,你怎麼還說‘把父顯示給我們’呢?
10እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ አታምንምን? እኔ የምነግራችሁን ቃል ከራሴ አልናገረውም፤ ነገር ግን በእኔ የሚኖረው አብ እርሱ ሥራውን ይሠራል።
10你不信我是在父裡面,父是在我裡面嗎?我對你們說的話,不是憑著自己說的,而是住在我裡面的父作他自己的事。
11እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ እመኑኝ፤ ባይሆንስ ስለ ራሱ ስለ ሥራው እመኑኝ።
11你們應當信我是在父裡面,父是在我裡面;不然,也要因我所作的而相信。
12እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል፥
12我實實在在告訴你們,我所作的事,信我的人也要作,並且要作比這些更大的,因為我往父那裡去。
13እኔ ወደ አብ እሄዳለሁና፤ አብም ስለ ወልድ እንዲከበር በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ።
13你們奉我的名無論求甚麼,我必定成全,使父在子的身上得著榮耀。
14ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ።
14你們若奉我的名向我求甚麼,我必定成全。
15ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤
15耶穌求父賜下保惠師“如果你們愛我,就要遵守我的命令。
17እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ።
16我要請求父,他就會賜給你們另一位保惠師,使他跟你們永遠在一起。
18ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ።
17這保惠師就是真理的靈,世人不能接受他,因為看不見他,也不認識他。你們卻認識他,因為他跟你們住在一起,也要在你們裡面。
19ገና ጥቂት ዘመን አለ ከዚህም በኋላ ዓለም አያየኝም፤ እናንተ ግን ታዩኛላችሁ፤ እኔ ሕያው ነኝና እናንተ ደግሞ ሕያዋን ትሆናላችሁ።
18我不會撇下你們為孤兒,我要回到你們這裡來。
20እኔ በአባቴ እንዳለሁ እናንተም በእኔ እንዳላችሁ እኔም በእናንተ እንዳለሁ በዚያን ቀን ታውቃላችሁ።
19不久以後,世人不再看見我,你們卻要看見我,因為我活著,你們也要活著。
21ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለችው የሚጠብቃትም የሚወደኝ እርሱ ነው፤ የሚወደኝንም አባቴ ይወደዋል እኔም እወደዋለሁ ራሴንም እገልጥለታለሁ።
20到那日,你們就知道我是在我父裡面,你們是在我裡面,我也在你們裡面。
22የአስቆሮቱ ያይደለ ይሁዳ። ጌታ ሆይ፥ ለዓለም ሳይሆን ራስህን ለእኛ ልትገልጥ ያለህ እንዴት ነው? አለው።
21那領受我的命令,並且遵守的,就是愛我的;愛我的,我父必定愛他,我也要愛他,並且要親自向他顯現。”
23ኢየሱስም መለሰ አለውም። የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል ወደ እርሱም እንመጣለን በእርሱም ዘንድ መኖሪያ እናደርጋለን።
22猶大(不是加略人猶大)對耶穌說:“主啊,你為甚麼要親自向我們顯現,不向世人顯現呢?”
24የማይወደኝ ቃሌን አይጠብቅም፤ የምትሰሙትም ቃል የላከኝ የአብ ነው እንጂ የእኔ አይደለም።
23耶穌回答:“人若愛我,就要遵守我的話,我父必定愛他,並且我們要到他那裡去,跟他住在一起。
25ከእናንተ ዘንድ ስኖር ይህን ነግሬአችኋለሁ፤
24不愛我的,就不會遵守我的話。你們所聽見的道,不是我的,而是那差我來的父的道。
26አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል።
25“我還跟你們在一起的時候,就對你們講了這些事。
27ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም።
26但保惠師,就是父因我的名要差來的聖靈,他要把一切事教導你們,也要使你們想起我對你們所說過的一切話。
28እኔ እሄዳለሁ ወደ እናንተም እመጣለሁ እንዳልኋችሁ ሰማችሁ። የምትወዱኝስ ብትሆኑ ከእኔ አብ ይበልጣልና ወደ አብ በመሄዴ ደስ ባላችሁ ነበር።
27我留下平安給你們,我把自己的平安賜給你們;我給你們的,不像世界所給的。你們心裡不要難過,也不要恐懼。
29ከሆነም በኋላ ታምኑ ዘንድ አሁን አስቀድሞ ሳይሆን። ነግሬአችኋለሁ።
28你們聽見我對你們說過:‘我去,但還要回到你們這裡來。’你們若愛我,就要喜樂,因為我到父那裡去,又因為父是比我大的。
30ከእንግዲህ ወዲህ ከእናንተ ጋር ብዙ አልናገርም፥ የዚህ ዓለም ገዥ ይመጣልና፤ በእኔ ላይም አንዳች የለውም፤
29現在事情還沒有發生,我就已經告訴你們,使你們在事情發生的時候可以相信。
31ነገር ግን አብን እንድወድ ዓለም ሊያውቅ፥ አብም እንዳዘዘኝ፥ እንዲሁ አደርጋለሁ። ተነሡ፤ ከዚህ እንሂድ።
30我不會再跟你們講很多的事,因為這世界的統治者將到;他在我身上毫無作用,
31但這些事是要使世人知道我愛父,並且知道父怎樣吩咐了我,我就怎樣作。起來,我們走吧!”