1እንዳትሰናከሉ ይህን ተናግሬአችኋለሁ።
1“我把這些事告訴了你們,使你們不致後退。
2ከምኵራባቸው ያወጡአችኋል፤ ከዚህ በላይ ደግሞ የሚገድላችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን እንደሚያገለግል የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል።
2人要把你們趕出會堂;並且時候要到,所有要殺害你們的人,以為這樣就是事奉 神。
3ይህንም የሚያደርጉባችሁ አብንና እኔን ስላላወቁ ነው።
3他們要作這些事,因為他們不認識父,也不認識我。
4ነገር ግን ጊዜው ሲደርስ እኔ እንደ ነገርኋችሁ ታስቡ ዘንድ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። ከእንናንተም ጋር ስለ ነበርሁ በመጀመሪያ ይህን አልነገርኋችሁም።
4我把這些事告訴了你們,讓你們到了那個時候,可以想起我告訴過你們了。我起初沒有把這些事告訴你們,因為我跟你們在一起。
5አሁን ግን ወደ ላከኝ እሄዳለሁ ከእናንተም። ወዴት ትሄዳለህ? ብሎ የሚጠይቀኝ የለም።
5聖靈的工作“現在我要到那差我來的那裡去,你們中間並沒有人問:‘你到哪裡去?’
6ነገር ግን ይህን ስለ ተናገርኋችሁ ኀዘን በልባችሁ ሞልቶአል።
6然而因為我把這些事告訴了你們,你們心裡就充滿憂愁。
7እኔ ግን እውነት እነግራችኋለሁ፤ እኔ እንድሄድ ይሻላችኋል። እኔ ባልሄድ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔ ብሄድ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ።
7但我要把實情告訴你們,我去是對你們有益的。如果我不去,保惠師就不會到你們這裡來;我若去了,就會差他到你們這裡來。
8እርሱም መጥቶ ስለ ኃጢአት ስለ ጽድቅም ስለ ፍርድም ዓለምን ይወቅሳል፤
8他來了,就要在罪、在義、在審判各方面指證世人的罪。
9ስለ ኃጢአት፥ በእኔ ስለማያምኑ ነው፤ ስለ ጽድቅም፥ ወደ አብ ስለምሄድ ከዚህም በኋላ ስለማታዩኝ ነው፤
9在罪方面,是因為他們不信我;
11ስለ ፍርድም፥ የዚህ ዓለም ገዥ ስለ ተፈረደበት ነው።
10在義方面,是因為我到父那裡去,你們就再看不見我;
12የምነግራችሁ ገና ብዙ አለኝ፥ ነገር ግን አሁን ልትሸከሙት አትችሉም።
11在審判方面,是因為這世界的統治者已經受了審判。
13ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል።
12“我還有許多事要告訴你們,可是你們現在擔當不了;
14እርሱ ያከብረኛል፥ ለእኔ ካለኝ ወስዶ ይነግራችኋልና።
13只等真理的靈來了,他要引導你們進入一切真理。他不是憑著自己說話,而是把他聽見的都說出來,並且要把將來的事告訴你們。
15ለአብ ያለው ሁሉ የእኔ ነው፤ ስለዚህ። ለእኔ ካለኝ ወስዶ ይነግራችኋል አልሁ።
14他要榮耀我,因為他要把從我那裡所領受的告訴你們。
16ጥቂት ጊዜ አለ፥ አታዩኝምም፤ ደግሞም ጥቂት ጊዜ አለ፥ ታዩኛላችሁም፥ እኔ ወደ አብ እሄዳለሁና።
15父所有的一切,都是我的;所以我說,他要把從我那裡所領受的告訴你們。
17ከደቀ መዛሙርቱም አንዳንዶቹ እርስ በርሳቸው። ጥቂት ጊዜ አለ፥ አታዩኝምም፤ ደግሞም ጥቂት ጊዜ አለ፥ ታዩኛላችሁም፤ ደግሞ። ወደ አብ እሄዳለሁና የሚለን ይህ ምንድር ነው? ተባባሉ።
16你們的憂愁要變為喜樂“不久,你們不會再看見我;再過不久,你們還要看見我。”
18እንግዲህ። ጥቂት የሚለው ይህ ምንድር ነው? የሚናገረውን አናውቅም አሉ።
17於是他的門徒中有幾個彼此說:“他對我們說:‘不久,你們不會看見我;再過不久,你們還要看見我。’又說:‘因為我到父那裡去。’這是甚麼意思呢?”
19ኢየሱስም ሊጠይቁት እንደ ወደዱ አውቆ እንዲህ አላቸው። ጥቂት ጊዜ አለ፥ አታዩኝምም፤ ደግሞም ጥቂት ጊዜ አለ፥ ታዩኛላችሁ ስላልሁ፥ ስለዚህ እርስ በርሳችሁ ትመራመራላችሁን?
18他們又說:“他所說的‘不久’,是甚麼意思呢?我們不曉得他在講甚麼。”
20እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ እናንተ ታለቅሳለችሁ ሙሾም ታወጣላችሁ፥ ዓለም ግን ደስ ይለዋል፤ እናንተም ታዝናላችሁ፥ ነገር ግን ኀዘናችሁ ወደ ደስታ ይለወጣል።
19耶穌知道他們想問他,就說:“我所說的‘不久,你們不會看見我;再過不久,你們還要看見我’,你們為了這話彼此議論嗎?
21ሴት በምትወልድበት ጊዜ ወራትዋ ስለ ደረሰ ታዝናለች፤ ነገር ግን ሕፃን ከወለደች በኋላ፥ ሰው በዓለም ተወልዶአልና ስለ ደስታዋ መከራዋን ኋላ አታስበውም።
20我實實在在告訴你們,你們要痛哭哀號,世人卻要歡喜;你們要憂愁,但你們的憂愁要變為喜樂。
22እንግዲህ እናንተ ደግሞ አሁን ታዝናላችሁ፤ ነገር ግን እንደ ገና አያችኋለሁ ልባችሁም ደስ ይለዋል፥ ደስታችሁንም የሚወስድባችሁ የለም።
21婦人生產的時候會有憂愁,因為她的時候到了;但生了孩子以後,就不再記住那痛苦了,因為歡喜有一個人生到世上來。
23በዚያን ቀንም ከእኔ አንዳች አትለምኑም። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል።
22現在你們也有憂愁;但我要再見你們,你們的心就會喜樂,你們的喜樂是沒有人能夠奪去的。
24እስከ አሁን በስሜ ምንም አልለመናችሁም፤ ደስታችሁ ፍጹም እንዲሆን ለምኑ ትቀበሉማላችሁ።
23到了那天,你們甚麼也不會問我了。我實實在在告訴你們,你們奉我的名無論向父求甚麼,他必定賜給你們。
25ይህን በምሳሌ ነግሬአችኋለሁ፤ ነገር ግን ስለ አብ ለእናንተ በግልጥ የምናገርበት እንጂ ከዚያ ወዲያ በምሳሌ የማልናገርበት ሰዓት ይመጣል።
24你們向來沒有奉我的名求甚麼;現在你們祈求,就必定得著,讓你們的喜樂滿溢。
26በዚያን ቀን በስሜ ትለምናላችሁ፤ እኔም ስለ እናንተ አብን እንድለምን የምላችሁ አይደለሁም፤
25耶穌已經勝過世界“我用譬喻對你們說了這些事,時候要到,我不再用譬喻對你們說了,而是把關於父的事明明白白告訴你們。
27እናንተ ስለ ወደዳችሁኝ ከእግዚአብሔርም ዘንድ እኔ እንደ ወጣሁ ስላመናችሁ አብ እርሱ ራሱ ይወዳችኋልና።
26到了那天,你們要奉我的名祈求,我不是說我要為你們請求父;
28ከአብ ወጥቼ ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤ ደግሞ ዓለምን እተወዋለሁ ወደ አብም እሄዳለሁ።
27父自己愛你們,因為你們已經愛我,並且信我是從 神那裡來的。
29ደቀ መዛሙርቱ። እነሆ፥ አሁን በግልጥ ትናገራለህ በምሳሌም ምንም አትነግርም።
28我從父那裡來,到了這世界;我又離開這世界,到父那裡去。”
30ሁሉን እንድታውቅ ማንምም ሊጠይቅህ እንዳትፈልግ አሁን እናውቃለን፤ ስለዚህ ከእግዚአብሔር እንደ ወጣህ እናምናለን አሉት።
29門徒說:“你看,現在你是明說,不是用譬喻說了。
31ኢየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው። አሁን ታምናላችሁን?
30現在我們知道你是無所不知的,不需要人向你發問。因此,我們信你是從 神那裡來的。”
32እነሆ፥ እያንዳንዳችሁ ወደ ቤት የምትበታተኑበት እኔንም ለብቻዬ የምትተዉበት ሰዓት ይመጣል፥ አሁንም ደርሶአል፤ ነገር ግን አብ ከእኔ ጋር ስለ ሆነ ብቻዬን አይደለሁም።
31耶穌對他們說:“現在你們信嗎?
33በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ።
32看哪,時候要到,而且已經到了,你們要分散,各人到自己的地方去,只留下我獨自一個人。其實我不是獨自一個人,因為有父與我同在。
33我把這些事告訴你們,是要使你們在我裡面有平安。在世上你們有患難,但你們放心,我已經勝了這世界。”