1ኢየሱስም ይህን ተናግሮ ወደ ሰማይ ዓይኖቹን አነሣና እንዲህ አለ። አባት ሆይ፥ ሰዓቱ ደርሶአል፤ ልጅህ ያከብርህ ዘንድ፥ በሥጋም ሁሉ ላይ ሥልጣን እንደ ሰጠኸው፥ ለሰጠኸው ሁሉ የዘላለምን ሕይወት ይሰጣቸው ዘንድ ልጅህን አክብረው።
1耶穌臨別為門徒禱告耶穌講完了這些話,就舉目望天,說:“父啊,時候到了,求你榮耀你的兒子,讓兒子也榮耀你,
3እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት።
2正如你把管理全人類的權柄給了他,使他賜永生給你所賜給他的人。
4እኔ ላደርገው የሰጠኸኝን ሥራ ፈጽሜ በምድር አከበርሁህ፤
3認識你是獨一的真神,並且認識你所差來的耶穌基督,這就是永生。
5አሁንም፥ አባት ሆይ፥ ዓለም ሳይፈጠር በአንተ ዘንድ በነበረኝ ክብር አንተ በራስህ ዘንድ አክብረኝ።
4我在地上已經榮耀了你,你交給我要作的工,我已經完成了。
6ከዓለም ለሰጠኸኝ ሰዎች ስምህን ገለጥሁላቸው። የአንተ ነበሩ ለእኔም ሰጠሃቸው፤
5父啊,現在讓我在你自己面前得著榮耀,就是在創世以前我與你同享的榮耀。
7ቃልህንም ጠብቀዋል። የሰጠኸኝ ሁሉ ከአንተ እንደ ሆነ አሁን ያውቃሉ፤
6“你從世上分別出來賜給我的人,我已經把你的名顯明給他們了。他們是你的,你把他們賜給了我,他們也遵守了你的道。
8የሰጠኸኝን ቃል ሰጥቻቸዋለሁና፤ እነርሱም ተቀበሉት፥ ከአንተም ዘንድ እንደ ወጣሁ በእውነት አወቁ፥ አንተም እንደ ላክኸኝ አመኑ።
7現在他們知道,你所給我的,無論是甚麼,都是從你那裡來的;
9እኔ ስለ እነዚህ እለምናለሁ፤ ስለ ዓለም አልለምንም ስለ ሰጠኸኝ እንጂ፤ የአንተ ናቸውና፤
8因為你賜給我的話,我已經給了他們,他們也領受了,又確實知道我是從你那裡來的,並且信你差了我來。
10የእኔም የሆነ ሁሉ የአንተ ነው የአንተውም የእኔ ነው፤ እኔም ስለ እነርሱ ከብሬአለሁ።
9我為他們求;我不為世人求,而是為你賜給我的人求,因為他們是你的。
11ከዚህም በኋላ በዓለም አይደለሁም፥ እነርሱም በዓለም ናቸው፥ እኔም ወደ አንተ እመጣለሁ። ቅዱስ አባት ሆይ፥ እነዚህን የሰጠኸኝን እንደ እኛ አንድ እንዲሆኑ በስምህ ጠብቃቸው።
10我的一切都是你的,你的一切也是我的,並且我因著他們得了榮耀。
12ከእነርሱ ጋር በዓለም ሳለሁ የሰጠኸኝን በስምህ እኔ እጠብቃቸው ነበር፤ ጠበቅኋቸውም መጽሐፉም እንዲፈጸም ከጥፋት ልጅ በቀር ከእነርሱ ማንም አልጠፋም።
11我不再在這世上,他們卻在這世上,我要到你那裡去。聖父啊,求你因你賜給我的名,保守他們,使他們合而為一,好像我們一樣。
13አሁንም ወደ አንተ እመጣለሁ፤ በእነርሱም ዘንድ ደስታዬ የተፈጸመ እንዲሆንላቸው ይህን በዓለም እናገራለሁ።
12我跟他們在一起的時候,因你賜給我的名,我保守了他們,也護衛了他們;他們中間除了那滅亡的人以外,沒有一個是滅亡的,這就應驗了經上的話。
14እኔ ቃልህን ሰጥቻቸዋለሁ፤ እኔም ከዓለም እንዳይደለሁ ከዓለም አይደሉምና ዓለም ጠላቸው።
13現在我到你那裡去,我在世上說這些話,是要他們心裡充滿我的喜樂。
15ከክፉ እንድትጠብቃቸው እንጂ ከዓለም እንድታወጣቸው አልለምንም።
14我把你的道賜給了他們;世人恨他們,因為他們不屬於這世界,像我不屬於這世界一樣。
16እኔ ከዓለም እንዳይደለሁ ከዓለም አይደሉም።
15我不求你使他們離開世界,只求你保守他們脫離那惡者。
17በእውነትህ ቀድሳቸው፤ ቃልህ እውነት ነው።
16他們不屬於這世界,像我不屬於這世界一樣。
18ወደ ዓለም እንደ ላክኸኝ እንዲሁ እኔ ወደ ዓለም ላክኋቸው፤
17求你用真理使他們成聖;你的道就是真理。
19እነርሱም ደግሞ በእውነት የተቀደሱ እንዲሆኑ እኔ ራሴን ስለ እነርሱ እቀድሳለሁ።
18你怎樣差我到世上來,我也怎樣差他們到世上去。
20ሁሉም አንድ ይሆኑ ዘንድ፥ ከቃላቸው የተነሣ በእኔ ስለሚያምኑ ደግሞ እንጂ ስለ እነዚህ ብቻ አልለምንም፤ አንተ እንደ ላክኸኝ ዓለም ያምን ዘንድ፥ አንተ፥ አባት ሆይ፥ በእኔ እንዳለህ እኔም በአንተ፥ እነርሱ ደግሞ በእኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ እለምናለሁ።
19我為了他們的緣故,自己分別為聖,使他們也因著真理成聖。
22እኛም አንድ እንደ ሆንን አንድ ይሆኑ ዘንድ፤ እኔም በእነርሱ አንተም በእኔ ስትሆን፥ በአንድ ፍጹማን እንዲሆኑ፥ የሰጠኸኝን ክብር እኔ ሰጥቻቸዋለሁ፤ እንዲሁም ዓለም አንተ እንደ ላክኸኝ በወደድኸኝም መጠን እነርሱን እንደ ወደድሃቸው ያውቃል።
20祈求使門徒合而為一“我不但為他們求,也為那些因他們的話而信我的人求,
24አባት ሆይ፥ ዓለም ሳይፈጠር ስለ ወደድኸኝ የሰጠኸኝን ክብሬን እንዲያዩ እኔ ባለሁበት የሰጠኸኝ እነርሱ ደግሞ ከእኔ ጋር ይሆኑ ዘንድ እወዳለሁ።
21使他們都合而為一,像父你在我裡面,我在你裡面一樣;使他們也在我們裡面,讓世人相信你差了我來。
25ጻድቅ አባት ሆይ፥ ዓለም አላወቀህም፥ እኔ ግን አወቅሁህ እነዚህም አንተ እንደ ላክኸኝ አወቁ፤
22你賜給我的榮耀,我已經賜給了他們,使他們合而為一,像我們合而為一。
26እኔንም የወደድህባት ፍቅር በእነርሱ እንድትሆን እኔም በእነርሱ፥ ስምህን አስታወቅኋቸው አስታውቃቸውማለሁ።
23我在他們裡面,你在我裡面,使他們完完全全合而為一,讓世人知道你差了我來,並且知道你愛他們,好像愛我一樣。
24父啊,我在哪裡,願你賜給我的人也和我同在哪裡,讓他們看見你賜給我的榮耀,因為在創立世界以前,你已經愛我了。
25公義的父啊,世人雖然不認識你,我卻認識你,這些人也知道你差了我來。
26我已經把你的名指示他們,還要再指示,使你愛我的愛在他們裡面,我也在他們裡面。”