Amharic: New Testament

聖經新譯本

Luke

24

1ነገር ግን ከሳምንቱ በመጀመሪያው ቀን ያዘጋጁትን ሽቱ ይዘው ከእነርሱም ጋር አንዳንዶቹ ወደ መቃብሩ እጅግ ማልደው መጡ።
1耶穌復活(太28:1~8;可16:1~8;約20:1~10)禮拜日大清早的時候,婦女們帶著預備好的香料,來到墳墓那裡,
2ድንጋዩንም ከመቃብሩ ተንከባሎ አገኙት፥
2發現石頭已經從墳墓輥開了,
3ገብተውም የጌታን የኢየሱስን ሥጋ አላገኙም።
3就進去,卻找不著主耶穌的身體。
4እነርሱም በዚህ ሲያመነቱ፥ እነሆ፥ ሁለት ሰዎች የሚያንጸባርቅ ልብስ ለብሰው ወደ እነርሱ ቀረቡ፤
4她們正為此事猜疑的時候,忽然有兩個人,穿著閃爍耀目的衣服,站在她們旁邊。
5ፈርተውም ፊታቸውን ወደ ምድር አቀርቅረው ሳሉ፥ እንዲህ አሉአቸው። ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ? ተነሥቶአል እንጂ በዚህ የለም።
5她們害怕,把臉伏在地上。那兩個人對她們說:“為甚麼在死人中找活人呢?
6የሰው ልጅ በኃጢአተኞች እጅ አልፎ ሊሰጥና ሊሰቀል በሦስተኛውም ቀን ሊነሣ ግድ ነው እያለ ገና በገሊላ ሳለ ለእናንተ እንደ ተናገረ አስቡ።
6他不在這裡,已經復活了。你們應當記得他還在加利利的時候,怎樣告訴你們,
8ቃሎቹንም አሰቡ፥ ከመቃብሩም ተመልሰው ይህን ሁሉ ለአሥራ አንዱና ለሌሎች ሁሉ ነገሩአቸው።
7說:‘人子必須被交在罪人手裡,釘在十字架上,第三日復活。’”
10ይህንም ለሐዋርያት የነገሩአቸው መግደላዊት ማርያምና ዮሐና የያዕቆብም እናት ማርያም ከእነርሱም ጋር የነበሩት ሌሎች ሴቶች ነበሩ።
8她們就想起他的話,
11ይህም ቃል ቅዠት መስሎ ታያቸውና አላመኑአቸውም።
9於是從墳地回去,把這一切事告訴十一個使徒和其餘的人。
12ጴጥሮስ ግን ተነሥቶ ወደ መቃብር ሮጠ፤ በዚያም ዝቅ ብሎ ሲመለከት የተልባ እግር ልብስን ብቻ አየ፤ በሆነውም ነገር እየተደነቀ ወደ ቤቱ ሄደ።
10那些婦女就是抹大拉的馬利亞,約亞拿和雅各的母親馬利亞,以及其他在一起的婦女,她們把這些事向使徒說了。
13እነሆም፥ ከእነርሱ ሁለቱ በዚያ ቀን ከኢየሩሳሌም ስድሳ ምዕራፍ ያህል ወደሚርቅ ኤማሁስ ወደሚባል መንደር ይሄዱ ነበር፤
11使徒以為這些話是無稽之談,就不相信。
14ስለዚህም ስለ ሆነው ነገር ሁሉ እርስ በርሳቸው ይነጋገሩ ነበር።
12彼得卻起來跑到墳墓那裡,屈身往裡觀看,只見細麻布在那裡,就回去了,對所發生的事非常驚奇。
15ሲነጋገሩና ሲመራመሩም፥ ኢየሱስ ራሱ ቀርቦ ከእነርሱ ጋር ይሄድ ነበር፤
13在以馬午斯路上顯現(可16:12~13)同一天,門徒中有兩個人往一個叫以馬午斯的村子去,那村子距耶路撒冷約十一公里;
16ነገር ግን እንዳያውቁት ዓይናቸው ተይዞ ነበር።
14他們彼此談論所發生的這一切事。
17እርሱም። እየጠወለጋችሁ ስትሄዱ፥ እርስ በርሳችሁ የምትነጋገሩአቸው እነዚህ ነገሮች ምንድር ናቸው? አላቸው።
15正在交談議論的時候,耶穌親自走近他們,與他們同行,
18ቀለዮጳ የሚባልም አንዱ መልሶ። አንተ በኢየሩሳሌም እንግዳ ሆነህ ለብቻህ ትኖራለህን? በእነዚህ ቀኖች በዚያ የሆነውን ነገር አታውቅምን? አለው።
16但他們的眼睛卻給蒙蔽了,認不出他來。
19እርሱም። ይህ ምንድር ነው? አላቸው። እነርሱም እንዲህ አሉት። በእግዚአብሔርና በሕዝቡ ሁሉ ፊት በሥራና በቃል ብርቱ ነቢይ ስለ ነበረው ስለ ናዝሬቱ ስለ ኢየሱስ፤
17耶穌說:“你們走路的時候,彼此討論的是甚麼事呢?”他們就站住,面帶愁容;
20እርሱንም የካህናት አለቆችና መኳንንቶቻችን ለሞት ፍርድ እንዴት አሳልፈው እንደ ሰጡትና እንደ ሰቀሉት ነው።
18一個名叫革流巴的回答他:“在耶路撒冷作客的,難道只有你不知道這幾天在那裡所發生的事嗎?”
21እኛ ግን እስራኤልን እንዲቤዥ ያለው እርሱ እንደ ሆነ ተስፋ አድርገን ነበር፤ ደግሞም ከዚህ ሁሉ ጋር ይህ ከሆነ ዛሬ ሦስተኛው ቀን ነው።
19他說:“甚麼事呢?”他們說:“就是拿撒勒人耶穌的事。他是先知,在 神和眾人面前,說話行事都有大能。
22ደግሞም ከእኛ ውስጥ ማልደው ከመቃብሩ ዘንድ የነበሩት አንዳንድ ሴቶች አስገረሙን፤
20我們的祭司長和官長,竟把他交出去,判了死罪,釘在十字架上。
23ሥጋውንም ባጡ ጊዜ። ሕያው ነው የሚሉ የመላእክትን ራእይ ደግሞ አየን ሲሉ መጥተው ነበር።
21但我們素來盼望要救贖以色列的就是他。不但這樣,這些事發生到今天,已經是第三天了。
24ከእኛም ጋር ከነበሩት ወደ መቃብር ሄደው ሴቶች እንደ ተናገሩት ሆኖ አገኙት፥ እርሱን ግን አላዩትም።
22而且我們中間有幾個婦女使我們驚奇,她們清早到墳墓那裡去,
25እርሱም። እናንተ የማታስተውሉ፥ ነቢያትም የተናገሩትን ሁሉ ልባችሁ ከማመን የዘገየ፤
23卻找不到他的身體。她們回來說看見天使顯現,天使說他活了。
26ክርስቶስ ይህን መከራ ይቀበል ዘንድና ወደ ክብሩ ይገባ ዘንድ ይገባው የለምን? አላቸው።
24又有我們中間的幾個人到墳墓那裡去,所看見的正如婦女們所說的,只是沒有看見他。”
27ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ ስለ እርሱ በመጻሕፍት ሁሉ የተጻፈውን ተረጐመላቸው።
25耶穌說:“無知的人哪,先知所說的一切話,你們心裡信得太遲鈍了!
28ወደሚሄዱበትም መንደር ቀረቡ፥ እርሱም ሩቅ የሚሄድ መሰላቸው።
26基督這樣受害,然後進入他的榮耀,不是應當的嗎?”
29እነርሱ። ከእኛ ጋር እደር፥ ማታ ቀርቦአልና ቀኑም ሊመሽ ጀምሮአል ብለው ግድ አሉት፤ ከእነርሱም ጋር ሊያድር ገባ።
27於是他從摩西和眾先知起,把所有關於自己的經文,都給他們解釋明白了。
30ከእነርሱም ጋር በማዕድ ተቀምጦ ሳለ እንጀራውን አንሥቶ ባረከው፥ ቈርሶም ሰጣቸው፤
28他們走近要去的村子,他好像還要往前行,
31ዓይናቸውም ተከፈተ፥ አወቁትም፤ እርሱም ከእነርሱ ተሰወረ።
29他們強留他說:“天晚了,太陽下山了,請與我們同住吧!”他就進去與他們同住。
32እርስ በርሳቸውም። በመንገድ ሲናገረን መጻሕፍትንም ሲከፍትልን ልባችን ይቃጠልብን አልነበረምን? ተባባሉ።
30到了吃飯的時候,他拿起餅來,感謝了,擘開遞給他們,
33በዚያችም ሰዓት ተነሥተው ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፥ አሥራ አንዱና ከእነርሱ ጋር የነበሩትም። ጌታ በእውነት ተነሥቶአል ለስምዖንም ታይቶአል እያሉ በአንድነት ተሰብስበው አገኙአቸው።
31他們的眼睛開了,才認出是耶穌來;他卻從他們面前不見了。
35እነርሱም በመንገድ የሆነውን እንጀራውንም በቈረሰ ጊዜ እንዴት እንደ ታወቀላቸው ተረኩላቸው።
32他們彼此說:“在路上他對我們說話,給我們解釋聖經的時候,我們的心不是火熱的嗎?”
36ይህንም ሲነጋገሩ ኢየሱስ ራሱ በመካከላቸው ቆሞ። ሰላም ለእናንተ ይሁን አላቸው።
33他們就立時起來回耶路撒冷去。在那裡遇見十一個使徒和跟他們聚在一起的人,
37ነገር ግን ደነገጡና ፈሩ መንፈስም ያዩ መሰላቸው።
34說:“主果然復活了,已經向西門顯現了。”
38እርሱም። ስለ ምን ትደነግጣላችሁ? ስለ ምንስ አሳብ በልባችሁ ይነሣል?
35兩個人就把在路上的事,和擘餅的時候他們怎樣認出耶穌來的事,都述說了一遍。
39እኔ ራሴ እንደ ሆንሁ እጆቼንና እግሮቼን እዩ፤ በእኔ እንደምታዩት፥ መንፈስ ሥጋና አጥንት የለውምና እኔን ዳስሳችሁ እዩ አላቸው።
36向眾門徒顯現(太28:16~20;可16:14~18;約20:19~23。參徒1:6~8)正說這話的時候,耶穌親自站在他們當中,說:“願你們平安。”
40ይህንም ብሎ እጆቹንና እግሮቹን አሳያቸው።
37他們非常驚怕,以為看見了靈。
41እነርሱም ከደስታ የተነሣ ገና ስላላመኑ ሲደነቁ ሳሉ። በዚህ አንዳች የሚበላ አላችሁን? አላቸው።
38他說:“你們為甚麼驚慌,為甚麼心裡疑惑呢?
42እነርሱም ከተጠበሰ ዓሣ አንድ ቁራጭ፥ ከማር ወለላም ሰጡት፤
39你們看我的手、我的腳,就知道我是誰。摸我看看,靈沒有骨,沒有肉;你們看,我是有的。”
43ተቀብሎም በፊታቸው በላ።
40說了這話,就把手和腳給他們看。
44እርሱም። ከእናንተ ጋር ሳለሁ በሙሴ ሕግና በነቢያት በመዝሙራትም ስለ እኔ የተጻፈው ሁሉ ይፈጸም ዘንድ ይገባል ብዬ የነገርኋችሁ ቃሌ ይህ ነው አላቸው።
41他們歡喜到不敢相信,並且很驚奇。耶穌說:“你們這裡有甚麼吃的沒有?”
45በዚያን ጊዜም መጻሕፍትን ያስተውሉ ዘንድ አእምሮአቸውን ከፈተላቸው፤
42他們就給了他一片燒魚。
46እንዲህም አላቸው። ክርስቶስ መከራ ይቀበላል በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ይነሣል፥
43他接過來,在他們面前吃了。
47በስሙም ንስሐና የኃጢአት ስርየት ከኢየሩሳሌም ጀምሮ በአሕዛብ ሁሉ ይሰበካል ተብሎ እንዲሁ ተጽፎአል።
44主對他們說:“這就是我從前與你們同在的時候,對你們說過的話:摩西的律法、先知書和詩篇上所記關於我的一切事,都必定應驗。”
48እናንተም ለዚህ ምስክሮች ናችሁ።
45於是他開他們的心竅,使他們明白聖經;
49እነሆም፥ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፤ እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ።
46又說:“經上這樣記著:基督必須受害,第三天從死人中復活。
50እስከ ቢታንያም አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው።
47人要奉他的名,傳講悔改與赦罪的道,從耶路撒冷起,直傳到萬國。
51ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ።
48你們就是這些事的見證。
52እነርሱም፤ ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፥
49我要使我父的應許臨到你們身上,你們當在城裡等候,直到得著從上面來的能力。”
53ዘወትርም እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ ኖሩ።
50耶穌升天(參可16:19~20;徒1:9~11)主帶他們出去,到了伯大尼附近,舉手給他們祝福。
51正在祝福的時候,他就離開他們,被接到天上去了。
52他們就敬拜他,歡歡喜喜地回到耶路撒冷,
53常常在殿裡稱頌 神。