Amharic: New Testament

聖經新譯本

Mark

1

1የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ።
1施洗約翰(太3:1~12;路3:1~18;約1:19~28) 神的兒子(有些抄本無“ 神的兒子”一句)耶穌基督福音的開始。
2እነሆ፥ መንገድህን የሚጠርግ መልክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ ተብሎ በነቢዩ በኢሳይያስ እንደ ተጻፈ፥
2正如以賽亞先知的書上寫著:“看哪,我差遣我的使者在你面前,預備你的道路;
4ዮሐንስ በምድረ በዳ እያጠመቀ የንስሐንም ጥምቀት ለኃጢአት ስርየት እየሰበከ መጣ።
3在曠野有呼喊者的聲音:‘預備主的道,修直他的路!’”
5የይሁዳም አገር ሁሉ የኢየሩሳሌምም ሰዎች ሁሉ ወደ እርሱ ይወጡ ነበር፥ ኃጢአታቸውንም እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ ከእርሱ ይጠመቁ ነበር።
4照這話,施洗的約翰在曠野出現了,傳講悔改的洗禮,使罪得赦。
6ዮሐንስም የግመል ጠጉር ለብሶ በወገቡ ጠፍር ይታጠቅ አንበጣና የበረሀ ማርም ይበላ ነበር።
5猶太全地和全耶路撒冷的人,都出來到他那裡去,承認自己的罪,在約旦河裡受了他的洗。
7ተጎንብሼ የጫማውን ጠፍር መፍታት የማይገባኝ ከእኔ የሚበረታ በኋላዬ ይመጣል።
6約翰身穿駱駝毛的衣服,腰束皮帶,吃的是蝗蟲和野蜜。
8እኔ በውኃ አጠመቅኋችሁ እርሱ ግን በመንፈስ ቅዱስ ያጠምቃችኋል እያለ ይሰብክ ነበር።
7他傳講說:“有一位在我以後來的,能力比我大,我就是彎腰給他解鞋帶都沒有資格。
9በዚያ ወራትም ኢየሱስ ከገሊላ ናዝሬት መጥቶ ከዮሐንስ በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠመቀ።
8我用水給你們施洗,他卻要用聖靈給你們施洗。”
10ወዲያውም ከውኃው በወጣ ጊዜ ሰማያት ሲቀደዱ መንፈስም እንደ ርግብ ሲወርድበት አየና። የምወድህ ልጄ አንተ ነህ፥
9耶穌受洗(太3:13~17;路3:21~22)那時候耶穌從加利利的拿撒勒來,在約旦河裡受了約翰的洗。
11በአንተ ደስ ይለኛል የሚል ድምፅ ከሰማያት መጣ።
10他從水裡一上來,就看見天裂開了,聖靈仿佛鴿子降在他身上。
12ወዲያውም መንፈስ ወደ ምድረ በዳ አወጣው።
11又有聲音從天上來說:“你是我的愛子,我喜悅你。”
13በምድረ በዳም ከሰይጣን እየተፈተነ አርባ ቀን ሰነበተ ከአራዊትም ጋር ነበረ፥ መላእክቱም አገለገሉት።
12耶穌受試探(太4:1~11;路4:1~13)聖靈隨即催促耶穌到曠野去。
14ዮሐንስም አልፎ ከተሰጠ በኋላ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል እየሰበከና። ዘመኑ ተፈጸመ የእግዚአብሔርም መንግሥት ቀርባለች ንስሐ ግቡ በወንጌልም እመኑ እያለ ወደ ገሊላ መጣ።
13他在那裡四十天,受撒但的試探,和野獸在一起,有天使來服事他。
16በገሊላ ባሕርም አጠገብ ሲያልፍ ስምዖንን ወንድሙንም እንድርያስን መረባቸውን ወደ ባሕር ሲጥሉ አየ፥ ዓሣ አጥማጆች ነበሩና።
14在加利利傳道(太4:12~17;路4:14~15)約翰被捕以後,耶穌來到加利利,宣講 神的福音,
17ኢየሱስም። በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ አላቸው።
15說:“時候到了, 神的國近了,你們應當悔改,相信福音。”
18ወዲያውም መረባቸውን ትተው ተከተሉት።
16呼召四個門徒(太4:18~22;路5:1~11;約1:35~42)耶穌沿著加利利海邊行走,看見西門和他弟弟安得烈在海上撒網;他們是漁夫。
19ከዚያም ጥቂት እልፍ ብሎ የዘብዴዎስን ልጅ ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ደግሞ በታንኳ ላይ መረባቸውን ሲያበጁ አየ።
17耶穌就對他們說:“來跟從我,我要使你們成為得人的漁夫。”
20ወዲያውም ጠራቸው አባታቸውንም ዘብዴዎስን ከሞያተኞቹ ጋር በታንኳ ላይ ትተው ተከትለውት ሄዱ።
18他們立刻撇下網,跟從了他。
21ወደ ቅፍርናሆምም ገቡ፤ ወዲያውም በሰንበት ወደ ምኵራብ ገብቶ አስተማረ።
19耶穌稍往前走,看見西庇太的兒子雅各,和雅各的弟弟約翰,正在船上整理魚網,
22እንደ ባለ ሥልጣን ያስተምራቸው ነበር እንጂ እንደ ጻፎች አይደለምና በትምህርቱ ተገረሙ።
20他立即呼召他們。他們撇下父親西庇太和雇工在船上,就跟從他去了。
23በዚያን ጊዜም በምኩራባቸው ርኵስ መንፈስ ያለው ሰው ነበረ፤
21在迦百農趕出污靈(路4:31~37)他們到了迦百農,耶穌隨即在安息日進入會堂教導人。
24እርሱም። የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ፥ ከአንተ ጋር ምን አለን? ልታጠፋን መጣህን? ማን እንደ ሆንህ አውቄአለሁ፥ የእግዚአብሔር ቅዱሱ ብሎ ጮኸ።
22大家對他的教訓都很驚奇,因為他教導他們,像一個有權柄的人,不像經學家。
25ኢየሱስም። ዝም በል ከእርሱም ውጣ ብሎ ገሠጸው።
23就在那時,會堂裡有一個被污靈附著的人,喊叫起來,
26ርኵሱም መንፈስ አንፈራገጠውና በታላቅ ድምፅ ጮኾ ከእርሱ ወጣ።
24說:“拿撒勒人耶穌,我們跟你有甚麼關係呢?你來毀滅我們嗎?我知道你是誰,你是 神的聖者。”
27ሁሉም። ይህ ምንድር ነው? በሥልጣን ርኵሳን መናፍስትን ያዝዛል፤ እነርሱም ይታዘዙለታልና ይህ አዲስ ትምህርት ምንድር ነው? ብለው እስኪጠያየቁ ድረስ አደነቁ።
25耶穌斥責他說:“住口!從他身上出來!”
28ዝናውም ወዲያው በየስፍራው ወደ ገሊላ ዙሪያ ሁሉ ወጣ።
26污靈使那人抽瘋,大聲喊叫,就從他身上出來了。
29ወዲያውም ከምኵራብ ወጥቶ ከያዕቆብና ከዮሐንስ ጋር ወደ ስምዖንና ወደ እንድርያስ ቤት ገባ።
27眾人都很驚訝,於是彼此對問說:“這是怎麼一回事?是個有權能的新道理啊!他吩咐污靈,污靈竟服從了他!”
30የስምዖንም አማት በንዳድ ታማ ተኝታ ነበር፥ ስለ እርስዋም ወዲያው ነገሩት።
28耶穌的名聲立刻傳遍了加利利一帶。
31ቀርቦም እጅዋን ይዞ አስነሣት ንዳዱም ወዲያው ለቀቃትና አገለገለቻቸው።
29治病趕鬼(太8:14~17;路4:38~41)他們一出會堂,就和雅各、約翰到西門和安得烈的家裡去。
32ፀሐይም ገብቶ በመሸ ጊዜ፥ የታመሙትንና አጋንንት ያደረባቸውን ሁሉ ወደ እርሱ አመጡ፤
30西門的岳母正在發燒躺著,他們立刻告訴耶穌。
33ከተማይቱም ሁላ በደጅ ተሰብስባ ነበር።
31耶穌走到她面前,拉著她的手,扶她起來,熱就退了,她就服事他們。
34በልዩ ልዩ ደዌም የታመሙትን ብዙዎችን ፈወሰ፥ ብዙዎችንም አጋንንት አወጣ፥ አጋንንትም ክርስቶስ መሆኑን አውቀው ነበርና ሊናገሩ አልፈቀደላቸውም።
32到了黃昏,有人不斷把生病的和被鬼附的,都帶到耶穌面前。
35ማለዳም ተነሥቶ ገና ሌሊት ሳለ ወጣ ወደ ምድረ በዳም ሄዶ በዚያ ጸለየ።
33全城的人都聚集在門口。
36ስምዖንና ከእርሱ ጋር የነበሩትም ገሥግሠው ተከተሉት፥
34耶穌醫好了各樣的病,也趕出許多的鬼,並且不許鬼說話,因為鬼認識他。
37ባገኙትም ጊዜ። ሁሉ ይፈልጉሃል አሉት።
35在加利利傳道趕鬼(路4:42~44)次日凌晨,天還沒有亮,耶穌起身出去,來到荒野的地方,在那裡禱告。
38እርሱም። በዚያ ደግሞ ልሰብክ ወደ ሌላ ስፍራ በቅርብ ወዳሉ መንደሮች እንሂድ ስለዚህ ወጥቻለሁና አላቸው።
36西門和那些跟他在一起的人就去尋找耶穌。
39በምኵራባቸውም እየሰበከ አጋንንትንም እያወጣ ወደ ገሊላ ሁሉ መጣ።
37他們找到了,就對他說:“大家都在找你呢!”
40ለምጻምም ወደ እርሱ መጥቶ ተንበረከከና። ብትወድስ ልታነጻኝ ትችላለህ ብሎ ለመነው።
38耶穌對他們說:“我們到鄰近的鄉鎮去吧,我也好在那裡傳道,因為我就是為這事而來的。”
41ኢየሱስም አዘነለት እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውና። እወድዳለሁ፤ ንጻ አለው።
39於是他走遍加利利全地,在他們的會堂裡傳道,並且趕鬼。
42በተናገረም ጊዜ ለምጹ ወዲያው ለቀቀውና ነጻ።
40治好痲風病人(太8:2~4;路5:12~16)有一個患痲風的人,來到耶穌跟前,跪下求他說:“如果你肯,必能使我潔淨。”
43በብርቱም ተናግሮ ወዲያው አወጣው፤
41耶穌動了憐憫的心,就伸手摸他,說:“我肯,你潔淨了吧!”
44ለማንም አንዳች እንዳትናገር ተጠንቀቅ፥ ነገር ግን ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ ለእነርሱም ምስክር እንዲሆን ስለ መንጻትህ ሙሴ ያዘዘውን አቅርብ አለው።
42痲風立刻離開了他,他就潔淨了。
45እርሱ ግን ሲወጣ ብዙ ሊሰብክና ነገሩን ሊያወራ ጀመረ፥ ስለዚህም ኢየሱስ ተገልጦ ወደ ከተማ መግባት ወደ ፊት ተሳነው፥ ነገር ግን በውጭ በምድረ በዳ ይኖር ነበር፤ ከየስፍራውም ወደ እርሱ ይመጡ ነበር።
43耶穌打發那人離開以前,嚴厲地吩咐他,
44說:“你千萬不可把這事告訴任何人,你只要去給祭司檢查,並且照著摩西所規定的,為你得潔淨獻祭,好向大家作證。”
45但那人出來,竟任意傳講,就把這事傳開了,以致耶穌不能再公開進城,只好留在外邊荒野的地方;然而還是有人從各處到他那裡去。