1በሰንበትም መጨረሻ መጀመሪያው ቀን ሲነጋ መግደላዊት ማርያምና ሁለተኛይቱ ማርያም መቃብሩን ሊያዩ መጡ።
1耶穌復活(可16:1~10;路24:1~12;約20:1~10)過了安息日,在禮拜日天亮的時候,抹大拉的馬利亞和另一個馬利亞來看墳墓。
2እነሆም፥ የጌታ መልአክ ከሰማይ ስለ ወረደ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ቀርቦም ድንጋዩን አንከባሎ በላዩ ተቀመጠ።
2忽然,地震得很厲害;主的使者從天上下來,把石頭輥開,坐在上面。
3መልኩም እንደ መብረቅ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበረ።
3他的樣子好像閃電,衣服潔白如雪。
4ጠባቆቹም እርሱን ከመፍራት የተነሣ ተናወጡ እንደ ሞቱም ሆኑ።
4看守的人因為害怕他,就渾身戰抖,好像死了一樣。
5መልአኩም መልሶ ሴቶቹን አላቸው። እናንተስ አትፍሩ የተሰቀለውን ኢየሱስን እንድትሹ አውቃለሁና፤
5那使者對婦女們說:“你們不要怕,我知道你們在找被釘十字架的耶穌。
6እንደ ተናገረ ተነሥቶአልና በዚህ የለም፤ የተኛበትን ስፍራ ኑና እዩ።
6他不在這裡,已經照他所說的復活了。你們來看安放他的地方吧。
7ፈጥናችሁም ሂዱና። ከሙታን ተነሣ፥ እነሆም፥ ወደ ገሊላ ይቀድማችኋል በዚያም ታዩታላችሁ ብላችሁ ለደቀ መዛሙርቱ ንገሩአቸው።
7快去告訴他的門徒:‘他已經從死人中復活了。他會比你們先到加利利去,你們在那裡必看見他。’現在我已經告訴你們了。”
8እነሆም፥ ነገርኋችሁ። በፍርሃትና በታላቅ ደስታም ፈጥነው ከመቃብር ሄዱ፥ ለደቀ መዛሙርቱም ሊያወሩ ሮጡ።
8她們立刻離開墳墓,又害怕,又十分歡喜,跑去告訴耶穌的門徒。
9እነሆም፥ ኢየሱስ አገኛቸውና። ደስ ይበላችሁ አላቸው። እነርሱም ቀርበው እግሩን ይዘው ሰገዱለት።
9忽然,耶穌向她們迎面而來,說:“你們好。”她們就上前,抱住他的腳拜他。
10በዚያን ጊዜ ኢየሱስ። አትፍሩ፤ ሄዳችሁ ወደ ገሊላ እንዲሄዱ ለወንድሞቼ ተናገሩ፥ በዚያም ያዩኛል አላቸው።
10耶穌對她們說:“不要怕,去告訴我的弟兄,叫他們到加利利去,他們在那裡必看見我。”
11ሲሄዱም ሳሉ እነሆ፥ ከጠባቆቹ አንዳንድ ወደ ከተማ መጥተው የሆነውን ሁሉ ለካህናት አለቆች አወሩ።
11衛兵受賄造謠她們去的時候,有些衛兵進了城,把一切所發生的事向祭司長報告。
12ከሽማግሎች ጋርም ተሰብስበው ተማከሩና ለጭፍሮች ብዙ ገንዘብ ሰጥተዋቸው።
12祭司長就和長老聚集在一起商量,然後拿許多錢給士兵,
13እኛ ተኝተን ሳለን ደቀ መዛሙርቱ በሌሊት መጥተው ሰረቁት በሉ።
13說:“你們要這樣說:‘他的門徒晚上來了,趁我們睡著的時候,把他偷走了。’
14ይህም በገዢው ዘንድ የተሰማ እንደ ሆነ፥ እኛ እናስረዳዋለን እናንተም ያለ ሥጋት እንድትሆኑ እናደርጋለን አሉአቸው።
14如果總督知道了這件事,我們會說服他,不會牽連你們。”
15እነርሱም ገንዘቡን ተቀብለው እንደ አስተማሩአቸው አደረጉ። ይህም ነገር በአይሁድ ዘንድ እስከ ዛሬ ድረስ ሲወራ ይኖራል።
15士兵收了錢,就照著祭司長和長老的指使去作。這種說法直到今日還流傳在猶太人當中。
16አሥራ አንዱ ደቀ መዛሙርት ግን ኢየሱስ ወዳዘዛቸው ተራራ ወደ ገሊላ ሄዱ፥
16主交給門徒的使命(可16:14~18;路24:36~49;約20:19~23。參徒1:6~8)十一個門徒往加利利去,到了耶穌指定的山上。
17ባዩትም ጊዜ ሰገዱለት፤ የተጠራጠሩ ግን ነበሩ።
17他們看見耶穌就拜他,但仍然有些人懷疑。
18ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው። ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ።
18耶穌上前來,對他們說:“天上地上一切權柄都賜給我了。
19እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።
19所以,你們要去使萬民作我的門徒,奉父子聖靈的名,給他們施洗(“奉父子聖靈的名,給他們施洗”或譯:“給他們施洗,歸入父子聖靈的名”),
20我吩咐你們的一切,都要教導他們遵守。這樣,我就常常與你們同在,直到這世代的終結。”