Amharic: New Testament

聖經新譯本

Matthew

27

1ሲነጋም የካህናት አለቆችና የሕዝቡ ሽማግሎች ሁሉ ሊገድሉት በኢየሱስ ላይ ተማከሩ፤
1耶穌被押交彼拉多(可15:1;路23:1;約18:28)到了早上,所有的祭司長和民間的長老商議怎樣對付耶穌,好殺掉他。
2አስረውም ወሰዱት፥ ለገዢው ለጴንጤናዊው ጲላጦስም አሳልፈው ሰጡት።
2他們把他綁起來,押去交給總督彼拉多。
3በዚያን ጊዜ አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ እንደ ተፈረደበት አይቶ ተጸጸተ፥ ሠላሳውንም ብር ለካህናት አለቆችና ለሽማግሎች መልሶ።
3猶大的結局(參徒1:18~19)那時,出賣耶穌的猶大見耶穌定了罪,就後悔了。他把那三十塊銀子還給祭司長和長老,說:
4ንጹሕ ደም አሳልፌ በመስጠቴ በድያለሁ አለ። እነርሱ ግን። እኛስ ምን አግዶን? አንተው ተጠንቀቅ አሉ።
4“我有罪了!我出賣了無辜的人(“人”原文作“血”)!”他們說:“這是你的事,跟我們有甚麼關係?”
5ብሩንም በቤተ መቅደስ ጥሎ ሄደና ታንቆ ሞተ።
5猶大把銀子丟進聖所,然後離開,出去吊死了。
6የካህናት አለቆችም ብሩን አንሥተው። የደም ዋጋ ነውና ወደ መባ ልንጨምረው አልተፈቀደም አሉ።
6祭司長把銀子拾起來,說:“這是血錢,不可放在殿庫裡。”
7ተማክረውም የሸክላ ሠሪውን መሬት ለእንግዶች መቃብር ገዙበት።
7他們商議之後,就用那些錢買了“陶匠的田”,用來作外國人的墳地。
8ስለዚህ ያ መሬት እስከ ዛሬ ድረስ የደም መሬት ተባለ።
8所以那田稱為“血田”,直到今日。
9በዚያን ጊዜ በነቢዩ በኤርምያስ የተባለው። ከእስራኤል ልጆችም አንዳንዶቹ የገመቱትን፥ የተገመተውን ዋጋ ሠላሳ ብር ያዙ፥
9這應驗了耶利米先知所說的:“他們拿了三十塊銀子,就是以色列人給他估定的價錢,
10ጌታም እንዳዘዘኝ ስለ ሸክላ ሠሪ መሬት ሰጡት። የሚል ተፈጸመ።
10用它買了‘陶匠的田’,正如主所指示我的。”
11ኢየሱስም በገዢው ፊት ቆመ፤ ገዢውም። የአይሁድ ንጉሥ አንተ ነህን? ብሎ ጠየቀው፤ ኢየሱስም። አንተ አልህ አለው።
11彼拉多判耶穌釘十字架(可15:2~15;路23:2、3、18~25;約18:29~19:16)耶穌站在總督面前,總督問他:“你是猶太人的王嗎?”耶穌回答:“這是你說的。”
12የካህናት አለቆችም ሽማግሎችም ሲከሱት ምንም አልመለሰም።
12祭司長和長老控告他的時候,他卻不回答。
13በዚያን ጊዜ ጲላጦስ። ስንት ያህል እንዲመሰክሩብህ አትሰማምን? አለው።
13彼拉多又問他:“他們作證指控你這麼多的事,你沒有聽見嗎?”
14ገዢውም እጅግ እስኪደነቅ ድረስ አንዲት ቃል ስንኳ አልመለሰለትም።
14耶穌一句話也不回答他,令總督非常驚奇。
15በዚያም በዓል ሕዝቡ የወደዱትን አንድ እስረኛ ሊፈታላቸው ለገዢው ልማድ ነበረው።
15每逢這節期,總督有一個慣例,就是給群眾釋放一個他們要求釋放的囚犯。
16በዚያን ጊዜም በርባን የሚባል በጣም የታወቀ እስረኛ ነበራቸው።
16那時,有個聲名狼藉的囚犯,名叫耶數.巴拉巴。
17እንግዲህ እነርሱ ተሰብስበው ሳሉ ጲላጦስ። በርባንን ወይስ ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን ማንኛውን ልፈታላችሁ ትወዳላችሁ? አላቸው፤
17群眾聚集的時候,彼拉多問他們:“你們要我給你們釋放誰?耶數.巴拉巴或是稱為基督的耶穌呢?”
18በቅንዓት አሳልፈው እንደ ሰጡት ያውቅ ነበርና።
18他知道他們是因為嫉妒才把耶穌交了來。
19እርሱም በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ሳለ ሚስቱ። ስለ እርሱ ዛሬ በሕልም እጅግ መከራ ተቀብያለሁና በዚያ ጻድቅ ሰው ምንም አታድርግ ብላ ላከችበት።
19彼拉多坐在審判臺上的時候,他的夫人派人來說:“你不要干涉這個義人的事,因為昨夜我在夢中因他受了很多的苦。”
20የካህናት አለቆችና ሽማግሎች ግን በርባንን እንዲለምኑ ኢየሱስን ግን እንዲያጠፉ ሕዝቡን አባበሉ።
20祭司長和長老慫恿群眾,叫他們去要求釋放巴拉巴,除掉耶穌。
21ገዢውም መልሶ። ከሁለቱ ማንኛውን ልፈታላችሁ ትወዳላችሁ? አላቸው፤ እነርሱም። በርባንን አሉ።
21總督問他們:“這兩個人,你們要我給你們釋放哪一個?”他們說:“巴拉巴!”
22ጲላጦስ። ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን እንግዲህ ምን ላድርገው? አላቸው፤ ሁሉም። ይሰቀል አሉ።
22彼拉多對他們說:“那麼,我怎樣處置那稱為基督的耶穌呢?”他們齊聲說:“把他釘十字架!”
23ገዢውም። ምን ነው? ያደረገው ክፋት ምንድር ነው? አለ፤ እነርሱ ግን። ይሰቀል እያሉ ጩኸት አበዙ።
23彼拉多說:“他作了甚麼惡事呢?”眾人更加大聲喊叫:“把他釘十字架!”
24ጲላጦስም ሁከት እንዲጀመር እንጂ አንዳች እንዳይረባ ባየ ጊዜ፥ ውኃ አንሥቶ። እኔ ከዚህ ጻድቅ ሰው ደም ንጹሕ ነኝ፤ እናንተ ተጠንቀቁ ሲል በሕዝቡ ፊት እጁን ታጠበ።
24彼拉多見無濟於事,反會引起騷動,就拿水在群眾面前洗手,說:“流這人的血,與我無關,你們自己負責吧。”
25ሕዝቡም ሁሉ መልሰው። ደሙ በእኛና በልጆቻችን ላይ ይሁን አሉ።
25群眾回答:“流他的血的責任,歸在我們和我們子孫的身上吧。”
26በዚያን ጊዜ በርባንን ፈታላቸው፥ ኢየሱስን ግን ገርፎ ሊሰቀል አሳልፎ ሰጠ።
26於是彼拉多給他們釋放了巴拉巴;他把耶穌鞭打了,就交給他們釘十字架。
27በዚያን ጊዜ የገዢው ወታደሮች ኢየሱስን ወደ ገዢው ግቢ ውስጥ ወሰዱት ጭፍራውንም ሁሉ ወደ እርሱ አከማቹ።
27士兵戲弄耶穌(可15:16~20;約19:2~3)總督的士兵把耶穌帶到總督府,召集全隊士兵到他面前。
28ልብሱንም ገፈው ቀይ ልብስ አለበሱት፥
28他們脫去他的衣服,給他披上朱紅色的外袍,
29ከእሾህም አክሊል ጎንጉነው በራሱ ላይ፥ በቀኝ እጁም መቃ አኖሩ፥ በፊቱም ተንበርክከው። የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፥ ሰላም ለአንተ ይሁን እያሉ ዘበቱበት፤
29又用荊棘編成冠冕,戴在他的頭上,把一根蘆葦放在他的右手,跪在他面前譏笑他說:“猶太人的王萬歲!”
30ተፉበትም መቃውንም ይዘው ራሱን መቱት።
30然後向他吐唾沫,又拿起蘆葦打他的頭。
31ከዘበቱበትም በኋላ ቀዩን ልብስ ገፈፉት፥ ልብሱንም አለበሱት ሊሰቅሉትም ወሰዱት።
31戲弄完了,就脫下他的外袍,給他穿回衣服,帶去釘十字架。
32ሲወጡም ስምዖን የተባለው የቀሬናን ሰው አገኙ፤ እርሱንም መስቀሉን ይሸከም ዘንድ አስገደዱት።
32耶穌被釘十字架(可15:22~32;路23:33~43;約19:17~24)他們出來的時候,遇見一個古利奈人,名叫西門,就強迫他背耶穌的十字架。
33ትርጓሜው የራስ ቅል ስፍራ ወደሚሆን ጎልጎታ ወደሚባለው ስፍራ በደረሱ ጊዜም፥
33到了一個地方,名叫各各他,就是“髑髏地”的意思,
34በሐሞት የተደባለቀ የወይን ጠጅ ሊጠጣ አቀረቡለት፤ ቀምሶም ሊጠጣው አልወደደም።
34他們把苦膽調和的酒給他喝,他嘗了卻不肯喝。
35ከሰቀሉትም በኋላ ልብሱን ዕጣ ጥለው ተካፈሉ፥
35士兵把他釘了十字架,就抽籤分他的衣服,
36በዚያም ተቀምጠው ይጠብቁት ነበር።
36然後坐在那裡看守他。
37ይህ ኢየሱስ የአይሁድ ንጉሥ ነው የሚል የክሱን ጽሕፈት ከራሱ በላይ አኖሩ።
37他們在耶穌的頭以上,釘了一塊牌子,寫著他的罪狀:“這是猶太人的王耶穌”。
38በዚያን ጊዜ ሁለት ወንበዶች አንዱ በቀኝ አንዱም በግራ ከእርሱ ጋር ተሰቀሉ።
38當時,有兩個強盜和他一同釘十字架,一個在右,一個在左。
39የሚያልፉትም ራሳቸውን እየነቀነቁ ይሰድቡት ነበርና።
39過路的人嘲笑他,搖著頭說:
40ቤተ መቅደስን የምታፈርስ በሦስት ቀንም የምትሠራው፥ ራስህን አድን፤ የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ ከመስቀል ውረድ አሉት።
40“你這個想拆毀聖所,三日之內又把它建造起來的,救救自己吧!如果你是 神的兒子,從十字架上下來吧!”
41እንዲሁም ደግሞ የካህናት አለቆች ከጻፎችና ከሽማግሎች ጋር እየዘበቱበት እንዲህ አሉ።
41祭司長、經學家和長老也同樣譏笑他,說:
42ሌሎችን አዳነ፥ ራሱን ሊያድን አይችልም፤ የእስራኤል ንጉሥ ከሆነ፥ አሁን ከመስቀል ይውረድ እኛም እናምንበታለን።
42“他救了別人,卻不能救自己。如果他是以色列的王,現在可以從十字架上下來,我們就信他。
43በእግዚአብሔር ታምኖአል፤ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ብሎአልና ከወደደውስ አሁን ያድነው።
43他信靠 神;如果 神喜悅他,就讓 神現在救他吧,因為他說自己是 神的兒子。”
44ከእርሱ ጋር የተሰቀሉት ወንበዶች ደግሞ ያንኑ እያሉ ይነቅፉት ነበር።
44和他一同釘十字架的強盜也都這樣侮辱他。
45ከስድስት ሰዓትም ጀምሮ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በምድር ሁሉ ላይ ጨለማ ሆነ።
45耶穌死時的情形(可15:33~41;路23:44~49;約19:28~30)從正午到下午三點鐘,遍地都黑暗了。
46በዘጠኝ ሰዓትም ኢየሱስ። ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ? ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህም። አምላኬ አምላኬ፥ ስለ ምን ተውኸኝ? ማለት ነው።
46大約三點鐘,耶穌大聲呼叫:“以利,以利,拉馬撒巴各大尼?”意思是“我的 神,我的 神,你為甚麼離棄我?”
47በዚያም ከቆሙት ሰዎች ሰምተው። ይህስ ኤልያስን ይጠራል አሉ።
47有幾個站在那裡的人,聽見了就說:“這個人在呼叫以利亞呢。”
48ወዲያውም ከእነርሱ አንዱ ሮጠ፤ ሰፍነግም ይዞ ሆምጣጤ ሞላበት፥ በመቃም አድርጎ አጠጣው።
48有一個人馬上跑去拿海綿蘸滿了酸酒,用蘆葦遞給他喝。
49ሌሎቹ ግን። ተው፥ ኤልያስ መጥቶ ያድነው እንደ ሆነ እንይ አሉ።
49但其他的人說:“等一等,我們看看以利亞來不來救他。”
50ኢየሱስም ሁለተኛ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ነፍሱን ተወ።
50耶穌再大聲呼叫,氣就斷了。
51እነሆም፥ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ፥ ምድርም ተናወጠች፥ ዓለቶችም ተሰነጠቁ፤
51忽然,聖所裡的幔子從上到下裂成兩半;地面震動,石頭崩裂;
52መቃብሮችም ተከፈቱ፥ ተኝተው ከነበሩትም ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ተነሡ፤
52而且墳墓開了,許多睡了的聖徒的身體也復活了,
53ከትንሣኤውም በኋላ ከመቃብሮች ወጥተው ወደ ቅድስት ከተማ ገቡና ለብዙዎች ታዩ።
53從墳墓裡出來;到了耶穌復活之後,他們進到聖城向許多人顯現。
54የመቶ አለቃም ከእርሱም ጋር ኢየሱስን የሚጠብቁ መናወጡንና የሆነውን ነገር አይተው። ይህ በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነበረ ብለው እጅግ ፈሩ።
54百夫長和跟他一起看守耶穌的士兵,看見了地震和所發生的事情,就十分懼怕,說:“這個人真是 神的兒子。”
55ኢየሱስን እያገለገሉ ከገሊላ የተከተሉት ብዙ ሴቶች በሩቅ ሆነው ሲመለከቱ በዚያ ነበሩ፤
55有許多婦女在那裡遠遠地觀看;她們是從加利利開始跟隨耶穌服事他的。
56ከእነርሱም መግደላዊት ማርያምና የያዕቆብና የዮሳ እናት ማርያም የዘብዴዎስም የልጆቹ እናት ነበሩ።
56她們中間有抹大拉的馬利亞、雅各和約西的母親馬利亞,以及西庇太的兒子的母親。
57በመሸም ጊዜ ዮሴፍ የተባለው ባለ ጠጋ ሰው ከአርማትያስ መጣ፥ እርሱም ደግሞ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ነበረ፤
57耶穌葬在新墳墓裡(可15:42~47;路23:50~56;約19:38~42)到了晚上,有一個亞利馬太的富翁來到,他名叫約瑟,是耶穌的門徒。
58ይኸውም ወደ ጲላጦስ ቀርቦ የኢየሱስን ሥጋ ለመነው።
58這個人去見彼拉多,請求領取耶穌的身體,彼拉多就吩咐給他。
59ጲላጦስም እንዲሰጡት አዘዘ። ዮሴፍም ሥጋውን ይዞ በንጹሕ በፍታ ከፈነው፥
59約瑟領了耶穌的身體,用乾淨的細麻布裹好,
60ከዓለት በወቀረው በአዲሱ መቃብርም አኖረው፥ በመቃብሩም ደጃፍ ታላቅ ድንጋይ አንከባሎ ሄደ።
60放在自己的新墳墓裡,就是在磐石裡鑿出來的。他輥了一塊大石頭來擋住墓門,然後才離開。
61መግደላዊት ማርያምም ሁለተኛይቱም ማርያም በመቃብሩ አንጻር ተቀምጠው በዚያ ነበሩ።
61抹大拉的馬利亞和另一個馬利亞都在那裡,對著墳墓坐著。
62በማግሥቱም ከመዘጋጀት በኋላ በሚሆነው ቀን፥ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን ወደ ጲላጦስ ተሰበሰቡና።
62衛兵嚴密看守墳墓第二天,就是過了“預備日”的那一天,祭司長和法利賽人去見彼拉多,說:
63ጌታ ሆይ፥ ያ አሳች በሕይወቱ ገና ሳለ። ከሦስት ቀን በኋላ እነሣለሁ እንዳለ ትዝ አለን።
63“大人,我們想起那個騙子,生前說過:‘三天之後,我要復活。’
64እንግዲህ ደቀ መዛሙርቱ መጥተው በሌሊት እንዳይሰርቁት ለሕዝቡም። ከሙታን ተነሣ እንዳይሉ፥ የኋለኛይቱ ስሕተት ከፊተኛይቱ ይልቅ የከፋች ትሆናለችና መቃብሩ እስከ ሦስተኛ ቀን ድረስ እንዲጠበቅ እዘዝ አሉት።
64所以請你下令把墳墓嚴密看守,直到第三天,免得他的門徒來把他偷去,然後對民眾說:‘他從死人中復活了。’這樣,日後的騙局比起初的就更大了。”
65ጲላጦስም። ጠባቆች አሉአችሁ፤ ሄዳችሁ እንዳወቃችሁ አስጠብቁ አላቸው።
65彼拉多對他們說:“你們帶著衛兵,盡你們所能的去嚴密看守吧。”
66እነርሱም ሄደው ከጠባቆች ጋር ድንጋዩን አትመው መቃብሩን አስጠበቁ።
66他們就去把墓前的石封好,又派衛兵把守,嚴密地守住墳墓。