Amharic: New Testament

聖經新譯本

Mark

14

1ከሁለት ቀን በኋላ ፋሲካና የቂጣ በዓል ነበረ። የካህናት አለቆችም ጻፎችም እንዴት አድርገው በተንኰል እንደሚይዙትና እንደሚገድሉት ይፈልጉ ነበር።
1商議怎樣殺害耶穌(太26:1~5;路22:1~6)過兩天,就是逾越節和除酵節了,祭司長和經學家設法怎樣用詭計逮捕耶穌,把他殺害。
2የሕዝብ ሁከት እንዳይሆን በበዓል አይሁን ይሉ ነበርና።
2不過他們說:“不可在節期下手,免得引起民眾暴動。”
3እርሱም በቢታንያ በለምጻሙ በስምዖን ቤት በነበረ ጊዜ፥ በማዕድ ተቀምጦ ሳለ፥ አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ የከበረ ጥሩ ናርዶስ ሽቱ የመላበት የአልባስጥሮስ ቢልቃጥ ይዛ መጣች፤ ቢልቃጡንም ሰብራ በራሱ ላይ አፈሰሰችው።
3伯大尼婦人用香膏膏主(太26:6~13。參約12:1~8)耶穌在伯大尼,在患痲風的西門家裡吃飯的時候,有一個女人來了,拿著一瓶珍貴的純哪噠香膏。她打破了瓶,把香膏澆在耶穌的頭上。
4አንዳንዶችም። ይህ የሽቱ ጥፋት ለምንድር ነው?
4有幾個人很生氣,彼此說:“為甚麼這樣浪費香膏呢?
5ይህ ሽቱ ከሦስት መቶ ዲናር በሚበልጥ ዋጋ ተሽጦ ለድሆች ሊሰጥ ይቻል ነበርና ብለው በራሳቸው ይቈጡ ነበር፤ እርስዋንም ነቀፉአት።
5這香膏可以賣三百多個銀幣,用來賙濟窮人。”他們就向她發怒。
6ኢየሱስ ግን እንዲህ አለ። ተዉአት፤ ስለ ምን ታደክሙአታላችሁ? መልካም ሥራ ሠርታልኛለች።
6但耶穌說:“由她吧!為甚麼難為她呢?她在我身上作的是一件美事。
7ድሆች ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ይኖራሉና፥ በማናቸውም በወደዳችሁት ጊዜ መልካም ልታደርጉላቸው ትችላላችሁ፥ እኔ ግን ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር አልኖርም።
7你們常常有窮人跟你們在一起,只要你們願意,隨時都可以向他們行善,然而你們卻不常有我。
8የተቻላትን አደረገች፤ አስቀድማ ለመቃብሬ ሥጋዬን ቀባችው።
8她已經盡她所能的作了。她預先用香膏膏了我的身體,是為了我的安葬。
9እውነት እላችኋለሁ፥ ይህ ወንጌል በዓለሙ ሁሉ በሚሰበክበት በማናቸውም ስፍራ፥ እርስዋ ያደረገችው ደግሞ ለእርስዋ መታሰቢያ ሊሆን ይነገራል።
9我實在告訴你們,福音無論傳到世界上甚麼地方,都要傳講這女人所作的來記念她。”
10ከአሥራ ሁለቱም አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ ሊሰጠው ወደ ካህናት አለቆች ሄደ።
10猶大出賣耶穌(太26:14~16)十二門徒中的一個,就是加略人猶大,去見祭司長,要把耶穌交給他們。
11ሲሰሙም ደስ አላቸው ብርም ይሰጡት ዘንድ ተስፋ ሰጡት። በሚመች ጊዜም እንዴት አድርጎ አሳልፎ እንዲሰጠው ይፈልግ ነበር።
11他們聽見了就很歡喜,答應給他銀子。於是猶大就找機會出賣耶穌。
12ፋሲካን በሚያርዱበት በቂጣ በዓል መጀመሪያ ቀን ደቀ መዛሙርቱ። ፋሲካን ትበላ ዘንድ ወዴት ሄደን ልናሰናዳ ትወዳለህ? አሉት።
12最後的晚餐(太26:17~30;路22:7~23;約13:21~30。參林前11:23~25)除酵節的第一天,就是宰殺逾越節羊羔的那一天,門徒問耶穌:“你要我們到哪裡去,為你預備逾越節的晚餐呢?”
13ከደቀ መዛሙርቱም ሁለት ላከ እንዲህም አላቸው። ወደ ከተማ ሂዱ፥ ማድጋ ውኃ የተሸከመ ሰውም ይገናኛችኋል፤
13他就差派兩個門徒,對他們說:“你們到城裡去,必有一個拿著水瓶的人,向你們迎面而來,你們就跟著他,
14ተከተሉት፥ የሚገባበትንም የቤቱን ጌታ። መምህሩ። ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ፋሲካን የምበላበት የእንግዳ ቤት ወዴት ነው? ይላል በሉት።
14無論他進入哪一家,你們要對那家主說,老師說:‘我的客廳在哪裡?我和門徒好在那裡吃逾越節的晚餐。’
15እርሱም በደርብ ላይ ያለውን የተሰናዳና የተነጠፈ ታላቅ አዳራሽ ያሳያችኋል፤
15他必指給你們樓上一間布置整齊、預備妥當的大房間,你們就在那裡為我們預備。”
16በዚያም አሰናዱልን። ደቀ መዛሙርቱም ወጡ ወደ ከተማም ሄደው እንዳላቸው አገኙ፥ ፋሲካንም አሰናዱ።
16門徒出去,進了城,所遇見的正如耶穌所說的,就預備好了逾越節的晚餐。
17በመሸም ጊዜ ከአሥራ ሁለቱ ጋር መጣ።
17到了晚上,耶穌和十二門徒來了。
18ተቀምጠውም ሲበሉ ኢየሱስ። እውነት እላችኋለሁ፥ ከእናንተ አንዱ፥ እርሱም ከእኔ ጋር የሚበላው አሳልፎ ይሰጠኛል አለ።
18他們坐著吃飯的時候,耶穌說:“我實在告訴你們,你們中間有一個跟我一起吃飯的人要出賣我。”
19እነርሱም ያዝኑ፥ እያንዳንዳቸውም። እኔ እሆንን? ይሉት ጀመር።
19他們就很憂愁,一個一個地問他:“是我嗎?”
20እርሱም መልሶ። ከአሥራ ሁለቱ አንዱ ከእኔ ጋር ወደ ወጭቱ እጁን የሚያጠልቀው ነው።
20耶穌對他們說:“他是十二門徒裡的一個,和我一同把手蘸在盤子裡的。
21የሰው ልጅስ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ ይሄዳል፤ ነገር ግን የሰው ልጅ አልፎ ለሚሰጥበት ለዚያ ሰው ወዮለት፤ ያ ሰው ባልተወለደ ይሻለው ነበር አላቸው።
21正如經上指著人子所說的,他固然要離世,但出賣人子的那人有禍了!他沒有生下來還好。”
22ሲበሉም ኢየሱስ እንጀራን አንሥቶ ባረከ ቈርሶም ሰጣቸውና። እንካችሁ፤ ይህ ሥጋዬ ነው አለ።
22他們吃的時候,耶穌拿起餅來,祝謝了,就擘開,遞給門徒,說:“你們拿去吃吧,這是我的身體。”
23ጽዋንም አንሥቶ አመስግኖም ሰጣቸው፥ ሁሉም ከእርሱ ጠጡ።
23又拿起杯來,祝謝了就遞給門徒,他們都喝了。
24እርሱም። ይህ ስለ ብዙዎች የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ነው።
24耶穌說:“這是我的血,是為立約的,為許多人流出來的。
25እውነት እላችኋለሁ፥ በእግዚአብሔር መንግሥት ከወይኑ ፍሬ አዲሱን እስከምጠጣበት እስከዚያ ቀን ድረስ ደግሞ አልጠጣውም አላቸው።
25我實在告訴你們,我決不再喝這葡萄酒,直到我在 神的國裡喝新酒的那一天。”
26መዝሙርም ከዘመሩ በኋላ ወደ ደብረ ዘይት ወጡ።
26他們唱完了詩,就出來,往橄欖山去。
27ኢየሱስም። በዚች ሌሊት ሁላችሁ በእኔ ትሰናከላላችሁ፤ እረኛዉን እመታለሁ በጎችም ይበተናሉ የሚል ተጽፎአልና።
27預言彼得不認主(太26:31~35;路22:31~34;約13:36~38)耶穌對他們說:“你們都要後退,因為經上記著:‘我要擊打牧人,羊群就分散了。’
28ነገር ግን ከተነሣሁ በኋላ ወደ ገሊላ እቀድማችኋለሁ አላቸው።
28但我復活以後,要比你們先到加利利去。”
29ጴጥሮስም። ሁሉም ቢሰናከሉ እኔ ግን ከቶ አልሰናከልም አለው።
29彼得對他說:“就算所有的人都後退,我卻不會。”
30ኢየሱስም። እውነት እልሃለሁ፥ ዛሬ በዚች ሌሊት ዶሮ ሁለት ጊዜ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ አለው።
30耶穌對他說:“我實在告訴你,就在今天晚上,雞叫兩遍以前,你會三次不認我。”
31እርሱም ቃሉን አበርትቶ። ከአንተ ጋር የምሞት እንኳ ቢሆን ከቶ አልክድህም አለ። ሁሉም ደግሞ እንደዚሁ አሉ።
31彼得更堅決地說:“就算必須與你一同死,我也決不會不認你!”眾人也都這樣說。
32ጌቴሴማኒ ወደምትባልም ስፍራ መጡ፥ ደቀ መዛሙርቱንም። ስጸልይ ሳለሁ፥ በዚህ ተቀመጡ አላቸው።
32在客西馬尼禱告(太26:36~46;路22:39~46)他們來到一個地方,名叫客西馬尼;耶穌對門徒說:“你們坐在這裡,我去禱告。”
33ጴጥሮስንና ያዕቆብን ዮሐንስንም ከእርሱ ጋር ወሰደ፤ ሊደነግጥም ሊተክዝም ጀመረና።
33他帶了彼得、雅各、約翰一起去,就驚懼起來,非常難過。
34ነፍሴ እስከ ሞት ድረስ እጅግ አዘነች፤ በዚህ ቈዩ ትጉም አላቸው።
34於是對他們說:“我的心靈痛苦得快要死了;你們要留在這裡,也要警醒。”
35ጥቂትም ወደ ፊት እልፍ ብሎ በምድርም ወድቆ፥ ይቻልስ ቢሆን ሰዓቲቱ ከእርሱ እንድታልፍ ጸለየና።
35耶穌稍往前走,俯伏在地上禱告:如果可能的話,使那時刻不要臨到他。
36አባ አባት ሆይ፥ ሁሉ ይቻልሃል፤ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን አንተ የምትወደው እንጂ እኔ የምወደው አይሁን አለ።
36他說:“阿爸、父啊,你凡事都能作,求你叫這杯離開我。但不要照我的意思,只要照你的旨意。”
37መጣም ተኝተውም አገኛቸው፥ ጴጥሮስንም። ስምዖን ሆይ፥ ተኝተሃልን? አንዲት ሰዓት ስንኳ ልትተጋ አልቻልህምን?
37耶穌回來,看見門徒睡著了,就對彼得說:“西門,你睡覺嗎?你連一個小時也不能警醒嗎?
38ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉ ጸልዩም፤ መንፈስስ ተዘጋጅታለች፥ ሥጋ ግን ደካማ ነው አለው።
38應當警醒、禱告,免得陷入試探;你們心靈雖然願意,肉體卻是軟弱的。”
39ደግሞም ሄዶ ያንኑ ቃል ጸለየ።
39耶穌又去禱告,說的也是同樣的話。
40ደግሞም መጥቶ ዓይኖቻቸው በእንቅልፍ ከብደው ነበርና ተኝተው አገኛቸው፥ የሚመልሱለትንም አላወቁም።
40他再回來的時候,看見門徒睡著了;因為他們十分疲倦,不知道該怎樣回答他。
41ሦስተኛም መጥቶ። እንግዲህስ ተኙ ዕረፉም፤ ይበቃል፤ ሰዓቲቱ ደረሰች፤ እነሆ፥ የሰው ልጅ በኃጢአተኞች እጅ አልፎ ይሰጣል።
41耶穌第三次回來,對他們說:“你們還在睡覺休息嗎?夠了,時候到了,看哪,人子要被交在罪人手裡了。
42ተነሡ፥ እንሂድ፤ እነሆ፥ አሳልፎ የሚሰጠኝ ቀርቦአል አላቸው።
42起來,我們走吧!出賣我的人來了。”
43ወዲያውም ገና ሲናገር ከአሥራ ሁለቱ አንዱ ይሁዳ መጣ፥ ከእርሱም ጋር ብዙ ሰዎች ሰይፍና ጐመድ ይዘው ከካህናት አለቆችና ከጻፎች ከሽማግሌዎችም ዘንድ መጡ።
43耶穌被捕(太26:47~56;路22:47~53;約18:3~11)耶穌還在說話的時候,十二門徒中的猶大和一群拿著刀棒的人來到了;他們是祭司長、經學家和長老派來的。
44አሳልፎ የሚሰጠውም። የምስመው እርሱ ነው፤ ያዙት ተጠንቅቃችሁም ውሰዱት ብሎ ምልክት ሰጥቶአቸው ነበር።
44出賣耶穌的人給他們一個暗號,說:“我跟誰親嘴,誰就是他。你們把他逮捕,小心帶去。”
45መጥቶም ወዲያው ወደ እርሱ ቀረበና። መምህር ሆይ፥ መምህር ሆይ፥ ብሎ ሳመው፤
45猶大來到,立刻上前對耶穌說:“拉比!”就跟他親嘴。
46እነርሱም እጃቸውን በእርሱ ላይ ጭነው ያዙት።
46他們就動手拿住耶穌,逮捕了他。
47በአጠገብ ከቆሙት ግን አንዱ ሰይፉን መዞ የሊቀ ካህናቱን ባሪያ መታ ጆሮውንም ቈረጠ።
47站在旁邊的人中有一個拔出刀來,砍了大祭司的僕人一刀,削掉了他的一隻耳朵。
48ኢየሱስም መልሶ። ወንበዴ እንደምትይዙ ሰይፍና ጐመድ ይዛችሁ ልትይዙኝ መጣችሁን?
48耶穌對他們說:“你們帶著刀棒出來,把我當作強盜捉拿嗎?
49በመቅደስ ዕለት ዕለት እያስተማርሁ ከእናንተ ጋር ስኖር አልያዛችሁኝም፤ ነገር ግን መጻሕፍት ይፈጸሙ ዘንድ ይህ ሆነ አላቸው።
49我天天在殿裡教導人,跟你們在一起,你們卻沒有捉拿我;但這是為了要應驗經上的話。”
50ሁሉም ትተውት ሸሹ።
50門徒都離開他逃跑了。
51ዕርቃኑን በነጠላ የሸፈነ አንድ ጎበዝ ይከተለው ነበር፥
51有一個青年,赤身披著一塊麻布,跟著耶穌。眾人捉住他的時候,
52ጎበዛዝቱም ያዙት፤ እርሱ ግን ነጠላውን ትቶ ዕራቁቱን ሸሸ።
52他就丟掉麻布,赤身逃跑了。
53ኢየሱስንም ወደ ሊቀ ካህናቱ ወሰዱት፥ የካህናት አለቆችም ሁሉ ሽማግሌዎችም ጻፎችም ተሰበሰቡ።
53大祭司審問耶穌(太26:57~68;路22:67~71;約18:12~13、19~24)他們把耶穌押到大祭司那裡,所有的祭司長、長老和經學家都聚集在一起。
54ጴጥሮስም እስከ ሊቀ ካህናቱ ግቢ ውስጥ በሩቁ ተከተለው፥ ከሎሌዎችም ጋር ተቀምጦ እሳት ይሞቅ ነበር።
54彼得遠遠地跟著耶穌,直到大祭司的官邸,和差役一同坐著烤火。
55የካህናት አለቆችም ሸንጎውም ሁሉ እንዲገድሉት በኢየሱስ ላይ ምስክር ይፈልጉ ነበር፥ አላገኙምም፤
55祭司長和公議會全體都尋找證據控告耶穌,要把他處死,卻沒有找著。
56ብዙዎች በሐሰት ይመሰክሩበት ነበርና፥ ምስክርነታቸው ግን አልተሰማማም።
56有許多人作假證供控告他,但他們的證供各不相符。
57ሰዎችም ተነሥተው። እኔ ይህን በእጅ የተሠራውን ቤተ መቅደስ አፈርሰዋለሁ በሦስት ቀንም ሌላውን በእጅ ያልተሠራውን እሠራለሁ ሲል ሰማነው ብለው በሐሰት መሰከሩበት።
57有幾個人站起來,作假證供控告他說:
59ምስክርነታቸውም እንዲሁ እንኳ አልተሰማማም።
58“我們聽他說過:‘我要拆毀這座人手所造的聖所,三日之內要另建一座不是人手所造的聖所。’”
60ሊቀ ካህናቱም በመካከላቸው ተነሥቶ። አንዳች አትመልስምን? እነዚህስ በአንተ ላይ የሚመሰክሩብህ ምንድር ነው? ብሎ ኢየሱስን ጠየቀው።
59就是這樣的見證,他們也不一致。
61እርሱ ግን ዝም አለ አንዳችም አልመለሰም። ደግሞ ሊቀ ካህናቱ ጠየቀውና። የቡሩክ ልጅ ክርስቶስ አንተ ነህን? አለው።
60大祭司站起來,走到中間,問耶穌:“這些人作證控告你的是甚麼呢?你怎麼不回答呢?”
62ኢየሱስም። እኔ ነኝ፤ የሰው ልጅም በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችሁ አለ።
61耶穌卻不作聲,甚麼也不回答。大祭司又問他:“你是那受稱頌者的兒子基督嗎?”
63ሊቀ ካህናቱም ልብሱን ቀደደና። ከእንግዲህ ወዲህ ምስክሮችን ምን ያስፈልገናል?
62耶穌說:“我是。你們要看見人子,坐在權能者的右邊,駕著天上的雲降臨。”
64ስድቡን ሰማችሁ፤ ምን ይመስላችኋል? አለ። እነርሱም ሁሉ። ሞት ይገባዋል ብለው ፈረዱበት።
63大祭司就撕開自己的衣服,說:“我們還要甚麼證人呢?
65አንዳንዶችም ይተፉበት ፊቱንም ሸፍነው ይጐስሙትና። ትንቢት ተናገር ይሉት ጀመር፤ ሎሌዎችም በጥፊ እየመቱ ወሰዱት።
64你們都聽見這褻瀆的話了。你們認為怎麼樣?”眾人都定他該死的罪。
66ጴጥሮስም በግቢ ውስጥ ወደ ታች ሳለ ከሊቀ ካህናቱ ገረዶች አንዲቱ መጣች፥
65於是有些人就向他吐唾沫,蒙住他的臉。用拳頭打他,對他說:“你說預言吧!”差役把他拉去,用手掌打他。
67ጴጥሮስም እሳት ሲሞቅ አይታ ተመለከተችውና። አንተ ደግሞ ከናዝሬቱ ከኢየሱስ ጋር ነበርህ አለችው።
66彼得三次不認主(太26:69~75;路22:54~62;約18:15~18、25~27)彼得在下邊院子的時候,大祭司的一個婢女來了,
68እርሱ ግን። የምትዪውን አላውቅም አላስተውልምም ብሎ ካደ። ወደ ውጭም ወደ ደጅ ወጣ፤ ዶሮም ጮኸ።
67看見彼得烤火,就瞪著他說:“你也是和拿撒勒人耶穌一夥的!”
69ገረዲቱም አይታው በዚያ ለቆሙት። ይህም ከእነርሱ ወገን ነው ስትል ሁለተኛ ትነግራቸው ጀመር።
68彼得卻否認說:“我不知道,也不明白你在說甚麼!”他就走出去,到了前院,雞就叫了(有些抄本無“雞就叫了”一句)。
70እርሱም ደግሞ ካደ። ጥቂት ቈይተውም በዚያ የቆሙት ዳግመኛ ጴጥሮስን። የገሊላ ሰው ነህና ከእነርሱ ወገን በእውነት ነህ አሉት።
69那婢女看見他,又對站在旁邊的人說:“這個人也是他們一夥的。”
71እርሱ ግን። ይህን የምትሉትን ሰው አላውቀውም ብሎ ይረገምና ይምል ጀመር። ወዲያውም ዶሮ ሁለተኛ ጮኸ።
70彼得還是不承認。過了一會,站在旁邊的人也對彼得說:“你真是他們一夥的,因為你也是加利利人。”
72ጴጥሮስንም ኢየሱስ። ዶሮ ሁለት ጊዜ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ ያለው ቃል ትዝ አለው፤ ነገሩንም አስቦ አለቀሰ።
71彼得就發咒起誓說:“我不認得你們說的這個人!”
72立刻雞就叫了第二遍。彼得想起耶穌對他說過的話:“雞叫兩遍以前,你要三次不認我。”他一想起來,就哭了(“他一想起來,就哭了”或譯:“他就奪步而出,痛哭起來”)。