Amharic: New Testament

聖經新譯本

Matthew

13

1በዚያን ቀን ኢየሱስ ከቤት ወጥቶ በባሕር አጠገብ ተቀመጠ፤
1撒種的比喻(可4:1~9;路8:4~8)那一天,耶穌從房子裡出來,坐在海邊。
2እርሱም በታንኳ ገብቶ እስኪቀመጥ ድረስ ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፥ ሕዝቡም ሁሉ በወደቡ ቆመው ነበር።
2有很多人聚集到他那裡。於是,他上船坐下來,眾人都站在岸上。
3በምሳሌም ብዙ ነገራቸው እንዲህም አላቸው። እነሆ፥ ዘሪ ሊዘራ ወጣ።
3他用比喻對眾人講了許多事,說:“有一個撒種的出去撒種。
4እርሱም ሲዘራ አንዳንዱ በመንገድ ዳር ወደቀ፥ ወፎችም መጥተው በሉት።
4撒的時候,有的落在路旁,小鳥飛來就吃掉了。
5ሌላውም ብዙ መሬት በሌለበት በጭንጫ ላይ ወደቀ፤ ጥልቅ መሬትም ስላልነበረው ወዲያው በቀለ፥
5有的落在泥土不多的石地上,因為泥土不深,很快就長起來。
6ፀሐይ በወጣ ጊዜ ግን ጠወለገ፥ ሥርም ስላልነበረው ደረቀ።
6但太陽一出來,就把它曬乾,又因為沒有根就枯萎了。
7ሌላውም በእሾህ መካከል ወደቀ፥ እሾህም ወጣና አነቀው።
7有的落在荊棘裡,荊棘長大了,就把它擠住。
8ሌላውም በመልካም መሬት ወደቀ፤ አንዱም መቶ፥ አንዱም ስድሳ፥ አንዱም ሠላሳ ፍሬ ሰጠ።
8有的落在好土裡,結出果實,有一百倍的,有六十倍的,有三十倍的。
9የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።
9有耳的,就應當聽。”
10ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው። ስለ ምን በምሳሌ ትነግራቸዋለህ? አሉት።
10用比喻的目的(可4:10~12;路8:9~10,10:23~24)門徒上前問耶穌:“你對他們講話,為甚麼用比喻呢?”
11እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው። ለእናንተ የመንግሥተ ሰማያትን ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፥ ለእነርሱ ግን አልተሰጣቸውም።
11他回答:“天國的奧祕,只給你們知道,卻不給他們知道。
12ላለው ይሰጠዋልና ይበዛለትማል፤ ከሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል።
12因為凡是有的,還要給他,他就充足有餘;凡是沒有的,就連他有甚麼也要拿去。
13ስለዚህ እያዩ ስለማያዩ እየሰሙም ስለማይሰሙ ስለማያስተውሉም በምሳሌ እነግራቸዋለሁ።
13因此,我用比喻對他們講話,因為他們看卻看不見,聽也聽不到,也不明白。
14መስማት ትሰማላችሁና አታስተውሉም፥ ማየትም ታያላችሁና አትመለከቱም።
14以賽亞的預言,正應驗在他們身上,他說:‘你們聽是聽見了,總是不明白;看是看見了,總是不領悟。
15በዓይናቸው እንዳያዩ፥ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፥ ተመልሰውም እንዳልፈውሳቸው፥ የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአልና ጆሮአቸውም ደንቁሮአል ዓይናቸውንም ጨፍነዋል የሚል የኢሳይያስ ትንቢት በእነርሱ ይፈጸማል።
15因為這人民的心思遲鈍,用不靈的耳朵去聽,又閉上了眼睛;免得自己眼睛看見,耳朵聽見,心裡明白,回轉過來,我就醫好他們。’
16የእናንተ ግን ዓይኖቻችሁ ስለሚያዩ ጆሮቻችሁም ስለሚሰሙ ብፁዓን ናቸው።
16“你們的眼睛是有福的,因為可以看見;你們的耳朵是有福的,因為可以聽見。
17እውነት እላችኋለሁ፥ ብዙዎች ነቢያትና ጻድቃን የምታዩትን ሊያዩ ተመኝተው አላዩም፥ የምትሰሙትንም ሊሰሙ ተመኝተው አልሰሙም።
17我實在告訴你們,曾經有許多先知和義人想看你們所看見的,卻沒有看到,想聽你們所聽見的,卻沒有聽到。
18እንግዲህ እናንተ የዘሪውን ምሳሌ ስሙ።
18解釋撒種的比喻(可4:13~20;路8:11~15)“所以你們要聽這撒種人的比喻。
19የመንግሥትን ቃል ሰምቶ በማያስተውል ሁሉ፥ ክፉው ይመጣል፥ በልቡ የተዘራውንም ይነጥቃል፤ በመንገድ ዳር የተዘራው ይህ ነው።
19凡是聽了天國的道卻不明白的,那惡者就來把撒在他心中的奪去。這就是撒在路旁的。
20በጭንጫ ላይ የተዘራውም ይህ ቃሉን ሰምቶ ወዲያው በደስታ የሚቀበለው ነው፤
20那撒在石地上的,就是人聽了道,立刻歡歡喜喜地接受,
21ነገር ግን ለጊዜው ነው እንጂ በእርሱ ሥር የለውም፥ በቃሉ ምክንያትም መከራ ወይም ስደት በሆነ ጊዜ ወዲያው ይሰናከላል።
21可是他裡面沒有根,只是暫時的;一旦為道遭遇患難,受到迫害,就立刻跌倒了。
22በእሾህ መካከል የተዘራውም ይህ ቃሉን የሚሰማ ነው፥ የዚህም ዓለም አሳብና የባለጠግነት መታለል ቃሉን ያንቃል፥ የማያፈራም ይሆናል።
22那撒在荊棘裡的,就是人聽了道,有今世的憂慮和財富的迷惑把道擠住,結不出果實來。
23በመልካም መሬት የተዘራውም ይህ ቃሉን ሰምቶ የሚያስተውል ነው፤ እርሱም ፍሬ ያፈራል አንዱም መቶ አንዱም ስድሳ አንዱም ሠላሳ ያደርጋል።
23那撒在好土裡的,就是人聽了道,又明白了,結出果實來,有一百倍的,有六十倍的,有三十倍的。”
24ሌላ ምሳሌ አቀረበላቸው እንዲህም አለ። መንግሥተ ሰማያት በእርሻው መልካም ዘርን የዘራን ሰው ትመስላለች።
24稗子的比喻耶穌對他們另外講了一個比喻,說:“天國好像人把好的種子撒在田裡。
25ሰዎቹ ሲተኙ ግን ጠላቱ መጣና በስንዴው መካከል እንክርዳድን ዘርቶ ሄደ።
25人們睡了的時候,他的仇敵來把稗子撒在麥子中間,就走了。
26ስንዴውም በበቀለና በአፈራ ጊዜ እንክርዳዱ ደግሞ ያን ጊዜ ታየ።
26到了發苗吐穗的時候,稗子也顯出來。
27የባለቤቱም ባሮች ቀርበው። ጌታ ሆይ፥ መልካምን ዘር በእርሻህ ዘርተህ አልነበርህምን? እንክርዳዱንስ ከወዴት አገኘ? አሉት።
27僕人都前來問家主:‘主人,你不是把好的種子撒在田裡嗎?那些稗子是從哪裡來的呢?’
28እርሱም። ጠላት ይህን አደረገ አላቸው። ባሮቹም። እንግዲህ ሄደን ብንለቅመው ትወዳለህን? አሉት።
28他回答:‘這是仇敵所作的。’僕人問他:‘你要我們去拔掉它嗎?’
29እርሱ ግን። እንክርዳዱን ስትለቅሙ ስንዴውን ከእርሱ ጋር እንዳትነቅሉት አይሆንም።
29他說:‘不用,因為拔稗子的時候,恐怕也把麥子連根拔出來。
30ተዉአቸው፤ እስከ መከር ጊዜ አብረው ይደጉ፤ በመከር ጊዜም አጫጆችን። እንክርዳዱን አስቀድማችሁ ልቀሙ በእሳትም ለማቃጠል በየነዶው እሰሩ፥ ስንዴውን ግን በጎተራዬ ክተቱ እላለሁ አለ።
30收割之前,讓它們一同生長。到了收割的時候,我會吩咐收割的工人先拔掉稗子,捆起來,留著焚燒,卻要把麥子收進我的倉裡。’”
31ሌላ ምሳሌ አቀረበላቸው እንዲህም አለ። መንግሥተ ሰማያት ሰው ወስዶ በእርሻው የዘራትን የሰናፍጭ ቅንጣት ትመስላለች፤
31芥菜種和麵酵的比喻(可4:30~32;路13:18~21)耶穌又對他們講了另外一個比喻,說:“天國好像一粒芥菜種,人拿去把它種在田裡。
32እርስዋም ከዘር ሁሉ ታንሳለች፥ በአደገች ጊዜ ግን፥ ከአታክልቶች ትበልጣለች የሰማይም ወፎች መጥተው በቅርንጫፎችዋ እስኪሰፍሩ ድረስ ዛፍ ትሆናለች።
32它是種子中最小的,但長大了,卻比其他的蔬菜都大,成為一棵樹,甚至天空的飛鳥也來在它的枝頭搭窩。”
33ሌላ ምሳሌ ነገራቸው እንዲህም አለ። መንግሥተ ሰማያት ሁሉ እስኪቦካ ድረስ ሴት ወስዳ በሦስት መስፈሪያ ዱቄት የሸሸገችውን እርሾ ትመስላለች።
33他對他們講了另一個比喻:“天國好像麵酵,婦女拿去放在三斗麵裡,直到全團發起來。”
34ኢየሱስም ለሕዝቡ ይህን ሁሉ በምሳሌ ተናገረ፤ በነቢዩም። በምሳሌ አፌን እከፍታለሁ፥ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተሰወረውንም እናገራለሁ የተባለው ይፈጸም ዘንድ ያለ ምሳሌ አልተናገራቸውም።
34解釋稗子的比喻耶穌用比喻向群眾講了這一切,他所講的,沒有不用比喻的。
36በዚያን ጊዜ ሕዝቡን ትቶ ወደ ቤት ገባ። ደቀ መዛሙርቱም ወደ እርሱ ቀርበው። የእርሻውን እንክርዳድ ምሳሌ ተርጕምልን አሉት።
35這就應驗了先知所說的:“我要開口用比喻,把創世以來隱祕的事說出來。”
37እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው። መልካምን ዘር የዘራው የሰው ልጅ ነው፤ እርሻውም ዓለም ነው፤
36耶穌離開群眾,進到屋裡,門徒前來問他:“請你給我們解釋田裡稗子的比喻。”
38መልካሙም ዘር የመንግሥት ልጆች ናቸው፤
37他回答:“那撒好種子的是人子,
39እንክርዳዱም የክፉው ልጆች ናቸው፥ የዘራውም ጠላት ዲያብሎስ ነው፤ መከሩም የዓለም መጨረሻ ነው፥ አጫጆችም መላእክት ናቸው።
38田就是世界,好種子就是屬天國的人,稗子就是屬那惡者的人,
40እንግዲህ እንክርዳድ ተለቅሞ በእሳት እንደሚቃጠል፥ በዓለም መጨረሻ እንዲሁ ይሆናል።
39撒稗子的仇敵是魔鬼,收割的時候是這世代的終結,收割的工人是天使。
41የሰው ልጅ መላእክቱን ይልካል፥ ከመንግሥቱም እንቅፋትን ሁሉ ዓመፃንም የሚያደርጉትን ይለቅማሉ፥
40稗子怎樣被拔掉用火焚燒,在這世代終結的時候,也是一樣。
42ወደ እቶነ እሳትም ይጥሉአቸዋል፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።
41那時,人子要差派他的使者,把一切使人犯罪的事和不法之徒,從他的國中拔掉,
43በዚያን ጊዜ ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ይበራሉ። የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።
42丟進火爐,在那裡必要哀哭切齒。
44ደግሞ መንግሥተ ሰማያት በእርሻ ውስጥ የተሰወረውን መዝገብ ትመስላለች፤ ሰውም አግኝቶ ሰወረው፥ ከደስታውም የተነሣ ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጠና ያን እርሻ ገዛ።
43那時,義人在他們父的國中,要像太陽一樣的照耀。有耳的,就應當聽。
45ደግሞ መንግሥተ ሰማያት መልካምን ዕንቁ የሚሻ ነጋዴን ትመስላለች፤
44其他的比喻“天國好像藏在田裡的寶貝,有人發現了,就把它藏起來,高高興興地離去,變賣了他的一切,來買那田地。
46ዋጋዋም እጅግ የበዛ አንዲት ዕንቁ በአገኘ ጊዜ ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጠና ገዛት።
45“天國好像一個商人,搜羅寶貴的珍珠。
47ደግሞ መንግሥተ ሰማያት ወደ ባሕር የተጣለች ከሁሉም ዓይነት የሰበሰበች መረብን ትመስላለች፤
46他發現了一顆極貴重的珍珠,就離去,變賣了他的一切,來買那顆珍珠。
48በሞላችም ጊዜ ወደ ወደቡ አወጡአት፥ ተቀምጠውም መልካሙን ለቅመው በዕቃዎች ውስጥ አከማቹ ክፉውን ግን ወደ ውጭ ጣሉት።
47“天國又好像一個網,撒在海裡,網到各樣的魚。
49በዓለም መጨረሻ እንዲሁ ይሆናል፤ መላእክት መጥተው ኃጢአተኞችን ከጻድቃን መካከል ይለዩአቸዋል፥ ወደ እቶነ እሳትም ይጥሉአቸዋል፤
48網滿了之後,人就把網拉上岸,坐下來把好的揀出,收藏起來,不好的就丟在外面。
50በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።
49這世代終結的時候,也是一樣。那時天使要出去,把惡人從義人中分別出來。
51ኢየሱስም። ይህን ሁሉ አስተዋላችሁን? አላቸው አዎን አሉት።
50丟進火爐,在那裡必要哀哭切齒。
52እርሱም። ስለዚህ የመንግሥተ ሰማያት ደቀ መዝሙር የሆነ ጻፊ ሁሉ ከመዝገቡ አዲሱንና አሮጌውን የሚያወጣ ባለቤትን ይመስላል አላቸው።
51“這一切你們明白嗎?”他們回答:“明白。”
53ኢየሱስም እነዚህም ምሳሌዎች ከጨረሰ በኋላ ከዚያ ሄደ።
52耶穌說:“所以,每一個作天國門徒的經學家,就像家主從寶庫中拿出新和舊的東西來。”
54ወደ ገዛ አገሩም መጥቶ እስኪገረሙ ድረስ በምኩራባቸው ያስተምራቸው ነበር፤ እንዲህም አሉ። ይህን ጥበብና ተአምራት ይህ ከወዴት አገኘው?
53耶穌在本鄉遭人厭棄(可6:1~6。參路4:16~30)耶穌講完了這些比喻,就離開那地方。
55ይህ የጸራቢ ልጅ አይደለምን? እናቱስ ማርያም ትባል የለምን? ወንድሞቹስ ያዕቆብና ዮሳ ስምዖንም ይሁዳም አይደሉምን?
54他回到自己的家鄉,在會堂裡教導人,眾人都驚奇,說:“這個人的智慧和能力是從哪裡來的呢?
56እኅቶቹስ ሁሉ በእኛ ዘንድ ያሉ አይደሉምን? እንኪያስ ይህን ሁሉ ከወዴት አገኘው? ተሰናከሉበትም።
55他不是木匠的兒子嗎?他母親不是馬利亞,他弟弟不是雅各、約瑟、西門和猶大嗎?
57ኢየሱስ ግን። ነቢይ ከገዛ አገሩና ከገዛ ቤቱ በቀር ሳይከበር አይቀርም አላቸው።
56他妹妹不是都在我們這裡嗎?他這一切是從哪裡來的呢?”
58በአለማመናቸውም ምክንያት በዚያ ብዙ ተአምራት አላደረገም።
57他們就厭棄耶穌。耶穌對他們說:“先知除了在本鄉本家之外,沒有不受人尊敬的。”
58因為他們不信,他就不在那裡多行神蹟了。