Amharic: New Testament

聖經新譯本

Matthew

14

1በዚያ ዘመን የአራተኛው ክፍል ገዥ ሄሮድስ የኢየሱስን ዝና ሰማ፥
1施洗約翰被殺(可6:14~29)那時,分封王希律聽見耶穌的名聲,
2ለሎሌዎቹም። ይህ መጥምቁ ዮሐንስ ነው፤ እርሱ ከሙታን ተነሥቶአል፥ ስለዚህም ኃይል በእርሱ ይደረጋል አለ።
2就對臣僕說:“這人是施洗的約翰,他從死人中復活,所以他身上有行神蹟的能力。”
3ሄሮድስ በወንድሙ በፊልጶስ ሚስት በሄሮድያዳ ምክንያት ዮሐንስን አስይዞ አሳስሮት በወህኒ አኑሮት ነበርና፤
3原來希律為了他弟弟腓力的妻子希羅底的緣故,拘捕了約翰,把他捆綁,關在監裡,
4ዮሐንስ። እርስዋ ለአንተ ትሆን ዘንድ አልተፈቀደም ይለው ነበርና።
4因為約翰多次告訴他:“你佔有她是不合理的。”
5ሊገድለውም ወዶ ሳለ፥ ሕዝቡ እንደ ነቢይ ስለ አዩት ፈራቸው።
5他想殺約翰,但又害怕群眾,因為他們都認為約翰是個先知。
6ነገር ግን ሄሮድስ የተወለደበት ቀን በሆነ ጊዜ፥ የሄሮድያዳ ልጅ በመካከላቸው ዘፈነች ሄሮድስንም ደስ አሰኘችው፤
6到了希律生日的那天,希羅底的女兒在眾人面前跳舞,希律非常高興,
7ስለዚህም የምትለምነውን ሁሉ እንዲሰጣት በመሐላ ተስፋ አደረገላት።
7就起誓答應她,無論求甚麼都給她。
8እርስዋም በእናትዋ ተመክራ። የመጥምቁን የዮሐንስን ራስ በዚህ በወጭት ስጠኝ አለችው።
8她在母親的慫恿之下,說:“請把施洗的約翰的頭放在盤子上給我。”
9ንጉሡም አዘነ፥ ነገር ግን ስለ መሐላው ከእርሱም ጋር ተቀምጠው ስላሉት ሰዎች እንዲሰጡአት አዘዘ፤
9王就憂愁,但因為誓言和在座的賓客,就下令給她。
10ልኮም የዮሐንስን ራስ በወህኒ አስቆረጠው።
10他派人去,在監裡斬了約翰的頭,
11ራሱንም በወጭት አምጥተው ለብላቴናይቱ ሰጡአት፥ ወደ እናትዋም ወሰደችው።
11把頭放在盤子上,拿來給那女孩子,她又帶給母親。
12ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው በድኑን ወሰዱና ቀበሩት፥ መጥተውም ለኢየሱስ አወሩለት።
12約翰的門徒前來,領了屍體,把它埋葬,然後去告訴耶穌。
13ኢየሱስም በሰማ ጊዜ ከዚያ ብቻውን ወደ ምድረ በዳ በታንኳ ፈቀቅ አለ፤ ሕዝቡም ሰምተው ከከተማዎቹ በእግር ተከተሉት።
13給五千人吃飽的神蹟(可6:32~44;路9:10~17;約6:1~13。參太15:32~38)耶穌聽見了,就離開那裡,獨自坐船到曠野去。群眾聽見了,就從各城步行來跟隨他。
14ወጥቶም ብዙ ሕዝብ አየና አዘነላቸው ድውዮቻቸውንም ፈወሰ።
14耶穌上了岸,看見一大群人,就憐憫他們,醫好了他們的病人。
15በመሸም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀርበው። ቦታው ምድረ በዳ ነው አሁንም ሰዓቱ አልፎአል፤ ወደ መንደሮች ሄደው ለራሳቸው ምግብ እንዲገዙ ሕዝቡን አሰናብት አሉት።
15黃昏的時候,門徒前來對他說:“這是曠野的地方,時間也不早了,請叫群眾散開,好讓他們往村裡去,買自己的食物吧。”
16ኢየሱስም። እናንተ የሚበሉትን ስጡአቸው እንጂ ሊሄዱ አያስፈልግም አላቸው።
16耶穌回答:“他們用不著離開,你們給他們吃吧!”
17እነርሱም። ከአምስት እንጀራና ከሁለት ዓሣ በቀር በዚህ የለንም አሉት።
17但門徒說:“我們這裡除了五個餅和兩條魚,甚麼也沒有。”
18እርሱም። እነዚያን ወደዚህ አምጡልኝ አላቸው።
18他說:“拿過來給我。”
19ሕዝቡም በሣር ላይ እንዲቀመጡ አዘዘ፥ አምስቱንም እንጀራና ሁለቱን ዓሣ ይዞ ወደ ሰማይ አሻቅቦ አየና ባረከ፥ እንጀራውንም ቆርሶ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፥ ደቀ መዛሙርቱም ለሕዝቡ።
19於是吩咐群眾坐在草地上,拿起那五個餅兩條魚,望著天,祝謝了;然後把餅擘開,遞給門徒,門徒又分給群眾。
20ሁሉም በልተው ጠገቡ፥ የተረፈውንም ቁርስራሽ አሥራ ሁለት መሶብ ሙሉ አነሡ።
20大家都吃了,並且吃飽了,他們把剩下的零碎拾起來,裝滿了十二個籃子。
21ከሴቶችና ከልጆችም በቀር የበሉት አምስት ሺህ ወንዶች ያህሉ ነበር።
21吃的人,除了婦女和孩子,約有五千。
22ወዲያውም ሕዝቡን ሲያሰናብት ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ በታንኳይቱ ገብተው ወደ ማዶ እንዲቀድሙት ግድ አላቸው።
22耶穌在海面上行走(可6:45~52;約6:15~21)耶穌立刻催門徒上船,叫他們先到對岸去,他卻留下來叫群眾散開。
23ሕዝቡንም አሰናብቶ ይጸልይ ዘንድ ብቻውን ወደ ተራራ ወጣ። በመሸም ጊዜ ብቻውን በዚያ ነበረ።
23他解散了群眾,就獨自上山去禱告。到了晚上,他還是獨自一人在那裡。
24ታንኳይቱም አሁን በባሕር መካከል ሳለች፥ ነፋስ ከወደ ፊት ነበርና በማዕበል ትጨነቅ ነበር።
24那時門徒的船已經離岸數公里,因為逆風,被波浪沖擊。
25ከሌሊቱም በአራተኛው ክፍል ኢየሱስ በባሕር ላይ እየሄደ ወደ እነርሱ መጣ።
25天快亮的時候(“天快亮的時候”原文作“夜裡四更天”),耶穌在海面上向他們走過去。
26ደቀ መዛሙርቱም በባሕር ላይ ሲሄድ ባዩት ጊዜ። ምትሐት ነው ብለው ታወኩ በፍርሃትም ጮኹ።
26門徒見他在海面上行走,就很驚慌,說:“有鬼啊!”並且恐懼得大叫起來。
27ወዲያውም ኢየሱስ ተናገራቸውና። አይዞአችሁ፥ እኔ ነኝ፤ አትፍሩ አላቸው።
27耶穌立刻對他們說:“放心吧!是我,不要怕。”
28ጴጥሮስም መልሶ። ጌታ ሆይ፥ አንተስ ከሆንህ በውኃው ላይ ወደ አንተ እንድመጣ እዘዘኝ አለው።
28彼得對他說:“主啊,如果是你,讓我在水面上到你那裡去。”
29እርሱም። ና አለው። ጴጥሮስም ከታንኳይቱ ወርዶ ወደ ኢየሱስ ሊደርስ በውኃው ላይ ሄደ።
29他說:“來吧!”彼得就從船上下來,行在水面上,走向耶穌那裡去。
30ነገር ግን የነፋሱን ኃይል አይቶ ፈራ፥ ሊሰጥምም በጀመረ ጊዜ። ጌታ ሆይ፥ አድነኝ ብሎ ጮኸ።
30但他一見風浪就害怕,快要沉下去的時候,就呼叫:“主啊!救我!”
31ወዲያውም ኢየሱስ እጁን ዘርግቶ ያዘውና። አንተ እምነት የጎደለህ፥ ስለምን ተጠራጠርህ? አለው።
31耶穌馬上伸手拉住他,對他說:“小信的人哪,為甚麼疑惑?”
32ወደ ታንኳይቱም በወጡ ጊዜ ነፋሱ ተወ።
32他們上了船,風就平靜了。
33በታንኳይቱም የነበሩት። በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ብለው ሰገዱለት።
33船上的人都拜他,說:“你真是 神的兒子。”
34ተሻግረውም ወደ ጌንሴሬጥ ምድር መጡ።
34治好革尼撒勒的病人(可6:53~56)他們過到對岸,來到革尼撒勒的地區。
35የዚያ ቦታ ሰዎችም ባወቁት ጊዜ በዙርያው ወዳለ አገር ሁሉ ላኩ፥ ሕመምተኞችንም ሁሉ ወደ እርሱ አመጡ፤
35那地的人認出是耶穌,就把消息傳遍了那一帶。眾人把一切有病的人都帶來,
36የልብሱንም ጫፍ ብቻ ሊዳስሱ ይለምኑት ነበር፤ የዳሰሱትም ሁሉ ዳኑ።
36求耶穌讓他們只摸一摸他衣服的繸子,摸著的人就都痊愈了。