1በዚያን ጊዜ መንግሥተ ሰማያት መብራታቸውን ይዘው ሙሽራውን ሊቀበሉ የወጡ አሥር ቆነጃጅትን ትመስላለች።
1十個童女的比喻“那時,天國好像十個童女,拿著她們的燈出去迎接新郎。
2ከእነርሱም አምስቱ ሰነፎች አምስቱም ልባሞች ነበሩ።
2她們中間有五個是愚蠢的,五個是聰明的。
3ሰነፎቹ መብራታቸውን ይዘው ከእነርሱ ጋር ዘይት አልያዙምና፤
3那些愚蠢的拿著燈,卻沒有帶油;
4ልባሞቹ ግን ከመብራታቸው ጋር በማሰሮአቸው ዘይት ያዙ።
4但那些聰明的拿著燈,也把油裝在瓶裡帶來。
5ሙሽራውም በዘገየ ጊዜ ሁሉ እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ተኙ።
5新郎很晚還沒有到,她們都打瞌睡,而且睡著了。
6እኩል ሌሊትም ሲሆን። እነሆ፥ ሙሽራው ይመጣል፥ ትቀበሉት ዘንድ ውጡ የሚል ውካታ ሆነ።
6半夜,有人喊叫:‘新郎來了,快出來迎接他。’
7በዚያን ጊዜ እነዚያ ቆነጃጅት ሁሉ ተነሡና መብራታቸውን አዘጋጁ።
7那些童女都醒過來,整理她們的燈。
8ሰነፎቹም ልባሞቹን። መብራታችን ሊጠፋብን ነው፤ ከዘይታችሁ ስጡን አሉአቸው።
8愚蠢的對聰明的說:‘請把你們的油分一點給我們,我們的燈快要滅了。’
9ልባሞቹ ግን መልሰው። ምናልባት ለእኛና ለእናንተ ባይበቃስ፤ ይልቅስ ወደሚሸጡት ሄዳችሁ ለራሳችሁ ግዙ አሉአቸው።
9聰明的回答:‘這些恐怕不夠我們大家用,不如你們自己到賣油的地方去買吧!’
10ሊገዙም በሄዱ ጊዜ ሙሽራው መጣ፥ ተዘጋጅተው የነበሩትም ከእርሱ ጋር ወደ ሰርግ ገቡ፥ ደጁም ተዘጋ።
10她們去買油的時候,新郎來了;準備好了的童女就和他一同進去參加婚筵,門就關上了。
11በኋላም ደግሞ የቀሩቱ ቈነጃጅት መጡና። ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ፥ ክፈትልን አሉ።
11後來,其餘的童女也來到,說:‘主啊,主啊,給我們開門吧!’
12እርሱ ግን መልሶ። እውነት እላችኋለሁ፥ አላውቃችሁም አለ።
12新郎卻回答:‘我實在告訴你們,我不認識你們。’
13ቀኒቱንና ሰዓቲቱን አታውቁምና እንግዲህ ንቁ።
13所以你們要警醒,因為不知道那日子和那時間。
14ወደ ሌላ አገር የሚሄድ ሰው ባሮቹን ጠርቶ ያለውን ገንዘብ እንደ ሰጣቸው እንዲሁ ይሆናልና፤
14三個僕人的比喻(路19:12~27)“天國又像一個人要出外遠行,就叫自己的僕人來,把產業交給他們。
15ለእያንዳንዱ እንደ ዓቅሙ፥ ለአንዱ አምስት መክሊት ለአንዱ ሁለት ለአንዱም አንድ ሰጠና ወደ ሌላ አገር ወዲያው ሄደ።
15他按照各人的才幹,一個給三萬個銀幣,一個給一萬二千個銀幣,一個給六千個銀幣(原文作“五個,二個,一個他連得”;一個他連得等於六千個銀幣),然後就遠行去了。
16አምስት መክሊትም የተቀበለው ሄዶ ነገደበት ሌላም አምስት አተረፈ፤
16那領了三萬的馬上去做生意,另外賺了三萬。
17እንዲሁም ሁለት የተቀበለው ሌላ ሁለት አተረፈ።
17那領了一萬二千的也是這樣,另賺了一萬二千。
18አንድ የተቀበለው ግን ሄዶ ምድርን ቈፈረና የጌታውን ገንዘብ ቀበረ።
18但那領了六千的,卻去把地挖開,把主人的錢藏起來。
19ከብዙ ዘመንም በኋላ የእነዚያ ባሮች ጌታ መጣና ተቆጣጠራቸው።
19過了很久,那些僕人的主人回來了,要和他們算帳。
20አምስት መክሊት የተቀበለውም ቀረበና ሌላ አምስት መክሊት አስረክቦ። ጌታ ሆይ፥ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ፥ ሌላ አምስት መክሊት አተረፍሁበት አለ።
20那領了三萬個銀幣的,帶著另外的三萬前來,說:‘主啊,你交了三萬給我,你看,我又賺了三萬。’
21ጌታውም። መልካም፥ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው።
21主人對他說:‘又良善又忠心的僕人哪,你作得好!你既然在不多的事上忠心,我要派你管理許多的事。進來,享受你主人的快樂吧!’
22ሁለት መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ። ጌታ ሆይ፥ ሁለት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ፥ ሌላ ሁለት መክሊት አተረፍሁበት አለ።
22那領了一萬二千的也前來,說:‘主啊,你交了一萬二千給我,你看,我又賺了一萬二千。’
23ጌታውም። መልካም፥ አንተ በጎ፥ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ እሾምሃለሁ፥ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው።
23主人對他說:‘又良善又忠心的僕人哪,你作得好!你既然在不多的事上忠心,我要派你管理許多的事。進來,享受你主人的快樂吧!’
24አንድ መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ። ጌታ ሆይ፥ ካልዘራህባት የምታጭድ ካልበተንህባትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ፤
24那領了六千的也前來,說:‘主啊,我知道你是個嚴厲的人,沒有撒種的地方,你要收割;沒有散播的地方,你要收聚。
25ፈራሁም ሄጄም መክሊትህን በምድር ቀበርሁት፤ እነሆ፥ መክሊትህ አለህ አለ።
25所以,我就害怕起來,去把你的錢藏在地裡。你看,你的錢還在這裡。’
26ጌታውም መልሶ እንዲህ አለው። አንተ ክፉና ሃኬተኛ ባሪያ፥ ካልዘራሁባት እንዳጭድ ካልበተንሁባትም እንድሰበስብ ታውቃለህን?
26可是主人對他說:‘你這個又可惡又懶惰的僕人,你既然知道我要在沒有撒種的地方收割,在沒有散播的地方收聚,
27ስለዚህ ገንዘቤን ለለዋጮች አደራ ልትሰጠው በተገባህ ነበር፥ እኔም መጥቼ ያለኝን ከትርፉ ጋር እወስደው ነበር።
27那你就應該把我的錢存入銀行,到我回來的時候,可以連本帶利收回。
28ስለዚህ መክሊቱን ውሰዱበት አሥር መክሊትም ላለው ስጡት፤
28你們把他的六千銀幣拿去,交給那個有六萬的。
29ላለው ሁሉ ይሰጠዋልና ይበዛለትማል፤ ከሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል።
29因為凡是有的,還要給他,他就充足有餘;凡是沒有的,就算他有甚麼也要拿去。
30የማይጠቅመውንም ባሪያ በውጭ ወዳለው ጨለማ አውጡት፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።
30把這沒有用的僕人丟在外面的黑暗裡,在那裡必要哀哭切齒。’
31የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክቱ ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል፤
31人子必審判萬族“當人子在他的榮耀裡,帶著所有的使者降臨的時候,他要坐在榮耀的寶座上。
32አሕዛብም ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛም በጎቹን ከፍየሎች እንደሚለይ እርስ በርሳቸው ይለያቸዋል፥
32萬族要聚集在他面前,他要把他們彼此分開,好像牧羊人把綿羊和山羊分開一樣:
33በጎችን በቀኙ ፍየሎችንም በግራው ያቆማቸዋል።
33把綿羊放在右邊,山羊放在左邊。
34ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል። እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ።
34那時,王要對右邊的說:‘蒙我父賜福的,來承受創世以來為你們預備好的國吧。
35ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፥ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፥
35因為我餓了,你們給我吃;我渴了,你們給我喝;我作旅客,你們接待我;
36ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።
36我赤身露體,你們給我衣服穿;我病了,你們看顧我;我在監裡,你們來看我。’
37ጻድቃንም መልሰው ይሉታል። ጌታ ሆይ፥ ተርበህ አይተን መቼ አበላንህስ? ወይስ ተጠምተህ አይተን መቼ አጠጣንህ?
37義人就回答:‘主啊,我們甚麼時候見你餓了就給你吃,渴了就給你喝呢?
38እንግዳ ሆነህስ አይተን መቼ ተቀበልንህ? ወይስ ታርዘህ አይተን መቼ አለበስንህ?
38又甚麼時候見你作旅客就接待你,赤身露體就給你衣服穿呢?
39ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ አይተን መቼ ወደ አንተ መጣን?
39或者甚麼時候見你病了,或在監裡就來看你呢?’
40ንጉሡም መልሶ። እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ይላቸዋል።
40王要回答他們:‘我實在告訴你們,你們所作的,只要是作在我一個最小的弟兄身上,就是作在我的身上了。’
41በዚያን ጊዜ በግራው ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል። እናንተ ርጉማን፥ ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ።
41“王也要對左邊的說:‘你們這被咒詛的,離開我,到為魔鬼和他的使者所預備的永火裡去吧!
42ተርቤ አላበላችሁኝምና፥ ተጠምቼ አላጠጣችሁኝምና፥ እንግዳ ሆኜ አልተቀበላችሁኝምና፥
42因為我餓了,你們沒有給我吃;我渴了,你們沒有給我喝;
43ታርዤ አላለበሳችሁኝምና፥ ታምሜ ታስሬም አልጠየቃችሁኝምና።
43我作旅客,你們沒有接待我;我赤身露體,你們沒有給我衣服穿;我病了,我在監裡,你們沒有看顧我。’
44እነርሱ ደግሞ ይመልሱና። ጌታ ሆይ፥ ተርበህ ወይስ ተጠምተህ ወይስ እንግዳ ሆነህ ወይስ ታርዘህ ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ መቼ አይተን አላገለገልንህም? ይሉታል።
44他們就回答:‘主啊,我們甚麼時候見你餓了、渴了、作旅客、赤身露體、病了,或在監裡,卻沒有服事你呢?’
45ያን ጊዜ። እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ለአንዱ ስላላደረጋችሁት ለእኔ ደግሞ አላደረጋችሁትም ብሎ ይመልስላቸዋል።
45王要回答他們:‘我實在告訴你們,這些事你們既然沒有作在一個最小的身上,就是沒有作在我的身上了。’
46እነዚያም ወደ ዘላለም ቅጣት፥ ጻድቃን ግን ወደ ዘላለም ሕይወት ይሄዳሉ።
46他們要進入永遠的刑罰,義人卻要進入永生。”