1ከዚያ ወዲያ ኢየሱስ ከዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ መንፈስ ወደ ምድረ በዳ ወሰደው፥
1耶穌受試探(可1:12~13;路4:1~13)隨後,耶穌被聖靈帶到曠野,受魔鬼的試探。
2አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ከጦመ በኋላ ተራበ።
2耶穌禁食了四十晝夜,就餓了,
3ፈታኝም ቀርቦ። የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፥ እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ በል አለው።
3試探者前來對他說:“你若是 神的兒子,就吩咐這些石頭變成食物吧!”
4እርሱም መልሶ። ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል አለው።
4耶穌回答:“經上記著:‘人活著,不是單靠食物,更要靠 神口裡所出的一切話。’”
5ከዚህ በኋላ ዲያቢሎስ ወደ ቅድስት ከተማ ወሰደውና እርሱን በመቅደስ ጫፍ ላይ አቁሞ።
5隨後,魔鬼帶耶穌進了聖城,使他站在殿頂上,
6መላእክቱን ስለ አንተ ያዝልሃል እግርህንም በድንጋይ ከቶ እንዳትሰናከል በእጃቸው ያነሡሃል ተብሎ ተጽፎአልና የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ፥ ወደ ታች ራስህን ወርውር አለው።
6對他說:“你若是 神的兒子,就跳下去吧!因為經上記著:‘ 神為了你,會吩咐自己的使者用手托住你,免得你的腳碰到石頭。’”
7ኢየሱስም። ጌታን አምላክህን አትፈታተነው ተብሎ ደግሞ ተጽፎአል አለው።
7耶穌對他說:“經上又記著:‘不可試探主你的 神。’”
8ደግሞ ዲያቢሎስ እጅግ ረጅም ወደ ሆነ ተራራ ወሰደው፥ የዓለምንም መንግሥታት ሁሉ ክብራቸውንም አሳይቶ።
8最後,魔鬼帶耶穌上了一座極高的山,把世界各國和各國的榮華都指給他看。
9ወድቀህ ብትሰግድልኝ ይህን ሁሉ እሰጥሃለሁ አለው።
9並且對他說:“你只要跪下來拜我,我就把這一切都給你。”
10ያን ጊዜ ኢየሱስ። ሂድ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአልና አለው።
10但耶穌說:“撒但,走開!經上記著:‘當拜主你的 神,單要事奉他。’”
11ያን ጊዜ ዲያቢሎስ ተወው፥ እነሆም፥ መላእክት ቀርበው ያገለግሉት ነበር።
11於是魔鬼離開了耶穌,有天使前來服事他。
12ኢየሱስም ዮሐንስ አልፎ እንደ ተሰጠ በሰማ ጊዜ ወደ ገሊላ ፈቀቅ ብሎ ሄደ።
12耶穌在加利利傳道(可1:14~20;路4:14~15,5:1~11,6:17~19;約1:35~42)耶穌聽見約翰被捕,就往加利利去。
13ናዝሬትንም ትቶ በዛብሎንና በንፍታሌም አገር በባሕር አጠገብ ወደ አለችው ወደ ቅፍርናሆም መጥቶ ኖረ።
13他又離開拿撒勒,往西布倫和拿弗他利境內近海的迦百農去,住在那裡,
14በነቢዩም በኢሳይያስ። የዛብሎን ምድርና የንፍታሌም ምድር፥ የባሕር መንገድ፥ በዮርዳኖስ ማዶ፥ የአሕዛብ ገሊላ፤ በጨለማ የተቀመጠው ሕዝብ ታላቅ ብርሃን አየ፥ በሞት አገርና ጥላ ለተቀመጡትም ብርሃን ወጣላቸው
14為了要應驗以賽亞先知所說的:
17የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሆነ። ከዚያ ዘመን ጀምሮ ኢየሱስ። መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ እያለ ይሰብክ ጀመር።
15“西布倫地、拿弗他利地,沿海之路,約旦河外,外族人的加利利啊!
18በገሊላ ባሕር አጠገብ ሲመላለስም ሁለት ወንድማማች ጴጥሮስ የሚሉትን ስምዖንን ወንድሙንም እንድርያስን መረባቸውን ወደ ባሕር ሲጥሉ አየ፥ ዓሣ አጥማጆች ነበሩና።
16住在黑暗中的人民,看見了大光;死亡幽暗之地的居民,有光照亮他們。”
19እርሱም። በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ አላቸው።
17從那時起,耶穌就開始傳道,說:“天國近了,你們應當悔改。”
20ወዲያውም መረባቸውን ትተው ተከተሉት።
18耶穌在加利利海邊行走的時候,看見兄弟二人,就是名叫彼得的西門和他的弟弟安得烈,正在把網撒到海裡去;他們是漁夫。
21ከዚያም እልፍ ብሎ ሌሎችን ሁለት ወንድማማች የዘብዴዎስን ልጅ ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ከአባታቸው ከዘብዴዎስ ጋር በታንኳ መረባቸውን ሲያበጁ አየ፤ ጠራቸውም።
19耶穌就對他們說:“來跟從我,我要使你們作得人的漁夫。”
22እነርሱም ወዲያው ታንኳይቱንና አባታቸውን ትተው ተከተሉት።
20他們立刻撇下網,跟從了他。
23ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ በሕዝብም ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ በገሊላ ሁሉ ይዞር ነበር።
21耶穌又往前走,看見另一對兄弟,就是西庇太的兒子雅各和約翰,正和父親西庇太在船上整理魚網,他就呼召他們。
24ዝናውም ወደ ሶርያ ሁሉ ወጣ፤ በልዩ ልዩ ደዌና ሥቃይም ተይዘው የታመሙትን ሁሉ አጋንንትም ያደሩባቸውን በጨረቃም የሚነሣባቸውን ሽባዎችንም ወደ እርሱ አመጡ፥ ፈወሳቸውም።
22他們立刻離了船,別了父親,跟從了耶穌。
25ከገሊላም ከአሥሩ ከተማም ከኢየሩሳሌምም ከይሁዳም ከዮርዳኖስም ማዶ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት።
23耶穌走遍加利利,在各會堂裡教導人,宣揚天國的福音,醫治民間各種疾病、各種病症。
24他的名聲傳遍了敘利亞全地,人們就把一切患病的,就是患各種疾病、疼痛、鬼附、癲癇、癱瘓的,都帶到他面前,他就醫好他們。
25於是有許多人從加利利、低加波利、耶路撒冷、猶太和約旦河東來跟從耶穌。