1ከዚህ በኋላ ታላቅ ስልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፥ ከክብሩም የተነሣ ምድር በራች።
1大巴比倫傾倒這些事以後,我看見有另一位掌大權柄的天使,從天上降下來,他的榮光照亮了大地。
2በብርቱም ድምፅ። ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች፥ ወደቀች፥ የአጋንንትም ማደሪያ ሆነች፥ የርኵሳንም መናፍስት ሁሉ መጠጊያ የርኵሳንና የተጠሉም ወፎች ሁሉ መጠጊያ ሆነች፤
2他用強有力的聲音呼喊說:“傾倒了!大巴比倫傾倒了!成了鬼魔的住處,各樣污靈的監獄,一切污穢可憎之雀鳥的牢籠,
3አሕዛብ ሁሉ ከዝሙትዋ ቍጣ ወይን ጠጅ የተነሳ ወድቀዋልና፥ የምድርም ነገሥታት ከእርስዋ ጋር ሴሰኑ የምድርም ነጋዴዎች ከቅምጥልነትዋ ኃይል የተነሳ ባለ ጠጋዎች ሆኑ ብሎ ጮኸ።
3因為各國都喝她淫亂烈怒的酒醉了;地上的君王與她行淫,世上的商人因她奢華揮霍就發了財。”
4ከሰማይም ሌላ ድምፅ ሰማሁ እንዲህ ሲል። ሕዝቤ ሆይ፥ በኃጢአትዋ እንዳትተባበሩ ከመቅሠፍትዋም እንዳትቀበሉ ከእርስዋ ዘንድ ውጡ፤
4我聽見另一個聲音從天上來,說:“出來吧!我的子民,要從那城出來,免得在她的罪上有分,受她所受的災難;
5ኃጢአትዋ እስከ ሰማይ ድረስ ደርሶአልና፥ እግዚአብሔርም ዓመፃዋን አሰበ።
5因為她的罪惡滔天, 神已經想起她的不義來。
6እርስዋ እንደ ሰጠች መጠን ብድራት መልሱላት፥ እንደ ሥራዋም ሁለት እጥፍ ደርቡባት፤ በቀላቀለችው ጽዋ ሁለት እጥፍ አድርጋችሁ ቀላቅሉባት፤
6她怎樣待人,你們也要怎樣待她;照著她所作的,加倍報應她;用她調酒的杯,加倍調給她。
7ራስዋን እንደ አከበረችና እንደ ተቀማጠለች ልክ ሥቃይና ኀዘን ስጡአት። በልብዋ። ንግሥት ሆኜ እቀመጣለሁ ባልቴትም አልሆንም ኀዘንም ከቶ አላይም ስላለች፥
7她怎樣炫耀自己,怎樣奢華揮霍,你們也要怎樣給她痛苦悲哀。因為她心裡常常說:‘我坐著作女王,我不是寡婦,決不會看見悲哀。’
8ስለዚህ በአንድ ቀን ሞትና ኀዘን ራብም የሆኑ መቅሰፍቶችዋ ይመጣሉ፥ በእሳትም ትቃጠላለች፤ የሚፈርድባት እግዚአብሔር ብርቱ ነውና።
8因此,在一日之內她的災難必然來到,就是死亡、悲哀和饑荒;她還要在火中被燒掉,因為審判她的主 神是大有能力的。
9ከእርስዋም ጋር የሴሰኑና የተቀማጠሉ የምድር ነገሥታት የመቃጠልዋን ጢስ ሲያዩ ስለ እርስዋ ዋይ ዋይ እያሉ ያለቅሳሉ፤
9“地上的眾王,就是跟她一同行邪淫、驕奢無度的,看見焚燒她的煙的時候,就必為她痛哭捶胸。
10ሥቃይዋንም ከመፍራት የተነሣ በሩቅ ቆመው። አንቺ ታላቂቱ ከተማ፥ ብርቱይቱ ከተማ ባቢሎን፥ ወዮልሽ፥ ወዮልሽ፥ በአንድ ሰዓት ፍርድሽ ደርሶአልና እያሉ ይናገራሉ።
10他們因為害怕她所受的痛苦,就遠遠地站著,說:‘有禍了!有禍了!這大城,巴比倫,這堅固的城啊!一時之間你的審判就來到了!’
11የመርከባቸውንም ጭነት ከእንግዲህ ወዲህ የሚገዛ የለምና የምድር ነጋዴዎች ያለቅሱላታል ያዝኑላትማል፤
11“地上的商人也為她悲哀痛哭,因為沒有人再買他們的貨物:
12ጭነትም ወርቅና ብር የከበረም ድንጋይ ዕንቁም፥ ቀጭንም ተልባ እግር ቀይም ሐርም ሐምራዊም ልብስ የሚሸትም እንጨት ሁሉ፥ ከዝሆን ጥርስም የተሰራ ዕቃ ሁሉ፥ እጅግም ከከበረ እንጨት ከናስም ከብረትም ከዕብነ በረድም የተሰራ ዕቃ ሁሉ፥
12就是金、銀、寶石、珍珠;細麻布、紫色布、絲綢、朱紅色布;各樣香木,各樣象牙製品,各樣極貴重的木器、銅器、鐵器、大理石製品;
13ቀረፋም ቅመምም የሚቃጠልም ሽቱ ቅባትም ዕጣንም የወይን ጠጅም ዘይትም የተሰለቀ ዱቄትም ስንዴም ከብትም በግም ፈረስም ሰረገላም ባሪያዎችም የሰዎችም ነፍሳት ነው።
13肉桂、荳蔻、香料、香膏、乳香;酒、油、麵粉、麥子;牛、羊、馬、車、奴僕、人口。
14ነፍስሽም የጎመጀችው ፍሬ ከአንቺ ዘንድ አልፎአል፥ የሚቀማጠልና የሚያጌጥም ነገር ሁሉ ጠፍቶብሻል፥ ሰዎችም ከእንግዲህ ወዲህ ከቶ አያገኙአቸውም።
14你所貪戀的果子離開你了!一切珍饈美味、華麗的美物,都從你那裡消失,再也找不到了!
15እነዚህን የነገዱ በእርስዋም ባለ ጠጋዎች የሆኑት እያለቀሱና እያዘኑ። በቀጭን ተልባ እግርና በቀይ ሐምራዊም ልብስ ለተጐናጸፈች በወርቅና በከበረ ድንጋይም በዕንቁም ለተሸለመች ለታላቂቱ ከተማ ወዮላት፥ ወዮላት፥ ይህን የሚያህል ታላቅ ባለ ጠግነት በአንድ ሰዓት ጠፍቶአልና እያሉ ስቃይዋን ከመፍራት የተነሣ በሩቅ ይቆማሉ። የመርከብም መሪ ሁሉ በመርከብም ወደ ማናቸውም ስፍራ የሚሄድ ሁሉ መርከበኞችም ከባሕርም የሚጠቀሙ ሁሉ በሩቅ ቆሙ፥
15販賣這些貨物,藉著她發了財的商人,因為害怕她受的痛苦,就遠遠地站著,痛哭悲哀,
18የመቃጠልዋንም ጢስ ባዩ ጊዜ። ታላቂቱን ከተማ የምትመስላት ምን ከተማ ነበረች? እያሉ ጮኹ።
16說:‘有禍了!有禍了!這大城啊!就是一向穿著細麻布、紫色、朱紅色的衣服,佩戴著金子、寶石和珍珠裝飾的,
19በራሳቸውም ላይ ትቢያ ነስንሰው እያለቀሱና እያዘኑ። በባሕር መርከቦች ያሉአቸውን ሁሉ ከባለ ጠግነትዋ የተነሣ ባለ ጠጋዎች ላደረገች ለታላቂቱ ከተማ ወዮላት፥ ወዮላት፥ በአንድ ሰዓት ጠፍታለችና እያሉ ጮኹ።
17一時之間,這麼大的財富竟蕩然無存!’“所有船長、旅客、水手,以及凡是靠海謀生的,都遠遠地站著。
20ሰማይ ሆይ፥ ቅዱሳን ሐዋርያት ነቢያትም ሆይ፥ በእርስዋ ላይ ደስ ይበላችሁ፥ እግዚአብሔር ፈርዶላችኋልና።
18他們看見了焚燒她的煙,就喊叫說:‘有哪一座城能與這大城相比呢?’
21አንድም ብርቱ መልአክ ትልቅን ወፍጮ የሚመስልን ድንጋይ አንስቶ ወደ ባሕር ወረወረው እንዲህ ሲል። ታላቂቱ ከተማ ባቢሎን እንዲህ ተገፍታ ትወድቃለች ከእንግዲህም ወዲህ ከቶ አትገኝም።
19他們又把塵土撒在自己頭上,痛哭悲哀,喊著說:‘有禍了!有禍了!這大城啊!凡是有船航行海上的,都因這城的財寶發了財;一時之間她竟成了荒場!’
22በገና የሚመቱና የሚዘምሩም ድምፅ እንቢልታንና መለከትንም የሚነፉ ድምፅ ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፥ የእጅ ጥበብም ሁሉ አንድ ብልሃተኛ እንኳ ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይገኝም፥ የወፍጮ ድምጽም ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፥
20天哪,你要因她歡喜!眾聖徒、眾使徒、眾先知啊,你們也要因她歡喜!因為 神已經在她身上為你們伸了冤。”
23የመብራትም ብርሃን ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይበራም፥ የሙሽራና የሙሽራይቱም ድምጽ ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፤ ነጋዴዎችሽ የምድር መኳንንት ነበሩና፥ በአስማትሽም አሕዛብ ሁሉ ስተዋልና።
21有一位大力的天使,把一塊好像大磨石一樣的石頭,舉起來拋在海裡,說:“巴比倫大城也必這樣被猛力地拋下去,決不能再找到了!
24በእርስዋም ውስጥ የነቢያትና የቅዱሳን ደም በምድርም የታረዱ ሁሉ ደም ተገኘባት።
22彈琴、奏樂、吹笛、吹號的聲音,在你中間決不能再聽到了!各樣手藝技工,在你中間決不能再找到了!推磨的聲音,在你中間決不能再聽到了!
23燈的亮光,在你中間決不能再照耀了!新郎新娘的聲音,在你中間決不能再聽到了!你的商人一向都是地上的大人物,萬國都因你的邪術受了迷惑。
24先知、聖徒和地上一切被殺的人的血,都在這城裡找到了!”